You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

አዲሱን ስራ ካገኙ በኋላ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎች፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sat, 12/29/2012 - 19:11

ዚህ በፊት የሚወዱትንና የሚያልሙትን ስራ ለማግኘት እንዴት እንደሚቻል መመሪያና ስልቱን አቅርቤ ነበር፡፡ አሁን ደግሞ ስራውን ካገኙ በኋላ ባዲሱ ስራዎ እንዲደሰቱና የስራ ማህበራዊ ኑሮውም እንዲስማማዎት ጠቃሚ መመሪያወች ይቀርባሉ፡፡
መጀመሪያ ስለ ስራ አፈላለግ ስልቱ ማንበብ ከፈለጉ እዚህ ላይ ያገኙታል፡፡ እንደጠቀመ ወይም ስራን ፈልጎ ለማግኘት ድጋፍ እንደሚሰጥ ተስፋ አለኝ፡፡ አሁን ደግሞ የፈለጉትን ስራ ካገኙ በኋላ ስራ ቦታ ላይ የሚያጋጥመወትን የተጻፉትንም ሆነ ያልተጻፉትን ህጎች አብረን እናያለን፡፡ በቀላሉ አባባል ያገኙትን ስራ እንዴት ጠብቀው ማቆየት እንደሚችሉ ለማብራራት ነው፡፡ የስራ አፈላለግ ስልቱ ላይ እንደተጠቀሰው ሁሉ ይህም እንደ ሃገሩና የስራው አይነት ትንሽ ለየት ሊል ይችላል፡፡

ዲስ ስራ መጀመር ለማንም ቢሆን ደስ ቢልም ስለመስሪያ ቤቱና ባህል፣ ስለሰራተኞቹ፣ በተለይ የርስዎ አቀራረብ ለሌሎች ምን እንደሚመስል በትክክል የሚታወቅ ነገር የለም፡፡ ሆኖም ግን የመጀመሪያ ቀን ላይ ከርስዎ በፊት የነበሩትን ሰራተኞች ሊተዋወቁ ይችላሉ፡፡ የስራ ድርሻዎ ጋር በቅርብ ሊተዋወቁ ይችላሉ፡፡ በሚቀጥሉት ቀኖች ውስጥ የተወሰነ ልምምድ ስለሚሰጥዎት እቅዱን ሊያውቁት ይችላሉ፡፡ ሌላም ሌላም እንደዚሁ፡፡ ልምምድ በሚሰጥዎት ጊዜ አንዳንድ የሚያውቋቸው ነገሮች ቢጠቀሱም የግድ ልምምድ ከሚሰጥዎት ሰው ጣልቃ መግባትና ማወቅዎን ማሳየት አሁን ጊዜው አይደለም፡፡ ወደፊትም ቢሆን በስራና ጥንቃቄ በተሞላበት አካሄድ ነው፡፡ አሁን ግን አዲስ ስለሆኑና ልምምድ እየተሰጠዎት ስለሆነ ማስታዋሻዎች መያዝ ይጠቅማል፡፡ ወደፊት የረሱት ነግር ቢኖር እንኳን ሰው ከመጠየቅ ማስታወሻዎን ማየት ይችላሉ፡፡ ለነገሩ ነው እንጂ እንኳን ልምምድ ላይ ቀርቶ ከእለት እለት ስራ ላይ እንኳን ማስታወሻ መያዝ በጣም ይጠቅማል፡፡ ልምምዱ ስለ ስራው ሙያ ብቻ ሳይሆን ስለመስሪያ ቤቱም የበለጠ እንዲያውቁ ስለሚያደርግ ተግተው መከታተል አለብወት፡፡

እየሰነበቱም ሲመጡ ስለስራውም ሆነ ስለመስሪያ ቤቱ የበለጠ ስለሚያውቁ የርስዎ አቀራረብም ምን መምሰል እንደሚችል ለማወቅ ይረዳወታል፡፡ ዋናው ነግር ግን ሁል ጊዜ በስራወም ላይ ሆነ ባቀራረብዎ መሻሻል እንደሚችሉ ማወቅና ይህንንም ሃሳብዎ ውስጥ እንዲቆይ በማድረግ ለመሻሻል መሞከር ነው፡፡ የስራ ድርሻ ላይ ለምሳሌ የሆነ ነገር ሰርተው ለማሳወቅ ወይም ተጠይቀው ለመንገር ወይም ለማስረዳት እድሉ ሲያጋጥምዎት አላስፈላጊ እኔ የሚለው ቃል እንዳይገባ ወይም እንዳይበዛ ልብ ማለት ጥሩ ነው፡፡ ለምሳሌ አሁን ጨርሻለሁ ከማለት ይልቅ አሁን ዝግጁ ነው ወይም አሁን አልቋል ማለት ብቻ በራሱ የበለጠ ተቀባይነት አለው፡፡ የስራ ባልደረቦችዎም ዋጋ ይሰጡታል፡፡ አንዳንድ ሰወች እኔ ማለት ስለሚያበዙ ባጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ሰው ስለነሱ ስሜት የለውም፡፡

አንዳንድ ሰወች እኔ ማለት ስለሚያበዙ ባጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ሰው ስለነሱ ስሜት የለውም፡፡

የሰሩትን ስራ ወይም ያገኙት ግኝት እኔ ስለሉ የርዎ ልፋት መሆኑን እኔ ማለት ሙሉ በሙሉ ማረጋገጫ አይደለም፡፡ አስፈላጊ በሚሆን ጊዜና ከፈለጉ ደግሞ አባባሉን አሳምረው ማድረግ ይችላሉ፡፡ አባባሉና አቀራረቡ እንጂ ማንኛውም ነገር ተቀባይነት አለው የሚለውን አባባል በደንብ ካሰቡበትና ካመኑበት፡፡

ላው ደግሞ ስራዎን ዋጋ መስጠት አለብዎት፡፡ መስሪያ ቤቱም ውስጥ ባለቤትነት እንዲሰማወት ያስፈልጋል፡፡ በተለይ ስራዎን ከወደዱት ዋጋም ይሰጡታል፤ ባለቤትነትም ይሰማወታል፡፡ እንደዛ ካልተሰማዎት ደግሞ የሆነ ምክንያት ስለሚኖር ቀስ ብለው አስበው ምክንያቱ ምን እንዲሆነ በመፈለግ በራስዎ መፍትሄ ማግኘት መሻት ነው፡፡ ለምሳሌ የስራ ጭነት ከሆነ አስፈላጊውን መጀመሪያ ማስቀደም ሊሆን ይችላል፡፡ ስራው ትንሽ ከበድ ብሎ ከሆነ በትርፍ ጊዜወና ከስራ መልስ በራስዎ የሚረዳ ነግር ማጥናትና ማድረግ ሊሆን ይችላል፡፡ ተጨማሪ እውቀት ማግኘት ከፈለጉ መስሪያ ቤትዎን አስፈቅደው ኮርሶችን መውሰድ ሊሆን ይችላል፡፡ ከሌሎች ሰራተኞች ጋር ማህበራዊ ኑሮው ያነሰ ነው ብለው ከገመቱ የራስዎን አቀራረብ ማስተካከል ይሻላል እንጆ ሌሎች ላይ መፍረድ ሁልጊዜ ትክክል አይደለም፡፡ ማህበራዊውን ነገር ጤናማ ለማድረግ ከላይ እንደተጠቀሰው እኔ የምትለዋን ካላበዙ፣ ፈገግ ካሉ፣ ሰላም ሲሉ አቀርቅረውና እያነበነቡ ሳይሆን የጠራ፣ የጎላና ዜማ ካለው፣ ፊትዎ ዘና ካለና፣ ስራዎ ላይ የበለጠ ካተኮሩ የማህበራዊ ኑሮውን በቀላሉ ማሻሻል ይችላሉ፡፡ ለማንኛውም ከላይ የተጠቀሱትን በሙሉ ልብና በገንቢ መልኩ ካደረጓቸው ብዙ ነገሮችን ያቀላሉ፡፡ ያ ካልሆነ ግን ምንም ዋስትና ባይኖረውም ከመደበርና ኮተት ከማብዛት ይልቅ ምናልባት ሌላ ስራ መፈለግና ማግኘት ይሻላል ይመስለኛል፡፡

ራው ላይ እየቆዩ በሚሄዱ ጊዜ የበለጠ ስለሚያውቁ አዲስ ሃላፊነት ለመውሰድ ድፍረት ማዳበር አለብዎት፡፡ መቼም ለእድገት አንደኛው አጋጣሚ አዲስ ሃላፊነት መውሰድ ነው፡፡ አዲስ ስራ ሲጀምሩም ሆነ፣ ስራው ላይ እያሉ ወይም አዲስ ሃለፊነት ወስደው እንዳለ ከመስሪያ ቤቱ ውጭ ኮርሶች መውሰድ የተለመደ ነው፡፡ በዚሁ አጋጣሚ መጥቀስ የምፈልገው በስራ ምክንያትም ሆነ በማህበራዊ ኑሮ ውስጥ ለመጀመሪያ ጊዜ ወይም ሰንብቶ ሰወችን ሰላም ለማለት በሚጨብጡ ጊዜ ተነስቶ ሰላም ማለትን የሚመሰለ ነገር የለም፡፡ እንደዚህ አይነት ቦታና አጋጣሚ ላይ ይቺ የኢትዮጵያ አሪፍ ባህል ግጥም አድርጋ ትሰራለች፡፡ እንዳውም ሌሎችም ዜጎች ይከተሉዎታል፡፡ እኔ እንደዛ አጋጥሞኛል፡፡ ማለት የፈለኩት የትም ሃገር ይኑሩ፤ ለመጀመሪያ ጊዜና አስፈላጊ ወቅት ላይ አንዳንድ ልዩ የኢትዮጵያ ባህሎች ድንቅ ስለሆኑ ይጠቀሙበት ለማለት ነው፡፡

ማለት የፈለኩት የትም ሃገር ይኑሩ፤ ለመጀመሪያ ጊዜና አስፈላጊ ወቅት ላይ አንዳንድ ልዩ የኢትዮጵያ ባህሎች ድንቅ ስለሆኑ ይጠቀሙበት ለማለት ነው፡፡

አንዱ ሌላው ቀላሉ ነገር ደግሞ በልደት፣ አመት በአል፣ ስጦታ ወዘተ ፈርሙ ሲባል በአማርኛ ወይም በሚችሉት ሌላ ቋንቋ ፈርመው በቅንፍ ውስጥ ቢተረጉሙት ማንነትዎን ያሳያል፡፡

በተረፈ ይቅናዎት!!!

Comments

ጥሩ ነው ።አሁን እኔ የመኪና የሞተር ዘይት እና ቅባቶች መሸጫ ልከፍት አስቤ ነበር ስለዚህ ስራ አሰራር እና አዋጭነት ምንአይነት ቦታ ላይ ቢከፈት ኬት ማስመጣት እንዳለብኝ እና ምን ያህል አዋጭ እንደሆነ ብታብራራልኝ

ኢት ኢስ ጉድ.
ልክ እንደ መፅሀፍ እድሳት በአዲስ ፅሁፍ እንደሚቀርብ እጠብቃለሁ።

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ