You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ማመልከቻ አጻጻፍ፣ ሂደቱና ክትትሉ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sun, 08/12/2007 - 23:05

ስራ ማመልከቻ የአመልካቹን ማንነት የሚገልጽ ነው፡፡ ስለዚህ ማመልካቻው ሲጻፍ ተገቢ ጥንቃቄና ትኩረት ያስፈልገዋል፡፡ ኮተትም ሳይበዛበት አጠር ብሎ ግልፅና ለመረዳትም ቀላል መሆን አለበት፡፡ ቀጣሪዎችም ብዙ ማመልከቻዎች ስለሚደርሷቸው እጥር ምጥን ያሉ ማመልከቻዎችን ይመርጣሉ፡፡ እንግዲህ ማመልከቻ ሲፅፉ ቀን፣ የእርስዎ ሙሉ ስምና አድራሻ ይቀድማል፡፡ ከዚያም የስራው አይነት ከነ አርእስቱ ጎላ ብሎ በአርእስት መልክ ገባ ብሎ ይሰፍራል፡፡ ወደ ዝርዝር ከመግባትዎ በፊት ስራውን በተመለከተ መቼና ከማን ጋር በስልክ ጥሩ ውይይት እንደነበረዎት ቢጠቅሱ ይታዎሳሉ፡፡ ከዚያም ይህንን ስራ ለምንና እንዴት እንደፈለጉት ባጭሩና በዝርዝር ያቀርባሉ፡፡ የትምህርት ጊዜ፣ የስራ ልምድ፣ በትርፍ ጊዜወ የሚደረጉት የተለያዩ ዝንባሌዎች፣ ወዘተ እራሱን በቻለ ገጽ ላይ እጥር ምጥን አድርጎ ማቅረብ የተለመደ ነው፡፡

ተጨማሪም አመልካቹ ባሁኑ ጊዜ ምን እንደሚያደርግና ህይወቱም ምን እንደሚመስል ቀንጨብ አድርጎ ቢያቀርብ ማመልከቻውን ሁለገብ ያደርገዋል፡፡ አመልካቹ በራሱ አስፈላጊና ጠቃሚ ናቸው ብሎ ያመነባቸውን የራሱን ሁኔታዎችና ልዮ ችሎታዎች ቢጠቅስ ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም፡፡ በመጨረሻም እርስዎን የሚያዉቁዎትንና የጠየቋቸውን የሁለት ወይም ሶስት ተጠሪ ግለሰቦች ስም ከነሙያቸው ያሰፍራሉ፡፡ ተጠሪዎቹም ድንገት ተደውሎላቸው እንዳይደናገሩ ጉዳዩን በቅድሚያ ይንገሯቸው፤ ያስታውሷቸውም፡፡ ማመልከቻውም ከተላከ ከሶስት እስከ አምስት ቀናት በኋላ ከዚህ በፊት ያነጋገሩት ሰው ዘንድ መደወል ጥሩ ነው፡፡ ስልኩንም እራሱ ሰውዬው ካነሳው/ችው በስም ሰላም እከሌ ብሎ ንግግር መጀመር ነው፡፡ ለምሳሌ በዚህ ቀን ላይ ስለዚህ ስራ ተነጋግረን ነበር፡፡ ማመልከቻ ልኬአለሁ፡፡ ስለ ማመልከቻው ምን ይመስልዎታል? ሌላ ተጨማሪ ነገር የምትፈልጉት ካለ መላክ እሽላለሁ ብሎ መጠየቅ ይጠቅማል፡፡ ማመልከቻው እስከዛሬ ድረስ ያልተነበበ ከሆነ አርስዎ ስለደወሉ ማመልከቻው ከተቀመጠበት ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊነበብ ይችላል።

ዋናው ቁም ነገር ግን አርስዎ አሁን እራስዎን እንደገና ለሁለተኛ ጊዜ አስተዋወቁ፡፡ የራስዎንም ማመልከቻ በደንብ ተከታተሉ፡፡ ከዚህ በፊት ያነጋገሩትንም ሰው በስም አስታወሱ፡፡ ይህንንም ስራ ለማግኘት ፍላጎትዎን እንደገና አሳዩ፡፡ ማመልካቻውም ከንብብሩ ላይ ተነስቶ ወይም ተመዞ አሁን ሊታይልወት ይችላል፡፡ ቀጣሪውም አርስዎን በቀላሉ ያስታውሰዎታል፡፡

ንግግሩም በሚካሄድበት ጊዜ እርስዎ እንደ ስራ ለማኝ ወይም ተስፋ ቢስ አይነት ሆነው መቅረብ የለብዎትም፡፡ ባነጋገር ሁኔታና በድምፅ ቃና በራስዎ የሚተማመኑ መሆንዎን ማሳወቅ መቻል አለብዎት፡፡ ይህ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡ ሳይጠበቁ ድንገት ለሚመጡ ጥያቄዎችና መልሶች በስልክም ቢሆን ቅሉ ዝግጁ መሆንና በተቻለ መጠን ምክንያታዊ ጥያቄ ማቅረብና መልስም መስጠት ከቀጣሪው ዘንድ ነጥብ ያሰጣል፡፡ መጨረሻም ላይም አመስግኖ ለቃለ ምልልስ እንድምጠራ ተስፋ አደርጋለሁ ሳይሆን ለቃለ ምልልስ እንደምጠራ እጠብቃለሁ ብለው በጨዋነት የስልኩን ንግግር መደምደም ነው፡፡ ዘንድሮ እኮ በጣም ፈጣጣና አይን አውጣ ሆንኩኝ ብለው አይስጉ።

ዋናው ነገር ወሬ ሳያበዙ ባጭሩ መጠየቅ፣ መልስ መስጠትና በጊዜው ውይይትዎን መጨረስ ነው። በሚቀጥሉት ቀናት ወይም ሳምንታት ውስጥ ለቃለ ምልልስ ካልተጠሩ ከላይ በተጠቀሰው መልኩ ሌላ ስራ ለማግኘት ስራ ማደንወን መቀጠል ነው፡፡ ለቃለ ምልልስ ከተጠሩ ደግሞ እሰየው ነው፡፡ አንድ እርምጃ ወደፊት፡፡

ለማስታወስ ያህል እስካሁን ድረስ የሚከተሉትን ነጥቦች በዝርዝር አይተናል፤

1. ለስራ ፍለጋ ቅድሚያ ዝግጅት፣
2. ክፍት የስራ ቦታዎች ምን ላይና እንዴት እንደሚወጡ፣
3. ማመልካቻ ከመጻፉ በፊት ስለሚደርጉ ቅድመ ዝግጂቶችና፣
4. የማመልከቻ አጻጻፍና ክትትሉን አይተናል፡፡

አሁን ደግሞ ለቃለ-ምልልስ ከተጠሩ ስራውን ለማግኘት ምን መደረግ እንዳለበት በሚቀጥለው ክፍል ላይ በዝርዝር እናያለን፡፡

Comments

ሰላም ተስፋሁን!
በጣም ጥሩ ጥያቄ ነው። የት እንደምትኖር ስለማላውቅ ምሳሌ ማቅረብ ያስቸግራል። ሆኖም ግን ጊዜ ሲኖርህ ጉግለ ላይ ከበረበርክ ብዙ ምሳሌወች ታገኛለህ። ብዙ ነገር ቢመሳሰልም እንደ ሃገሩም ይለያያል። እኔ ያቀረብኩት የስራ አፈላለግ መሰረተ ሃሳብ መመሪያ ነው። መልካም እድል!!!

ብርቱካን አዳነ's picture

እኔ ብርቱካን እባላለሁ ያለሁት ሳውድ አርቢያ ነው ግን ኢትዩ ተመልሽ። በንግድ ስራ መሰማራት ፈልጌ ነበር ግን እንደት እንደምሰራ እያሰብኩ ነው። እና ምን መስራት እችላለሁ እርዳታችሁን እፈልጋለሁ ያገሬ ልጆች

ሰላም ብርቱካን!
እኔ ውጭ ስለምኖር አሁን ኢትዮጵያ ውስጥ ምን አይነት ንግድ ስራ እንደሚያዋጣ አላውቅም። ምናልባት አንቺ እድሉ ካለሽ ሃገርቤት ካሉ ዘመዶችሽ ወይም የልብ ጓደኛ ጋር ብትመካከሪ ጥሩ ይመስለኛል። ከቻልሽም ወደ ሃገር ቤት ሄደሽ ሁኔታውችንና ሊያዋጣ መስሎ የሚታየውን ንግድ አይነት ብታጣሪ ጥሩ ይመስለኛል። መጨረሻ ላይ ደግሞ የሚያዋጣ አይነት መስሎ ቢታይም የምትወጂው ወይም ወደፊት ልትወጅው የምትችይ ንግድ አይነት ቢሆን ቆንጆ ይመስለኛል። መልካም እድል ብርቱካን!! //ፋተ

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ