You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

መሰረታዊ የኮምፕዩተር ዕውቀት፤ ኦፐሬቲንግ ሲስተምና ሶፍትዌር፡፡

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sun, 01/12/2014 - 19:02
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic

Operating System ወይም ግብረተ ሲስትም፡፡ መጀመሪያው ክፍል ላይ ባጭሩ እንደቀረበው ግብረተ ሲስተም የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ Windows ዊንዶውስ፣ Mac ማክ፣ Linux ሊነክስ የመሳሰሉት ግብረተ ስይስተም ናቸው፡፡ ግብረተ ሲስተሙ ስራውን የሚጀምረው ገና ኮምፕዩተሩ እንደተለኮሰ ነው፡፡ ለምሳሌ ኮምፕዩተር ሲቀሰቀስ የሚያቃስተውና ጊዜ የሚወስድበት መጀመሪያ የኮምፕዩተር አካል ወይም ሃርድዌርና ሶስፍትዌሮች ወይም የትእዛዞች ጥርቅም መስማማታቸውንና መስራታቸውን ግብረተ ሲስተሙ ማወቅና መቆጣጠር ስላለበት ነው፡፡ ከቁጥጥር በኋላ አንገብጋቢ ስህተት ከተገኙ ኮምፕዩተሩ መልእክት ያሳያል፡፡ ወይም ይቆማል፡፡ ኮምፕዩተሩ ከጀመረ በኋላም ግብረተ ሃይሉ ይህንንኑ ተግባር ይቀጥላል፡፡ ያለ ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሃርድዌርና ሶፍትዌር ብቻቸውን ምንም አያደርጉም፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa AmharicSoftware የትእዛዞች ጥርቅም ነው፡፡ ሶፍትዌር ማለት ባጭሩ የትእዛዞች ጥርቅም ማለት ነው፡፡ እነዚህም ሶፍትዌሮች ለምሳሌ ሰነድ መጻፊያወች፣ ኢንተርኔት መቅዘፊያ (Mozila Firefox, Google Chrome, Internet Explorer, Opera ሌሎችም)፣ ጨዋታወች፣ ስእል መሳሊያወች፣ ፎቶና ቪዴወ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ የማይክሮሶፍት ኦፊስ ወርድ ለተለያዩ ሰነዶች መጻፊያ፣ ኤክሰል ማጥለያ ለሚያስፈልጋቸው የተለያዩ ሰነዶች ማዘጋጃ፣ ፓወርፖይንት ደግሞ የስራ ውጤትን ለምሳሌ ስብሰባ ላይ ማሳያ ያገለግላል፡፡ ምሳሌውን ጠቀስኩ እንጂ ሶስቱም እንደተጠቃሚው ችሎታና የስራው አይነት ብዙ አይነት ስራወችን ያከናውናሉ፡፡ ሌሎቹም ተመሳሳይ ስራ የሚሰሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ ለምሳሌ LibreOffice የነጻ ሆኖ ግን ልክ እንደ ኦፊስ አይነተ አገልግሎት አለው፡፡ ብዙ ኢትዮጵያውያን ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ኦፊስን አደናግረው ይናገራሉ፡፡ ራምና ካዝናን አደባልቀው ይናገራሉ፡፡ ጥያቄ ሲጠይቁም ለምሳሌ ልክ ቤት ከገዙ/ከተከራዩ በኋላ እቤት ውስጥ ገብተው ወንበሩ ለመቀመጫ መሆኑን ስተውት ደውለው የሚጠይቁም አሉ፡፡ ነገሩ አስቂኝ ነው ግን ይደርሳል፡፡ ነገሩን ለመጥቀስ ብየ ነው እንጂ ለመፎገር አይደለም፡፡ የነዚህ ልዩነት ሁለተኛው ጽሁፍ ላይ ቀርቧል፡፡

ላይ እንደተጠቀሰው ሶፍትዌሮች ብዙ ናቸውና አንድ ተጠቃሚ የሚያስፈልጉትን መምረጥና መጠቀም ይችላል፡፡ ከላይ የኢንተርኔት መቅዘፊያወች የተለያዩ እንደሆኑ ሁሉ ሌሎችም ፕሮግራሞች አይነታቸው ብዙ ነው፡፡ ሶስፍትዌር የትእዛዝ ጥርቅም ስለሆነ ለምሳሌ አንዱ የፎቶ መስሪያ ሶፍትዌር ብቻ ላይ እንደ አይነቱና ትልቅነቱ ቢለያይም በመቶና በሺ የሚቆጠሩ ትእዛዞች አሉት፡፡ ለምሳሌ ፎቶው ላይ የተለያዩ ቀለሞችንና መጠን ለመቀየር፣ ለማሳመር፣ ለማበላሸት፣ ለመደረብ፣ ለመደባለቅ፣ ቅርጽ ለመቀያየር ወዘተ የሚያስችለው የፎቶው ሶፍትዌር ሰሪ እነዚህን የትእዛዝ ጥርቅሞች ስላስገባበት ነው፡፡ እንደሚታወቀው የነጻም ሆነ የሚሸጡ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ ጥራታቸው ይለያያል፡፡ ብዙውን ጊዜ የሚገዙት የተሻሉ ቢሆኑም የነጻም ሆነው ከሚሸጡት በላይ የሚሻሉ አሉ፡፡ እንደተጠቃሚው ችሎታ፣ ፍላጎትና ቅምሻ ይለያያል፡፡ ባሁኑ ጊዜ የነጻ ሶፍትዌሮች ብዙ ስለሆኑ መግዛት የማይፈልጉ ተጠቃሚወች ጥቂት አይደሉም፡፡ በተረፈ ይህ ጽሁፍ እንደረዳ ተስፋ አለኝ፡፡

Comments

መሐመድ ሰኢድ's picture

ስለ ሴልስ ሲስተም ማወቅ
ፈልጋለው እውቀቱን ለቸረሕ በአብ ስም እጠይቀሐለው
ከስራዬ ጋር ስለተያያዘ ነው::

ሰላም!
'' ሴልስ ሲስተም'' ሰፊ አባባል ነው። ስለ የትኛው ሴልስ ሲስተም ማወቅ ፈልገው ነው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት ተገቢ መልስ ለመስጠት ይመቻል። //ፋተ

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ