
ቀናቶች ተቆጥረው ወርን ይሰፍራሉ፣
ወሮችም ተቆጥረው ዓመት ይሞላሉ፣
እንዲሁም ዓመቶች ዘመን ይለያሉ።
የሚገርም እኮ ነው እንዲህ በድንገት፣
ይቺ ጊዜ እሚሏት አላት ብልሃት፣
ይዛ ትመጣለች አዲሱን ዓመት፣
ከተፍ በማለት ሰው ሳይነቃባት።
እራሴን ስጠይቅ በዚህ አዲስ ዓመት፣
ቁጥር ጨመረና ምንድነው የኔ እድገት?
አዲስ ዓመት ቢሆን ልክ እንደ መስታዎት፣
ምን አንዳደረኩኝ ልኩን የማይበት፣
እያልኩ ጠየኩት እራሴ በድንገት፣
መቼ ይሆን እኔ ለውጦች የማይበት።
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 7208 reads
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ