You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

መሰራታዊ የኮምፕዩተር እውቀት፤ ኮምፒዩተር ምንድነው?

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Fri, 01/03/2014 - 20:15
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic

ምፒውተር ማለት በሰውም ይሁን በፕሮግራም በታዘዘው የተለያዩ ትእዛዞች መሰረት ስራ የሚያከናውን ማሽን ነው፡፡ ይህ ስራ ለምሳሌ ሰነድ ለመጻፍ፣ ሂሳብ ለማሰል፣ ኢንተርኔት ለመቅዘፍ፣ ለመጫወት፣ ለመሳል፣ ፎቶና ቪዴወ ለማዘጋጀት ወዘተ ሊሆን ይችላል፡፡ ይህንን የስራ ክንውን ለመፈጸም ኮምፕዩተር በሶስት ዋና ዋና ክፍሎች ይከፈላል፡፡ ከታች የቀረቡት ሶስቱ መሰረታዊ ክፍሎች ኮምፕዩተሩ እንደ ኮምፕዩተር እንዲሆንና ትእዛዞቹም እንዲፈጸሙ ያስችሉታል፡፡ በአይነትም ሆነ በትልቅነት የተለያዩ ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ለምሳሌ የጭን፣ የቤት፣ የመስሪያ ቤት ኮምፕዩተሮች አሉ፡፡ ከአካል መጠናቸው፣ ከፍጥነታቸውና ከአቅማቸው ልዩነት በስተቀር መሰረታዊ አሰራራቸው ይመሳሰላል፡፡

አንደኛው የውስጥ አካላዊ ክፍሎቹ ለምሳሌ Harddrive HD ካዝና፣ RAM ራም ወይም ጊዜያዊ ተሸካሚ፣ Motherboard ዋና ካርድ፣ Sound card የድምጽ ካርድ፣ Video card የቪዴወ ካርድ፣ CPU አማካይ አዛዥ ይገኙበታል፡፡ እና የውጭ አካላዊ ክፍሎቹ ደግሞ Display ማሳያ፣ Keyboard መጻፊያ፣ CD/DVD-rom የሲዲ/ዲቪዲ ቤት፣ printer ማተሚያ፣ Mouse አይጥ፣ ይገኙበታል፡፡ የሁሉም የውስጥና የውጭ አካል የጋራ ስም ደግሞ ሃርድዌር ይባላል፡፡ ይህ ሃርድዌር በአካል የሚታይና የሚነካ ነው፡፡

ለተኛው ክፍል ደግሞ አካላዊ ያልሆኑ ፕሮግራም ተብለው የሚጠሩ ናቸው፡፡ እነዚህም ለምሳሌ ሰነድ መጻፊያወች፣ ሂሳብ ማስሊያወች፣ ኢንተርኔት መቅዘፊያወች፣ ጨዋታወች፣ ስእል መሳሊያወች፣ ፎቶና ቪዴወ ማቀናበሪያወች ወዘተ የሚያገለግሉ ፕሮግራሞች ናቸው፡፡ እንደተጠቃሚው ፍላጎትና ስራ በመቶና በሺህ የሚቆጠሩ ፕሮግራሞች አሉ፡፡ የሁሉም ፕሮግራሞች አጭር የጋራ ስም software ወይም የትእዛዝ ጥርቅሞች ሊባል ይችላል፡፡ ሶፍትዌር ልክ እንደ ሃርድዌር የሚነካና የሚጨበጥ አይደለም፡፡ ሶፍትዌር ግን የባይነካና የማይጨበጥ ቢሆንም ክስተት የሚያሳይ የትእዛዝ ጥርቅም ነው፡፡ ከዚህ በተጨማሪ ደግሞ የኮምፕዩተር የእያንዳንዱ የውስጥና የምጭ አካሎች የራሳቸው ድራይቨር (አስማሚ) የሚባል ሶፍትዌር አላቸው፡፡ ለምሳሌ የድምጽ ካርዱ የድምጽ ካርድ መሆኑን ኮምፕዩተሩ ውስጥ እንዲታወቅ ለማድረግ ነው፡፡

ስተኛው ክፍል ደግሞ Operating System ግብረተ ሲስትም ይባላል፡፡ የግብረተ ሲስተሙ ዋና ዋና ሚና ካላቸው አንዱ ክፍል ነው፡፡ ብዙ ሰወች ግብረተ ሲስተሙንና ሁለተኛው ነጥብ ላይ የተጠቀሰውን ሶፍትዌር አደባልቀውና አደናግረው ይነጋራሉ፡፡ ግን በቀጥታ ትክክል አይደለም፡፡ ባጭሩ ዋናው የግብረተ ሲስተሙ ስራ ግን የኮምፕዩተር የውስጥና የውጭ አካል እና ሶፍትዌሮች በአንድ ላይ ተጣጥመው ወይም እጅና ጓንት ሆነው እንዲሰሩ የሚያስችል ነው፡፡ ለምሳሌ Windows ዊንዶውስ፣ Mac ማክ፣ Linux ሊነክስ የመሳሰሉት ግብረተ ስይስተም ናቸው፡፡

ኮምፕዩተሩ እንዲሰራ ሶስቱም ክፍሉች ማለትም አካላዊ ክፍሎቹ፣ ፕሮግራሞቹና ግብረተ ሲስተሙ በአንድ ላይ ተቀናጅተውና ተስማምተው መስራት አለባቸው፡፡ እነዚህ ሶስቱም ክፍሎች እንዴት እንደሚሰሩ ሰሞኑን በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡

Comments

ሰላም!
የኮምፕዩተር ውስንነት በሰው ፕሮግራም ተደርጎ ካልተወቀረ በስተቀር በራሱ አይሰራም።

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ