You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የአፍ ንጽህና አጠባበቅና አያያዝ መመሪያ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Mon, 01/28/2013 - 19:16

መጀመሪያ ማንም ሰው ቢሆን በተከታታይ ሁልጊዜ የትንፋሹ ሽታ ምን ምን እንደሚል ዋስትና የለውም፡፡ ዋናው ነገር ግን በተቻለ መጠን አንድ ሰው ቀላል የሆኑ ጥንቃቄወችን ካደርገና ከደጋገመ ትንፋሹ ጥሩ እንዲሸት ያግዙታል፡፡ ትንፋሽ ሊያሸቱ የሚችሉ ሁኔታወች ከታወቁና ጥንቃቄ ከተደረገባቸው ትንፋሽ የመሽተቱ እድል ይጠፋል ወይም በጣም ይቀንሳል፡፡ የጥርስ ሃኪምዎ እንኳን ጊዜ ተጠቅሞ እንደዚህ ላያብራራ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እኔ ሃኪም ባልሆንም የምችለውንና የሞከርኩትን ባካፍል ምንም አይደለም፡፡

የሚከተሉት ዋና ዋና ምክንያቶች ትንፋሽ ያሸታሉ፡፡

አስፈላጊ ወቅት ላይ ለምሳሌ ጧትና ማታ ከመተኛት በፊት አፍና ጥርስ በደንብ ካልጸዳ፡፡
ጥርስን ብቻ አጽድቶ ምላስና የጉንጭን ዙሪያ መተው፡፡
ለረጅም ሰአታት ያለ ምግብና መጠጥ ከተቆየ አፍ ሲደርቅ ሽታ መፍጠሩ አይቀርም፡፡
ቅመማ ቅማም የበዛበት ምግብ ማዘውተር፡፡
የተወሰኑ ወቅቶች ላይ በተገቢው ከመብላት ይልቅ ቅምሻና ጉርሻ ማዘውተር፡፡
ሲጋራ ማጨስና አልኮሆልና ቡና መጠጣት፡፡
ጥርስ ውስጥ ቀዳዳ ሲፈጠር፡፡
ከተቻለ ቢያንስ በአመት አንድ ጊዜ እንኳን ጥርስ ሃኪም አለመጎብኘት፡፡

ላይ የተጠቀሱትን ምክንያቶች ባጠቃላይና በዝርዝር እናያለን፡፡ ጧት ከቁርስ በኋላና ማታም ከእራት በኋላ አፍና ጥርስን ማጽዳት ለጤንነትም ሆነ ሽታን ለማስወገድ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ ማታ ላይ አፍን ካጸዱ በኋላ ምናልባት ውኃ መጠጣት ብቻ ካልሆነ በስተቀር ምግብ መብላት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ጥርስ ውስጥና ጉንጭ ዙሪያ ፍርፋሪና ጣምና ስለሚቀር ሌሊቱን ቫክተሪያ ሰርቶ ስለሚያድር ነው፡፡ አንዳንድ ሰወች ጧት ልክ ከእንቅልፍ እንደተነሱ ጥርስን መቦረሽ ወይም መሟጨት ያስፈልጋል ይሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ማታ ከእንቅልፍ በፊት አጽድተው ካደሩ ጧት ፊት ሲታጠቡ በውኃ ብቻ መጉመጥመጥና ቁርስ መብላት ይቻላል፡፡ ከቁርስ በኋላ ግን አፍን አጽድቶና ንጹህ ሆኖ መውጣት እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡

አፍና ጥርስን እዴት አድርጎ ማጽዳት ይቻላል?

ው ሁላችንም እንደምናውቀው ኮልጌት፣ ቡርሽና ውኃ ያስፈልጋል፡፡ በሃገራችን በኢትዮጵያ ደግሞ መሟጪያ የሚጠቀሙም ይኖራሉ፡፡ ያው ለመጥቀስ እንጂ አፍና ጥርስን ለማጽዳት እራሱን የቻለ ትንሽ ጥበብ ወይም ዘዴ አለው፡፡ ምክንያቱም ዘዴ የሚያስፈልገው አፍና ጥርስ ሳሙና ውስጥ ተነክሮ ሳይጸዳ የወጣ ልብስ እንዳይመስል ነው፡፡ ሳይጸዳ ግን ተነክሮ ብቻ የወጣ እንዳይሆን ለማለት ነው፡፡ አፍና ጥርስን ለማጽዳት በጎልጌቱ የጥርስን ዙሪያ መቦረሽ እንደጀመሩ አፍን አ አ አ ብሎ ምላስን ካወጡ በኋላ እዛው ቀስ ብሎ በቡርሹ ምላስን በኮልጌት መቀባት፡፡ ከዛም ጥርስን መቦረሽ መቀጠል፡፡ ለምሳሌ ለሶስት ደቂቃ አካባቢ በኤለትሪክም ሆነ በጅ ቡርሽ ከቦረሹ በኋላ አፍ ውስጥ ጎልጌቱ ከምራቅ ጋር ፈሳሽ ስለሚሰራ አፍን ገጥሞ ምላስን 360 ዲግሪ እያስሽከረከሩ የጉንጭን ግድግዳ ዙሪያ በምላስ መፈተግ ወይም መጥረግ፡፡ ይህ በሚደረግ ጊዜ አፍ መዘጋት አለበት፡፡ አንድ ደቂቃ አካባቢ ሊበቃ ይችላል፡፡ መጨረሻ ላይም ምላስን አ አ አ አ ብሎ ምላስን ጎልጉሎ በምላስ መጥረጊያ የምላስን አናት ለምሳሌ ለ30 ሰኮንዶች ማጽዳት፡፡ ምላስ መጽዳቱ የሚታወቀው የተፈጥቶ ስጋ መልኩ ከታየ ነው፡፡ የቆሸሸ ምላስ ጥቁር ወይም ቡናማ ነው፡፡ ምላስን ሲያጸዱ የግድ በጣም ወደ ውስጥ መግባት አያስፈልግም፡፡ ምክንያቱም ሊያስመልስ ስለሚችል ነው፡፡ ከዛም በንጹህና በቀዝቃዛ ውኃ ተጉመጥምጦ መጨረስ፡፡ የሁሉም ጠቅላላ ሂደት 5 ደቂቃወች አካባቢ ይወስዳል፡፡ ከጥርስ በተጨማሪ ምላስና የጉንጭ ዙሪያ የጠቀስኩት የምግብ ፍርፋሪና ጣም ምላስና ጉንጭ ላይ ስለሚቀር ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቫክተሪያ ሰርቶ ሽታ ስለሚፈጥር ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ጥርስን ብቻ ቦርሾ ምላስና የጉንጭን ዙሪያ መተው ትርጉም የለውም፡፡

ከጥርስ በተጨማሪ ምላስና የጉንጭ ዙሪያ የጠቀስኩት የምግብ ፍርፋሪና ጣም ምላስና ጉንጭ ላይ ስለሚቀር ከትንሽ ቆይታ በኋላ ቫክተሪያ ሰርቶ ሽታ ስለሚፈጥር ነው፡፡ ዞሮ ዞሮ ጥርስን ብቻ ቦርሾ ምላስና የጉንጭን ዙሪያ መተው ትርጉም የለውም፡፡

የቀን ውሎንስ እንደት ወዋል ይቻላል?

ስራ፣ በትምህርት፣ በስብሰባ ወይም በሆነ ጉዳይ ምክንያት ጉዙ ላይ ሲቆይ አፍ ስለሚደርቅ ሽታ መፍጠሩ አይቀርም፡፡ ነገር ግን ገና ጧት ከቤት ሲወጣ ንጹህ ሆኖ ካልተወጣ ከምሳም ሆነ ከጉዞ በኋላ ሽታው ይብስበታል፡፡ ከምሳ በኋላ ቡና አለመጠጣት ለአፍ ንጽህና አስተዋጾ አለው፡፡ ልክ ምሳ ከበሉ በኋላ ደግሞ ያው ኮልጌት ምናምን ስለማይኖር እዛው ከሚበላበት ቦታ ፍራፍሬ ካለ፤ በተለይ ፓም መግመጥ፣ ጥርስን በስንጥር መሰቅሰቅና ውኋ ተጎንጭቶ ምላስን 360 ዲግሪ እያስሽከረከሩ የጉንጭን የውስጥ ግድግዳ መጥረግና ከዛም ውሃውን በዛው መዋጥ ይቻላል፡፡ ከ2 - 3 ጊዜ ይህንን ከደጋገሙት ይረዳል፡፡ እዛው የሚበላበት ቦታ ላይ ማድረግ ይቻላል፡፡ መጨረሻ ላይም ውኃ ተጎንጭቶ መዋጥ ለአፍ ንጽህና በጣም ይጠቅማል፡፡ ማስቲካና ሚንት ነገር ለጊዜው እራስን ማታለያ እንጂ ምንም አይረዳም፡፡ እንዳውም ማስቲካ ስናኝክ ብዙ አየር ስለምንውጥ ሆዳችን ውስጥ አየር ያበዛል፡፡ ማስቲካና የመሳሰሉትን ግን ካስፈለገ እንኳን አፍ ውስጥ ብዙ አለማቆየት ነው፡፡ ማስቲካና ሚንትም ለጥርስ ደህንነት ጥሩ መሆናቸው ያጠራጥራል፡፡

ግብ በተወሰኑ ወቅቶች ላይ መብላትና የተጠቀሱትን ዘደወች በመጠቀም የትንፋሽ ሽታን በጣም መቀነስ ይቻላል፡፡ ሰው ለጊዜው ትንፋሼ ይሸታል ብሎ ከተጠራጠረ ወደ ሌላ ሰው በጣም አለመጠጋትና ሲተነፍሱም ለምሳሌ ባፍንጫ መተንፈስ ከትዝብት ያድናል፡፡ አብሮ ለሚኖር ሰው ምናልባት ሽታ ስለተለመደ አይታወቅም፡፡ ከቤት ሲወጣ ግን ለምሳሌ፤ ለስራ፣ ለትምህርት፣ ለስብሰባ፣ ወደ ቤተ ክርስቲያ፣ ጸድቶ መውጣት ለሽታ ብቻ ሳይሆን ለጤንነትም ጭምር በጣም አስፈላጊ ነው፡፡ አንዳንድ ሰወች በቀላሉ እራሳቸውን ማጽዳት ሲችሉ ከሰላምታቸው በፊት ሽታቸው የሚቀድም አለ፡፡ የፈለገ ወዳጅ ቢሆንም ትንፋሽህ ይሸታል ብሎ ደፍሮ የሚነግር የለም፡፡ ወዳጅ ከሆኑማ ደግሞ ላለማስቀየም ምልክት እንኳን ሳያሳዩ ችሎ መቆየት የተለመደ ነው፡፡ አንዳንድ ሰወችም ሽታ ሲያስቸግራቸው አፋቸውን በጃቸው የሚከልሉ አሉ፡፡ የሰው ልጆች ስንባል እንዲሁ ጥሎብን ሽታና ጠረን ለረጅም ጊዜ ማስታወስ እንችላለን፡፡ ታዲያ የምናውቀው ሰው አንዳንድ ጊዜ ወይም ሁል ጊዜ የሚሸት ከሆነ፤ ገና ሰላም ከመባባላችን በፊት መጀመሪያ የምናስታውሰው መጥፎውንም ሆነ ደህናውን ሽታ ነው፡፡ ስለዚህ ሰው እራሱ ባለቤቱ በቀላሉ ንጽህናውን መጠበቅና ሌላ ሰውንም አለማስቸገር ተገቢ ነው፡፡

main category:

Comments

Dear Fantaw!

You have raised here an important social problem. These days it is widespread in our society. The majority has this problem. The advices you enumerated if strictly followed can alleviate the problem but cannot get rid of it.

The following points have either not been addressed or need more clarification:

1)The source of the problem can sometimes be a chronic disease of the gums in which case the remedy could be to look for advice from a dental doctor.

2)The use of other mouth cleaning agents which help to improve the breathing from the mouth and noses.

3)The fact that chewing gums help in minimizing bad odors.

4)Is breathing via the noses free from bad odor?

5)Does drinking coffee result in a bad odor in the mouth?

With best regards

Samson Seifu

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ