
አርዕስቱ ላይ ስፖርትና እንቅስቃሴ የጠቀስኩበት ምክንያት ሁሉም ሰው ስፖርት መስራት ስለማይችል ነው። ይህም በእድሜ ምክንያት፣ ጊዜ በማጣት ምክንያት፣ ወይም በሌላ እክል ምክንያት ስፖርት ላይሰሩ ይችላሉ። ሆኖም ግን በስፖርት ፋንታ የተለያዩ እንቅስቃሴወች ማድረግ እንደሚችሉ ለመግለጽ ነው። የዚህ ጽሁፍ ዋናው አላማ ግን ስፖርት ወይም እንቅስቃሴ ከትክክለኛ አመጋገብ ጋር ለጤንነት አስተዋጾ ማድረጉን በምችለው መንገድ ለማሳየት ነው። ሁሉም ሰው ስፖርት አይሰራም። ሁሉም ሰው ጠፍጣፋ ሆድ የለውም። አንዳንድ ቀላል እንቅስቃሴዎችን እያደረጉ ቁጥጥር ማድረግ ግን ሌላ ነው።
ስፖርትና እንቅስቃሴ፤
እዚህ ጽሁፍ ላይ ስፖርት ስል ለውድድር የሚደረግ ስፖርት ሳይሆን ጤንነትን በሚመለከት የሚሰራ ስፖርት ነው። ለምሳሌ ተከታታይና መለስተኛ ሩጫ፣ እግር ኳስ፣ ክብዴት ማንሳት ወዘተ ሊሆን ይችላል። ይህንን የሚያደርጉ ከሆነ ምናልባት አመጋገብ ላይ ካልሆነ በስተቀር ብዙም የምለው የለኝም።
ስፖርት የማይሰሩ ከሆነ ግን በቀላሉና በየአጋጣሚው ደስ እያለዎት የሚያደርጓቸው ብዙ ነገሮች አሉ። ችግር የለም። የምነግረወት ጥሩ ዜና አለኝ! ልዩ የሆነ ችግር ካልሆነ በስተቀር አንድ ቦታ ላይ ቁጭ ብለው አይውሉም። ወደ ስራ ይሄዳሉ። ወደ ጉብኝት ይሄዳሉ። ወደ ት/ቤት ይሄዳሉ። ወደ ቤ/ክርስቲያን ወይም ወደ መስጊድ ይሄዳሉ። በኛ አባባል "ወክ እንብላ" ይባላል እና ለምሳሌ ብቻዎን ወይም ከጓደኛዎ ጋር ለዘገማ ይወጣሉ። በሌሎችም አጋጣሚ በእግርዎ ይሄዳሉ። በህይወት ውስጥ የሚያንቀሳቅሱን ምክንያቶች ብዙ ናቸው። ዘፈን ላይ "እንቅስቃሴወች ሁሉ ዳንስ ናቸው" እንደተባለው ሁሉ "እንቅስቃሴወች ሁሉ ስፖርት ናቸው"።
ግን ..... ሲንቀሳቀሱ ትልቅ ግን አለበት። ሲንቀሳቀሱ እንደት ነው የሚንቀሳቀሱት? እኔ እንደታዘብኩት በጣም በሚያስገርም ሁኔታ አብዣኛው ኢትዮጵያዊ የሚንቀሳቀሰው ወይም የሚሄደው ቀስስስስስስስስስ ብሎ እየተሳበ ነው። ከላይ የጠቀስኳቸውን እንቅስቃሴወች ለማድረግና ውጤት ለማየት ከፈለጉ በየአጋጣሚው ሁሉ ላጥ፣ ላጥ ፣ ላጥ ፣ ላጥ፣ እያሉ መሄድ ያስፈልጋል። በደንብ እየገሰገሱ ማለቴ ነው። በእጅዎ የሆነ ነገር ካልያዙ ደግሞ እጆችዎን እያወዛወዙ መገስገስ እንቅስቃሴውን ሙሉ ያደርገዋል። እጅ ኪስ ውስጥ መግባት የለበትም። በዚህ ሁኔታ ላይ እንዳሉ ለምሳሌ አንድ ሰው ከኋላዎ እየገሰገሰ ከቀደመዎት ደራ ሊይዘዎት ያስፈልጋል። በጣም የገነነ መገስገስ ካልሆነ በስተቀር በመገስገስ መቅደም መቻል አለብዎት። ይህን የሚያደርጉት ለውድድር ሳይሆን ሰውነትዎን፣ አቅምዎንና፣ ፍላጎትዎን ለማዳበርና እራስዎን ለማለማመድ ነው። የአቅምዎን ድንበር መፈታተን አለብዎት። ይህን እንደ ጥሩ አመል ካዳበሩትና ከደጋገሙት በየቀኑ የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ስለሆነ ለጤንነት ትልቅ አስተዋጾ አለው። ጊዜም ይቆጥባሉ። ለምሳሌ ልጅ ጋር ከሆኑ ወይም መገስገስ የሚከለክል ሁኔታ ላይ ካሉ ሚዛን አድርጎ መያዝ ነው። ስፖርት ካልሰራሁኝ ውጤት አላመጣም ብለው የሚያስቡ ሰወች ሊኖሩ ይችላሉ። አሁን ግን በቀላሉ በእንቅስቃሴ ለውጥ ማምጣት እንደሚቻል እንደተረዱት ተስፋ አለኝ!! ስንት ካሎሪን ማቃጠል እችላለሁ የሚለው ሂሳብ ውስጥ አልገባሁም። ይህን ከፈለጉ በራስዎ ፈልገው ማወቅ ይችላሉ። እኔ በበኩሌ ምክንያታዊ ሆኘ እንደሚመቸኝ አደርጋለሁ እንጂ ስለ ካሎሪን አስቤበት አላውቅም። ማስታወቂያውና ንግዱ የጦፈ ስለሆነ ያደናግራል።
ምግብና መጠጥ፤
አመጋገብና ምግብ ከስፖርትና እንቅስቃሴ ይበልጣል። ጠበብተኞችም ይህን ይላሉ። በዚህ አባባል መስማማት አይቸግረኝም። እኔ እንደሚመስለኝ ለምሳሌ በቀን ሶስት ጊዜ አካባቢ ስለምንበላና ቁጥሩ የማይታወቅ መጠጥም ስለምንጠጣ ሰውነታችን ውስጥ ያለጥርጥር አስተዋጾ ይኖረዋል። እንደሚባለው ለጤንነትና ለውጤት ምግብ 80% አካባቢ፤ ስፖርት ወይም እንቅስቃሴ ደግሞ 20% አካባቢ ይሸፍናል። በተለይ ምግብ በበዛበት ሃገር ውስጥ ሰወች የትኛውን ምግብ እንብላ በማለት ይጨነቃሉ። የዚህን አይነት ምግብ ይብሉ ብሎ ለሌላ ሰው መንገር አስቸጋሪ ነው። ሰው በራሱ እንደምርጫውና እንደሚስማማው ቢበላ ይሻላል ይመስለኛል። ግን አንድ እውነት አለ። ሰው የሚስማማውንና የማይስማማውን ምግብ ማወቅ መቻል አለበት። በተጨማሪም ሰው ከመብላቱ በፊት ምግቡ ምን አይነት እንደሆነ በማየት ማወቅ ይችላል። ከበላ በኋላ ደግሞ የሚሰማው ስሜት ይነግረዋል። ንቁ መሆንና መታዘብ መቻል ብቻ ነው። ለምሳሌ ምግብ በልተው ሆድዎ ከተጨነቀ ወይም ድካም ከተሰማዎት በአንድ ጊዜ ብዙ ምግብ ወይም ቅባት የበዛበት ምግብ በልተው ሊሆን ይችላል። ሌላም ምክንያት ሊሆን ይችላል። ምግቡ ቶሎ ካልተፈጨና እየጨነቀዎት ከቆዩ ያ ምግብ አይስማማወትም ማለት ነው። የዚህ አይነት ምግብ ላይ ለሁለተኛው ጊዜ መጠንቀቅ አለብዎት። ፈስ ወይም ሆድዎ ውስጥ ንፋስ ካስቸገረዎት ደግሞ፤ የበሉት ምግብ በደንብ አልትፈጨም ወይም በደንብ አኝከው አልዋጡትም ሊሆን ይችላል። ሰውነታችን የሚነግረን መልዕክት አለ። በቀላሉ ሆድን ጎንበስ ብሎ በቆረጣ አይቶ ሆዳችን ያለወትሮው ከተወጠረ በምግቡ ምክንያት የሆነ ችግር አለ ማለት ነው።
ከምግብ በኋላ መልዕክቱን ካዳመጥነው፣ ስሜቱን ልብ ካልነውና ሆዳችንን ጎንበስ ብለን በቆረጣ ካየነው ለሁለተኛው ጊዜ የምንበላውን የምግብ አይነት ማስተካከል እንችላለን። ስንጸዳዳ እንቢ ካለንና ከደረቀ ደግሞ የተለየ ችግር ከሌለ በስተቀር በቂ ውኋ አልጠጣንም ይሆናል። ከላይ እንደተጠቀሰው እንቅስቃሴ አሳንሰን ይሆናል። ፋይበር ያነሰው ምግብ ብቻ ተመግበን ይሆናል። ሌላም ምክንያት ሊኖር ቢችልም እነዚህ ሶስቱ ግን ዋናዎቹ ናቸው። መጠጥን በተመለከተ ውኋ ማዘውተር ተፈጥሯዊ ነው። ምክንያቱም ውኋ በዝናም መልክ ከሰማይ ይወርዳል። ከመሬት ይመነጫል!! ውኋ ጥሩ መሆኑን ለማወቅ የዚህን ያህል ቀላል ነው።
ስፖርት ለመስራት ወይም እንቅስቃሴ ለማድረግና የሚስማማ ምግብ አይነት ለመምረጥ ውስብስብ አይደለም።
ታታሪው ዶት ኔት ላይ ገብተው ስላነበቡ አመሰግናለሁ። አስተያየት ካለወት ከታች ይስጡ!!
main category:
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 18422 reads
Comments
it's cool thanks
it's cool thanks
Thanks, I am happy you like
Thanks, I am happy you like it Helen. //Fantaw
በጣም እናመሰግናለን
በጣም እናመሰግናለን
I lik the way you teach and
I lik the way you teach and it is true movement is very important to have Good theath and life will be smoth
Thank you
አመሰግናለሁ! ልክ ነው። ቀላል እንቅስቃሴወች
አመሰግናለሁ! ልክ ነው። ቀላል እንቅስቃሴወች ለውጥ ማምጣት ይችላሉ። //ፋተ
Kjære Fantaw!!
Kjære Fantaw!!
Tusen Takk for en lærerik og viktig tema.Mann kan lære masse på en enkelt møte fra den artikkelen.
stå på!
Mvh
HM
Tusen takk Hawa! Håper at
Tusen takk Hawa! Håper at flere kan ta tipset med seg. Takk for gode ord. //FT
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ