You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የማይጠይቅና የማይንቀሳቀስ ጥቅም ላይ ያልዋለ አቧራ የሚሰበስብ እቃ ብቻ ነው!

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 03/13/2015 - 19:51
tatariw ethiopia amharic addis ababa passions

ጠየቅ የማናውቀውን እንድናውቅና የማንችለውን እንድንችል ያደርጋል። መጠየቅ የጎደለውን እንድንሞላና የተጣመመውን እንድናስተካክል መንገድ ይከፍታል። መጠየቅ ያላየነውን እንድናይና ያልሰማነውን እንድንሰማ ያደርጋል። መጠየቅ እውቀታችን እንዲጨምርና ችሎታችን እንዲሰፋ ያደርጋል። መጠየቅ ሰው መብቱን እንዲያውቅና ተንቀሳቅሶ እርምጃ እንዲወስድ ያገፋፋል፡፡

በተቃራኒው ደግሞ፤ የማይጠይቅ የተጣመመ አያስተካክልም። የማይጠይቅ የጎደለ አይሞላም። የማይጠይቅ አያይም። የማይጠይቅ አይሰማም። የማይጠይቅ እውቀቱ አይጨምርም። የማይጠይቅ ችሎታው ከፍ አይልም። የማይጠይቅ አያድግም። የማይጠይቅ ነጻ አይደለም ወይም መሆን አይችልም። የማይጠይቅ አምናም ሆነ ዘንድሮ፤ ትላንትም ሆነ ዛሬ ያው ነው። ለውጥ የለውም፡፡

ከላይ ያልኩትን ላብራር።

ጭሩና ዋናው ነጥቡ የጠየቀ ያገኛል፤ ያልጠየቀ ግን አያገኝም ነው። የጠየቁትን ለማግኘት ሁለት ነገሮች ወሳኝ ናቸው። አንደኛው አስቦ ማድረግ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ አስቦ መጠየቅ ናቸው። አስቦ ማድረግ የምንፈልገውን ነገር ለማግኘት የምናሳየው እንቅስቃሴ ነው። ለምሳሌ ተንቀሳቅሰን እጆቻችን እንዲሰሩ የምናደርግበት ሁኔታ ሊሆን ይችላል። አስቦ መጠየቅ ደግሞ አይኖቻችንን ገልጠን መሻሻል ያለበት ማንኛውም ነገር ላይ ልብ ስንልና አስተያየት ሲኖረን ነው። መጠየቅ ሰው ሃሳቡን መሰረት በማድረግ እራሱን ይጠይቃል። በተመሳሳይ ደግሞ ተናግሮና በአፉ ቃላት አውጥቶ ይጠይቃል። አስቦ መጠየቅ፤ ካየነውና ከሰማናው በመነሳት ከውስጣችን የሚመነጨው ሃሳብ ነው። ይህ ለምሳሌ የዚህ ህንጻ አሰራር ጥሩ ነው ወይስ አይደለም የሚል ሊሆን ይችላል። እስካሁን ድረስ በማሽን ሳይሆን በበሬ መሬት እንደት ይታረሳል ሊሆን ይችላል። እኔ ነጻ ነኝ ወይስ አይደለሁም ብለው እራስዎን የሚጠይቁት ጥያቄ ሊሆን ይችላል። በቃላት ተናግረን የምጠይቃቸው ጥያቄወች ደግሞ እንደሚታወቀው ተናግረን ሌላ ሶስተኛ አካል ስንጠይቅ ነው። ለምሳሌ የሆነ ነገር እንዴት እንደሚሰራ በራሳችን ካልቻልን ሰው ጠይቀን መፍትሄ የምንሻበት መንገድ ነው።

ባጠቃላይ ሁሉም ነገር ከሃሳብ ይፈልቃል። ከዛም ያሰብነውንና የተመኘነውን ነገር ለማግኘት መጠየቅ የግድ ነው። ካልጠየቅንና ዝም ካልን ለማግኘትና ለማወቅ የተመኘነውን ሁሉ እናጣለን። ሌላ ስውም ሊነጥቀን ይችላል፡፡ የማይጠይቅ በሃሳቡም ሆነ በአካሉ አይንቀሳቀስም። እንደ ሁኔታው ቢለያይም ሰው ሲጠይቅ ያስባል፣ ይናገራል ወይም በአካል ተንቀሳቅሶ እርምጃ ይወስዳል።

ማይንቀሳቀስ ሰው ልክ አንድ ቦታ ላይ ቁጭ ብሎ አቧራ የሚሰበስብ እቃ ጋር ይመሳሰላል። ሰውን እቃ ነው ማለቴ ሳይሆን ሁኔታው መመሳሰሉን ለማሳየት ነው፡፡ አንድ ቦታ ላይ የቆየ እቃ ጥቅም ላይ ስለማይውል የሚሰበስበው አቧራ ብቻ ነው ለማለት ነው። አቧራውን እፍ ሲሉት እቃው ልክ እንደዱሮው ነው። አቧራውም የውሸት ሽፋን ስለሆነ በቀላሉ እፍ ሲሉት አየር ላይ ይበተናል። የዚህ ጽሁፍ ዋናው አላማ ከላይ በምሳሌ እንደተጠቀሰው በሃሳቡም ሆነ በአካሉ የማይጠይቅ አምናም ሆነ ዘንድሮ ለውጥ አያመጣም ለማለት ነው። ሰው እንደዚህ መሆኑን እንደት ያውቀዋል? መልሱ በጣም ቀላል ነው። ለምሳሌ ተምሮም ሆነ ሳይማር ቋንቋ ከቀላቀለ፤ በቀጠሮ ለፈረንጅ ሲሆን በሰአቱ የሚደርስ ለኢትዮጵያዊ ሲሆን ግን የሚዘገይ፤ ቀለም ትምህርት ቢወስድም ሁለገብ ያልሆነና አይቶ የማይጠይቅ። ምሳሌው ብዙ ነው። ሰው ይህን ሊያውቅ የሚችለው ግን እራሱን መጠየቅ ሲችል ነው።

Comments

አያሌው ዋሲሁን's picture

በጣም ገንቢ ትምህርት ነው እውነት ነው እምልህ የኔን ችግር ነው የነገርከኝ በዝምታ ብዙ ነገር ያልፈኛል ግን ካሁን በኋላ ተምሪያለሁ ከንተም ትምህርት ብቻ ሳይሆን ሁኔታወችም አስተምረውኛል

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ