You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ወዳጅና ጓደኛዎ ማነው? መስጠትና መቀበል ነው። ክፍል አንድ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 02/27/2015 - 13:07

ዳጅ በተለያየ መንገድ ሊተረጎም ይችላል። ዋናው መንፈሱ ግን ወዳጅ ማለት የልብን ለመንገር የሚታመን ሰው ሲሆን ነው። ክፉም ሆነ ደግ ሲደርስ አብሮ ተካፋይ ወይም ከጎን የሚቆም ሰው ሲሆን ነው። ወዳጅነት ከልጅነት ጀመሮ የቆየ ሊሆን ይችላል። ከብዙ አመታት ትውውቅና መተሳሰብ የመጣ ሊሆን ይችላል። አጋጣሚ የፈጠረው ወዳጅነት ሊሆን ይችላል። በጋራ ጉዳይና ፍላጎት ላይ የተመሰረተ ሊሆን ይችላል። ወዳጅ ለማፍራት ምክንያቱና አጋጣሚው ብዙ ነው። ከስራ ቦታ፣ ከት/ቤት ወዘተ ሊጀምር ይችላል። ሆኖም ግን የልብ ወዳጅ ለማፍራት ቀላል አይደለም።

ወዳጅነት አብሮ በመብላትና በመጠጣት በቀጥታ አይገኝም። ይህንማ ሁሉም ያደርገዋል። ብዙ ሰው አብሮ ይበላል። ብዙ ሰው አብሮ ይጸልያል። ብዙ ሰው አብሮ ይሰራል። ብዙ ሰው አብሮ ት/ቤት ውስጥ ይማራል። ብዙ ሰው ጎረቤት አለው። ሁሉም ሰው ለሁሉም ሰው ወዳጅ ይሆናል ማለቴ ሳይሆን፤ ሰውና ሰው የሚገናኝበት መንገድ ብዙ መሆኑን ለመጥቀስ ነው።

ንደሚመስለኝ ወዳጅነት የመስጠትና የመቀበል ጉዳይ ነው። በተለይ ከማግኘትና ከመጠበቅ ይልቅ አብዣኛው ሰው መስጠት ላይ ቢያተኩር ሁኔታውን ያቀለዋል። ሳይሰጡ ማግኘት ያስቸግራል። መስጠት ስል ደግሞ ቁሳቁስ ወይም ገንዘብ ማለቴ አይደለም። ቁሳቁስና ገንዘብ ሰውን አይገዛውም። ወዳጅም አያፈራም። ፍቅርም አያመጣም። መስጠት ስል ለምሳሌ ክብር ከመጠበቅ ይልቅ መጀመሪያ ሌላውን ሰው ማክበር ሊሆን ይችላል። ፈገግታ ከመጠበቅ ይልቅ እራስን ፈገግ ማድረግ ሊሆን ይችላል። ሰላምታ ከመጠበቅ ይልቅ መጀመሪያ እራስ ፈገግ ብሎ ሰውን ሰላም ማለት ሊሆን ይችላል። በቃል መገኘት ሊሆን ይችላል። ለወዳጅ ተብሎ ጊዜ መጠቀም ሊሆን ይችላል። ወዳጅን መጠየቅ፣ ማሰብና መውደድን ማሳየት ሊሆን ይችላል። ሁኔታው ላይ ሌላ የተለየ ኮተት የሌለበት ካልሆነ በስተቀር አንድ ሰው ሲወዱት፣ ሲያስቡለትና ሲጠይቁት ዋጋ የማይሰጥበት ምክንያት የለም።

ንዳንድ ሰወች በተደጋጋሚ ሲያስቡላቸውና ሲጠይቋቸው ብዙም አይጥማቸውም። ሰው ጥቅም የፈለገ ሊመስላቸው ይችላል። ይጠራጠራሉ። ተቀብለው ጸጥ ይላሉ። እንደዚህ አይነት ምልክት ከታየ ችክ ማለት አያስፈልግም። መተውና ህይወትን መቀጠል ይሻላል። በወዳጅነት መካከል ቅሬታ ሊፈጥሩ ከሚችሉ ነገሮች ውስጥ አንዳንዶቹ መጠራጠር፣ አፍራሽ ነገር ማሰብና ጥቃቅን ነገሮችን መከታተል ናቸው። እነዚህን ሁኔታወች እንደት ማሻሻል እንደሚቻል ሁለተኛው ክፍል ላይ አቀርባለሁ።
ባጠቃላይ ወዳጅነት በመስጠትና በመቀበል የሚገኝ ስለሆነ በራስዎ የሚፈጥሩት ነው።

ታታሪው ዶት ኔት ላይ መጥተው ስላነበቡ አመሰግናለሁ!! አስተያየት ወይም መልእክት ካለወት ይላኩ።

Comments

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ