You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ሰው እንደሚያስበው ይሆናል! ክፍል አንድ፡፡

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Mon, 12/30/2013 - 09:21
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic

ህይወት ስኬታማ መሆን፣ ደስታ፣ ጤናማ ማህበራዊ ህይወት፣ ጭንቀት፣ ጥርጣሬና ጥላቻ፣ መጥፎም ይሁን መልካም ድርጊት መነሻው ከአስተሳሰብ ነው፡፡ ለዚህም ነው ሰው እንደሚያስበው ይሆናል የሚባለው፡፡ ይህንን አባባል ብዙወቻችን ሰምተነዋል፡፡ ነገር ግን አስተሳሰብ በህይወታችን ውስጥ የቱን ያህል ተግባራዊ ቅርጽ እንደሚያወጣ ትንሽ ብገልጸው አይከፋም፡፡

ለምሳሌ አንድ ሰው ዘወትር ገንቢ የሆኑ ሃሳቦች በሃሳቡ ከመጡለት ለራሱም ሆነ ለሌሎች መልካም ያስባል፡፡ መልካም ያደርጋል፡፡ ዘወትር ገንቢ የሆነ ነገር የሚያስብ ግለሰብ ህይወቱ በደስታና በጤና የተሞላ ነው፡፡ በተቃራኒው ደግሞ ዘወትር አፍራሽ የሆኑ ሃሳቦች ላይ ካተኮረ ራሱንም ሆነ ሌሎችን አይጠቅምም፡፡ እራሱንም ሆነ ሌሎችን ሊጎዳ ይችላል፡፡ ለምሳሌ ከጎጅና አፍራሽ ሃሳቦች ውስጥ ፍርሃት፣ ጭንቀት፣ ጥላቻ፣ እራስን ዝቅ አድርጎ ማየት፣ ያለ ምክንያት ሰወችን መጠራጠር፣ ነገሮች ላይ ጹጉር መሰንጠቅና ሌላ ትርጉም መስጠት፣ አልችልም ማለት፣ ስህተትን እንደ ትምህርት ሳይሆን እንደ ውድቀት መቁጠር፣ ስንፍና፣ ሂስ የሚሰጥን እንደ ጠላት ማየትና አትንኩኝ ማለት ይገኙበታል፡፡ ዘወትር አፍራሽ ነገር የሚያስቡ ሰወች ህይወታቸው በአፍራሽ አስተሳሰብ የተሞላ ነው፡፡ አፍራሽ ሃሳባቸው የሚያመጣውን ውጤት አይረዱትም፡፡ የሃሳብ ሃይልን አያውቁትም፡፡

ገንቢ ሃሳቦች ውስጥ ደግሞ ድፍረት፣ ጠቃሚ ለመሆን እልህ፣ በራስ መተማመን፣ ሰውን ከመጠራጠር ይልቅ ምክንያቱን ማወቅ፣ ዋናውን ነጥብ ሳይስቱ ማስረዳት፣ ለመቻል/ለማድረግ የሚያስፈልገውን ሁሉ ማድረግ፣ ጉብዝና፣ ከስህተት መማር፣ ሂስን እንደ ትምህርት መቁጠር ይገኙበታል፡፡ ገንቢ ሃሳብ የሚያስቡ ሰወች ግን ማንኛውም ነገር መነሻው ጭንቅላታቸው በሚያመርተው ሃሳብ መሆኑን ያውቁታል፡፡ ለዚህም ልምምድ ስለሚያደርጉ ትኩረታቸውና ኑሮአቸው ገንቢ ሃሳብ ላይ መሰረት በማድረግ ነው፡፡

ሰወች ስለሆንና ጭንቅላታችንም የተለያየና ውስብስብ ስለሆነ መጥፎ አስተሳሰብን ሙሉ በሙሉ ማስወገድ አይቻልም፡፡ ነገር ግን በተቻለ መጥፎ አስተሳሰቦችን ማሳነስና ገንቢ አስተሳሰቦችን መጨመር የተሻለ ሰው ያደርገናል፡፡ ለክፉም ይሁን ለደግ አስተሳሰባችን ልክ እንዳሰብነው ያደርገናል፡፡ ምክንያቱም ክፉም ይሁን ደግ፤ ያሰብነው ነገር ወደድንም ጠላን ወደ እውነታና ውጤት ስለሚቀየር ነው፡፡ አፍራሽ ሃሳቦችን ለማስቀረት ከላይ በተጠቀሱት ገንቢ ሃሳቦች ላይ መለማመድ አንዱ መፍትሄ ነው፡፡ በተጨማሪም ገንቢ ሃሳብ ያላቸው ሰወች ጋር ጓደኝነት መግጠምና አብሮ ጊዜ ማሳለፍ ይጠቅማል፡፡ አፍራሽ ሃሳብ ያላቸው ሰወች ጋር ደጋግሞ ጊዜ ማሳለፍ አብሮ ሚንስቶ ከመሆን በስተቀር ምንም አይጠቅምም፡፡ ምክንያቱም ትንሽ አፍራሽ ነገር በፍጥነትና ሳይታሰብ እየሰፋ ስለሚሄድ ገንቢ አይደለም፡፡ ሰው ተጠቀመብኝ፣ ተጎድቻለሁ፣ ወዘተ እያሉ ሁል ጊዜ ስለ ችግሩ ከማነብነብ ችግሩን መጋፈጥና ሃላፊነት መውሰድም አንዱ መፍትሄ ነው፡፡

ገንቢ አስተሳሰብ በስሜት ሳይሆን በምክንያት ከተመሰረተ ህይወታችንን ከማቅለሉም በተጨማሪ ለህሊናም ጥሩ ምግብ ነው፡፡ አስተሳሰብ ሃይል ስላለው ሁሉም ነገር ነው፡፡

መልካም የአውሮፓውያን 2014 አዲስ አመት!!

Comments

Pages

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ