You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ኮምፕዩተርወ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ክፍል ሁለት፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተሞችና ማንነታቸው።

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Tue, 04/22/2014 - 23:09
Ethiopia wake up addis ababa amharic ethiopia tatariw

ታወቁትና ዋና ዋና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ዊንዶውስ ማክ እና ሊኑክስ ናቸው። አሁን በአውሮፓውያን 2014 ዊኪፔድያ እንደሚለው ዊንዶውስ በቁጥር ከፍተኛና 87% ተጠቃሚወች አሉት። ማክ 7,5% ተጠቃሚወች አሉት። ሊኑክስ ደግሞ 1.5 አካባቢ ተጠቃሚወች አሉት። ኦፕሬቲንግ ሲስተም ማለት ምን እንደሆነ ከዚህ በፊት ኦፕሬቲንግ ሲስተም ላይ ከዚህ በፊት በቀላሉ አስረድቻለሁ።

ዊንዶውስ፤

የአንድ ኦፕሬቲንግ ሲስተም (ኦሲ) ተጠቃሚወች በበዙ ቁጥር ያ ኦሲ ለጥቃትና ለስለላ የተጋለጠ ነው። ይህ ማለት ዊንዶውስ ለመጠቃት ብዙ ቀዳዳ ስላለው በተደጋጋሚ ይጠቃል። በተለይ ተጠቃሚው ቀላልና ተገቢ ጥንቃቄውችን ካላደረገ (ያጠቃቀም ባህሪ) አላስፈላጊ ብላሽ ፕሮግራሞች ስለሚሰፍሩ ዊንዶውስ ለቫይረስ የተጋለጠ ነው። ለዚህም ነው አንቲቫይረስ እየተባለ ተጠቃሚው ተጨማሪ ሶፍትዌር እንዲገዛ የሚደረገው። ዊንዶውስ የተሰራውም በአንድ ዝግና ሞኖፖል ባለው ድርጅት ስለሆነ ጥቂት በማይባሉ ተጠቃሚወች አይወደድም። በተጨማሪም ዊንዶውስ ስራወችን ኮምፕዩተሩ ላይ ለማከናወን ከጊዜ ወደ ጊዜ ቀርፋፋ መሆኑ የተለመደ ነው። ማይክሮሶፍት ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ቢያመርትም ሃርድዌሩንና ሌሎች ተጨማሪ ፕሮግራሞች ግን በሌላ ድርጂት የተመረቱ ናቸው። በዚህም ምክንያት እንኩአን ዊንዶውስ ለጥቃት የተጋለጠ ነው።

ማክ፤

ክ አፐል የሚባል ድርጂት የሚሰራው ነው። አፕል ኮምፕዩተሩን ኦፕሬቲንግ ሲስተሙንና ተጨማሪ ፕሮግራሞችንም በራሱ ዘይቤ ይሰራል። በዚህም ምክንያት ሲስተሙ ከዊንዶውስ የበለጠ ዝግና ሞኖፖል ስላለው በቫይረስ ወይም በስለላ የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ነው። ብዙ ግራፊክስ የሚሰሩና የዜና አውታሮች ይጠቀሙበታል። ማክ እኔ ተጠቅሜ አላውቅም ግን ማክ አስተቸገርኝ የሚሉ አሉ። ስራውን ግን ማክ ይሰራል። ዋጋው ደግሞ በታም ውድ በመሆኑ ይታወቃል።

ሊኑክስ፤

ኑክስ ባጭሩ ኮዱ ክፍት (ኦፐንሶርስ) ስለሆነ በአለም ውስጥ ባሉ ስማርት ህብረተሰቦች የሚሰራ ነው። ለመጠቀም ነጻም ነው። ሰሪው ህብረተሰቡ ገቢ የሚያገኘው በልገሳና በስፖንሰሮች ነው። ሊኑክስን ማጥቃት በጣም አስቸጋሪ ነው። ምክንያቱም ሊኑክስ በህብረተሰብ ስለሚሰራና ስለሚዳብር ሊኑክስ ላይ የመጠቃት ጥርጥራ ከታየ ወዲያውኑ ስለሚነቃ ቶሎ ብሎ ህብረተሰቡ መፍትሄ ያገኛል። ችግሩ ይታረማል። ቀዳዳው ትደፈናል። በግለሰቦች ደረጃ እንጂ ለምሳሌ ትልልቅ ካምፓኒወች፣ ድረጅቶች፣ ባንኮች፣ መንግስቶች ወዘተ ሰርቨራቸው ላይ ሊኑክስን በሰፊው ይጠቀማሉ። ምክንያቱም ሊኑክስን መጠቀም ደህንነቱ ብቻ ሳይሆን ፍጥነት አለው። እንደ ዊንዶውስ በቀላሉ ክራሽም አያደርግ። እነዚህ የጠቀስኳቸው ሊኑክስን የሚጠቀሙ ድርጅቶች ሰርቨራቸው 24 ሰአት ሙሉ ያለማቋረጥ መስራት ስላለበት ሊኑክስ ከዊንዶውስ የበለጠ አስተማማኝ ነው። ታዲያ እንዘህ ድርጅቶች ከሊኑክስ ህብረተሰብ ካምፓኒ ጋር ቴክኒካዊ ኮንትራት አላቸው። ታዲያ ሊኑክስ ከልገሳና ከስፖንሰር በተጨማሪ ሌላም ገቢ አለው ማለት ነው።

ስካሁን ድረስ ብዙ ሰወች ሊኑክስ የተሰራው ለሰርቨር እንጂ እንደ ዊንዶውስ በግል ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ብለው ይገምታሉ። ይህ አባባል ለምሳሌ ከ10 አመታት በፊት ቢሆን ኖሮ በከፊል ትክክል ነው። አሁን ግን በተለይ ካለፉት 5 አመታት ጀምሮ ሊኑክስን በግል ለመጠቀም እንዳውም ከዊንዶውስ ይቀላል። ሊኑክስ ባለቤት የለውም ብለው እርዳታ ሲፈልጉ ቶሎ እርዳታ የማያገኙ ስለሚመስላቸው ሊኑክስን ለመጠቀም የሚፈሩ ሰወች አሉ። ነገር ግን ለዊንዶውስ ተከፍሎ እንኳን የማይደርስበት የሊኑክስ ህብረተሰብ ቶሎ ምላሽ ይሰጣል። ከላይ ከጠቀስኩት ጥቅሞች በተጨማሪ ደግሞ የሚያስፈልጉትም ሶፍትዌሮች በሙሉ አንድ ቦታ ላይ ስላሉ አያስቸግርም። ሃርድዌሮቹን የሚያጣጥሙት ሶፍትዌሮችን እንኳን ለማግኘት እንደ ዊንዶውስ ከሌላ ቦታ ፈልጎ ማምጣት አያስፈልግም። ሁሉም ነገር ተጣጥሞ ኮምፕዩተሩ ላይ ይሰፍራል። በአማርኛ ወይም በሌላ ቋንቋ እዛው በቀላሉ መጻፍ ይቻላል።

አስር አመት በፊት አካባቢ ጀምሮ እኔ በዊንዶውስና በሊኑክስ መካከል እያፈራረቅሁ እጠቀም ነበር። ያው አሁንም ቢሆን ዊንዶውስና ሊኑክስ ሁለቱም እራሱን የቻለ ጥንካሬና ድክመት አላቸው። አሁን ግን ሊኑክስ በጣም ተሻሽሏል። እኔ ሊኑክስን አሁን ደስ ብሎኝ በቋሚነት እጠቀማለሁ። በተጨማሪ ደግሞ ውብ ነው። ከውስጥም ሆነ ከውጭ ቆንጆ እንደሆነች ሴት ፍቅር ያስያዛል። እውነቴን ነው። አንድ ኮምፕዩተር ላይ ሊኑክስን ለመሞከር የግድ ኮምፒውተሩ ላይ በቀጥታ ማስፈር አያስፈልግም። በሲዲ/ዲቪዲ/ዩኤስቪ ቀድቶ ካዛ ላይ መሞከርና መንዳት ይቻላል። ሊኑክስን እዛው ተመሳሳይ ኮምፕዩተር ላይ ከዊንዶውስ ጎን ወይም ላዩ ላይ ጭኖ መሞከር ይቻላል። ሊኑክስ የዚህን ያህል ቀላልና ሁለገባዊ ነው።
ትንሽ ስለ ዩቡንቱ ሊኑክስ ማወቅ ከፈለጉ Ubuntu Desktop ላይ አለ። ዩቡንቱም ሆነ ሌሎች ሊኑክሶሽ የተለያየ ዝርያ ስላለቸው ሰው እንደ ቅምሻው ምርጫው ብዙ ነው። የሊኑክስ አይነቶችን ደግሞ distrowatch ላይ ማየት ይቻላል።

አሁን የሶስቱንም ዋና ዋና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ሁለተኛው ክፍል ላይ አይተናል። የትኛው እንደሚሻልም ትንሽ ምልከት የሰታል። ሶስተኛው ክፍል ላይ ደግሞ ስለ ደህንነትና የዊንዶውስ አጠቃቀም አቀርባለሁ። ባሁኑ ወቅት ያው አብዛኛው ህዝብ የሚጠቀመው ዊንዶውስን ስለሆነ የሚቀጥለው ክፍል ዊንዶውስ ላይ እናተኩራለን።

Comments

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ