You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የሚዛናዊ መሪ ሃላፊነትና ሚና ከችሎታውና ትህትናው ጋር፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Mon, 10/03/2011 - 19:35

ሚዛናዊ መሪ ሃላፊነትና ሚና ሰፊ ሆኖ ችሎታና ትህትናን ማጣመር ሲችል ነው፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡ የተለያዩ ሁኔታወችና ቦታዎች ላይ መሪዎች እንዳሉ የታወቀ ነው፡፡ ለምሳሌ የቤተሰብ፣ የክለብ፣ የሃይማኖት፣ የድርጅት፣ የተለያዩ ተቋማት፣ የሃገር ወዘተ መሪ ሊሆን ይችላል፡፡ መሪ መሆን ማለት ደግሞ ወሳኝ የሆነ ቁልፍ ቦታ ላይ ሃላፊነት መውሰድ ማለት ነው፡፡ ይህንን ሃላፊነት ለመወጣት ታዲያ መሪ ሚዛናዊ መሆን አለበት፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡ ሚዛናዊ ስል አንድ መሪ ከበቂ ችሎታ ባሻገር ጥሩ ራዕይና ትህትና ያለው ሆኖ ከሰዎች ጋር አብሮ ለመስራትና ህዝብ ለማገልገል ዝግጁ መሆን ሲችል ነው፡፡

ሰዎች ጋር አብሮ መስራት ስል ሰዎች ችሎታቸውን ለሃገር ወይም ለተቋሙ እንዲጠቀሙበት ማመቻቸት መቻል ማለቴ ነው፡፡ በተለይ በተለይ ያለ እራዕይና ትህትና ሚዛናዊ መሪ መሆን ያስቸግራል፡፡ ምክንያቱም አንድ መሪ ራእይ ሲኖረው ጎበዝ ስለሆነ ሰዎች ደህንነት ስለሚሰማቸው ያምኑታል፡፡ ትህትና ሲያሳይ ደግሞ በተከታዮቹ ወይም በህዝብ ይከበራል፡፡ ይወደዳል፡፡

ራእይ ማለቴ ለምሳሌ መሪው ችሎታና ጥበብ ስላለው ለሚመራው ተቋም፣ ህዝብ ወይም ሃገር ምን አይነት ጠቃሚ ነገር እንደሚያስፈልግ ስልሚያስብና ስለሚያውቅ እቅድ ያወጣል፤ አዲስ ሃሳብም ያመነጫል፡፡ የስራ አጋሮቹንም አዲስ ሃሳብ እንዳላቸው ይጠይቃል፡፡ እንግዲህ ጥበብ ተጠቅሞ ራእይ ያለው መሪ ስል የማሻሻል አላማ ኖሮት ጥሩ አቅጣጫም የሚያሳይ ነው ለማለት ይሆናል፡፡

ትህትና ማለቴ ደግሞ ለምሳሌ መሪው የሚመራውን ተቋም ወይም ሃገር በቅን አስተሳሰብ ለማገልገልና ለመስራት ዝግጁ ሲሆን ነው፡፡ ለምሳሌ ህግ፣ ህዝብ፣ አገር፣ ወግና ባህል የሚያከብር ሲሆን ነው፡፡ የማይዋሽ ለማለት ነው፡፡ አቀራረቡ በስነስርአትና በአክብሮት የተላበሰ በሚሆን ጊዜ ደግሞ ሰወች መሪን ሁለገባዊ መሆኑን ስለሚረዱ ይወዱታል፡፡ ያከብሩታል፡፡ እንደማስበው ባጭሩ የሚዛናዊ መሪ ጥበብና ሚና ይህንን ይመስላል፡፡

ተለያዩ አጋጣሚዎች እንደሰማሁት ብዙ ሰዎች መሪ መሆን ማለት ትእዛዝ ማስተላለፍ ብቻ ይመስላቸዋል፡፡ ይህ አባባል ሙሉ በሙሉ እውነት አይደለም፡፡ ሰወች መሪ ትእዛዝ ሰጪ ነው ብለው በሚያስቡ ጊዜ በውድም ሆነ በግድ ትእዛዝ ተቀባይ ብቻ ይሆናሉ፡፡ እንደዚህ የሚያስቡ ሰወች በራሳቸው ስለማይተማመኑ እራሱን የቻለ የራሳቸው አስተሳሰብና ሚዛናዊ እውቀት አንሷቸው ሊሆን ይችላል፡፡ በተለያዩ ምክንያቶችና ጥቅሞች ወይም በእውቀት ማነስ ምክንያት ትእዛዝ ፈጻሚዎች ወይም ተቀባዮች ብቻ ይሆናሉ፡፡

ለምሳሌ ማንኛችንም እድሜአችን ከ75 አመት በታች የሆን ኢትዮጵያውያን እስካሁን ድረስ ነጻ ሆነን የኖርንበት ጊዜ ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም እስካሁን ድረስ ራእይ፣ ጥበብና ትህትና ያለው መሪ ኖሮን አያውቅም፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው በቃ በማለት ፋንታ መጥፎ መሪዎችን እንዲቆዩ ስለምንፈቅድላቸው ነው፡፡ አንዳንዶቻችን ነጻ ለመሆን ሁልጊዜ እንታገላለን፡፡ አንዳንዶች ለመጥፎ ነገር ተገዢና ታዛዥ ሆነው ሌላው እንዲበደል ተባባሪዎች ይሆናሉ፡፡ አንዳንዶች ደግሞ እንደማያገባቸው ዝም ይላሉ፡፡ ዞሮ ዞሮ ግን ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ገና ነጻ አልሆንም፡፡ ለእውነተኛ ነጻነት የሚታገለው ክፍል ለራሱ ብቻ ሳይሆን ሁሉም ኢትዮጵያዊ ነጻ ሆኖ ኢትዮጵያ ውስጥ እኩልነት እንዲሰፍን ነው ብዬ አምናለሁ፡፡
ስለዚህ ነጻነትን የምናገኘው ተገዢና ታዛዥ ሆነን ወይም ዝም ብለን ሳይሆን ሁላችንም ለሁላችን ስንተሳሰብና ኢትዮጵያ የእኩልነትና የነጻነት ሃገር እንዲትሆን አብረን ስንታገል ነው፡፡

ነጻነትን የምናገኘው ተገዢና ታዛዥ ሆነን ወይም ዝም ብለን ሳይሆን ሁላችንም ለሁላችን ስንተሳሰብና ኢትዮጵያ የእኩልነትና የነጻነት ሃገር እንዲትሆን አብረን ስንታገል ነው፡፡ የዚህ ጽሁፍ አላማ ለመጥፎ ነገር ተገዢና ታዛዥ ከመሆን ወይም ዝም ከማለት ይልቅ ለነጻነት መታገል ይበልጣል ለማለት ነው፡፡
አስተያየትዎን ከታች ለማስፈር አይርሱ!!

Comments

I think this is what we Ethiopians must internalize and work hard to put it in practice. we are still far away from working together to realize our common objective or dream of seeing a free Ethiopia

Thank you brother Fantaw

ድንቅ ትምህርት

ውድ ፋንታው በውነቱ ብዙ ትምህርት ነው የተማርኩት፡፡እያንዳንዱ ዜጋ ማንበብ ቢወድ ሁሉም ራሱን በዚህ ጽሁፍ ውስጥ ይመለከት ነበር፡፡ለማንኛውም አመልካች ወንድም አይጥፋ፡፡ብዙ ነገሮችን ነቅሰሕ አሳይትኽናል..አንብቦ የመማርና የመረዳት ሥራ የኛው ነው፡፡ እግዜር ይስጥልኝ፡፡አክባሪህ እንግዳ

ወቅታዊ ነው

ፋንታው ያቀረብከው ጽሁፍ ጥሩና ትምህርት የሚሰጥና ወቅታዊ ነው.በርታ

ሚሊዮን

Qualities needed by capable and promising leaders.

Dear Fantaw,

The qualities your commentary describes are indispensable for capable and promising leaders. Unfortunately dictators like the ethnofacist Meles Zenawi can not have these qualities. Continue to raise and discuss such points and issues because many can benefit from them and shape their actions and behavoour accordingly.

ለሚገባው ጥሩ ፅሁፍ ነው፡፡

መሪዎች በማንኛውም መመዘኛ ቢያንስ በፅሁፍህ ውስጥ የተጠቀሱትን መመዘኛዎች እራሳቸውን ቢጠይቁና መልስ ቢሰጡ ከእራሳቸው ግል ሰሜት(egoism)ይላቀቃሉ ብዬ አምናለሁ፡፡ዛሬ ለውጪ አልጋ ለቤት ቀጋ ሆነው የተፈጠሩ እስከሚመስለን ድረስ የምናያቸው መሪዎች በማሰቢያ አንጎላቸው ውስጥ የጠቀስካቸውን መስፈርቶችን በቀለም ቀቢ ካልሆነ በስተቀር በምናባቸው ኮርኩረው ቦታ ሊያገኙለት አልታደሉም፡፡እንዳልከው በቃ የሚል አካል እስካሌለ ድረስ የሕሊናቸውንና ነፃነታቸውን መሪ የሚዘወረው በአለቆቻቸው ቀስት ይሆናል፡፡ከራእይና ከትህትና በላይ ግን መሪ ለአንድ ሕዝብ፤ቡድን፤ሐገር ወይም ስብስብ ለአንድነትና ለታማኝነት ተገዢ ከሆነ በሂደቶች ውስጥ የጠቀስካቸውን መስፈርቶች ሳይወድ በግድ እንዲያሟላ ያደርጉታል የሚል ግምት አለኝ፤ለምን ቢባል ለሕግ የበላይነት ይገዛል ማለት ነው፡፡ውድ ወንድም ፋንታው ርዕሱ በጥልቀት የሚመረመር ነው የባለሙያዎችን ድጋፍ ይሻል ለጠቋሚ መሰረታዊ ሀሳብ ሳላደንቅህ አላልፍም፡፡በርታ

ዳዊት መኮንን (NORWAY)

ስሪታችን ላይ ጥርጥር ገባኝ!'s picture

ስሪታችን ላይ ጥርጥር ገባኝ!

አንድ ወንድሜ እንዲህ አለ።"እኛ የተሰራንበት ቅመማው ስህተት አለው"

ለምሳሌ አሁን አንተ የፃፍከውን እውነት መሪዎች አያውቁትም?መልካም ስራ ሰርቶ ማለፍ ኩራት እንደሆነ የማይረዳ አለ?መልካም ነገሮችን እናውቃለን።መልካም ነገር ለማድረግ ግን አንፈልግም።ለምን?በፅሁፉ ላይ የተነሱት ጉዳዮች በሙሉ ሊተገበሩ የሚችሉ ቀላል ጉዳዮች ናቸው።ግን ሳይሳካልን ትውልድ አልፎ ትውልድ ተተካ።የወደፊቱም ትውልድ ይህንኑ ጠማማ ሂደት ከመረከብ ውጭ ሌላ አማራጭ የለውም።ላቀረብከው ፅሁፍ ምስጋናዬ ከፍ ያለ ነው።

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ