You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የሚያልሙትን ስራ አይነት ለማግኘት የስራ አፈላለግ ስልት!

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Tue, 07/10/2007 - 11:13

ስደት የምንኖር ኢትዮጵያዊያን የፈለግነውንና የተመኘነውን የስራ አይነት በሙያችን ለማግኘት የተለያዩ ፈተናወች ወይም እንቅፋቶች ያጋጥሙናል፡፡ በተለይ የመኖሪያ ፈቃድ ከሌለን ደህና የሆነ ስራ በሙያችን ለማግኘት ያስቸግራል፡፡ በዚህም ላይ ደግሞ ጸጉረ ልውጦች ስለሆንን ቀጣሪዎች ጥርጣሬ ይገባቸዋል፡፡ ቀጣሪዎች እኛን ስራ ለመስጠት ቢፈልጉም እንኳን ያገሬው ሰራተኞች አይፈልጉ ይሆናል በማለት ከመቀጠር የሚቆጠቡበትም ጊዜ አለ፡፡ ማንም ግለሰብ ቢሆን የሚፈልገውንና ያለመውን ስራ ማግኘት ይወዳል። ምክንያቱም ጥሩና ተስማሚ ሥራ ማግኘት ለደመወዝ ብቻ ሳይሆን በራሱ በስራው እርካታ ለማግኘትና እድገትም ለመጨመር ነው። ገና ከመጀመሪያው የሚፈለገውን ስራ ለማግኘት እራሱን የቻለ አካሄድና ስልት አለው። ይህ የሥራ አፈላለግ ስልት ውጭ በምንገኝ ኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ቢሆንም የትም ሃገር ቢሆን ለማንኛውም ዜጋ ሊጠቅም ይችላል።

ምናልባት በማደግ ላይ ያሉ ሃገሮች ይህንን የሥራ አሰጣጥና አፈላለግ ስልት ሙሉ በሙሉ ላይጠቀሙበት ይችላሉ። ባደጉ ሃገሮች ውስጥ ግን ስልቱ የተለመደ ነው፡፡ ስለዚህ ማንኛውም ዜጋ አገሩ ውስጥም ሆነ ሌላ ሃገር ቢኖርም፤ እዚህ ጽሁፍ ላይ የተጠቀሰውን የሥራ አፈላለግ፣ ደንብና ስርአት ቢያውቅ ጠቃሚነት አለው። እርስዎ ይህንን ስልት በተገቢው ከተጠቀሙበት ከአንድ ስራ በላይም ሊያገኙ ስልሚችሉ ስራ መምረጥ ይችላሉ፡፡ ለምሳሌ እኔ ባንድ ወቅት ላይ ሁለት ሥራዎች አግኝቼ አንዱን የተሻለውን ልመርጥ ችያለሁ፡፡ ይህም ሊሆን የቻለው ሌላ ሥራ ላይ እያለሁ ቢሆንም ሶስት ዓመታት ሙሉ የተሻለ ሥራ ፍለጋ ላይ ነበርኩ። በዚህ ጊዜ ውስጥ የተለያየ ትምህርት ወስጃለሁ፤ ስህተቶችም ሰርቻለሁ፡፡ የመጀመሪያም ሆነ የተሻለ ሥራ ለማግኘት ቋሚ የሆነ ህግና ደንብ ወይም የስራ አፈላለግ ህግ የለም፡፡ እንደ ሁኔታው ይለያያል፡፡ በግሌ የማውቀውንና የወሰድኩትን ልምድ ለሌሎች ባካፍል ግን በጣም ደስ ይለኛል፡፡

ዚህ ኢትዮጵያ ተነሺ ላይ የቀረቡት የስራ አፈላለግ ስልቶች በደንብ ተነበው በተገቢው ከተፈፀሙ አንድ ስራ ማግኘት ቀርቶ ስራ ለመምረጥም ጭምር እድል ያሰፋሉ፡፡ እነዚህ ስልቶች የተጻፉት ባንድ ንጋት ምርምር ሳይሆን በአመታት ጊዜ ውስጥ ከወሰድኩት ልምድ ነው፡፡ ውጤትም ለማግኘት ከፈለጉ በስልቶቹ መሰረት ልምምድ፣ ክትትልና ትኩረት ማድረግ አለብዎት፡፡ ስልቱን በቅደም ተከተል አንብበውና ተረድተው በተግባር ከተረጎሙት ስራ የማግኘቱ ዕድል ይሰፋልዎታል! በሦስት አመታት ጊዜ ውስጥ ከመቶ በላይ ማመልከቻዎች ልኬ ወደ በርካታ ቃለ ምልልሶች ተጠርቼ ነበር፡፡ በደንብ እየታሸሁኝና እየበሸቁኝ ስህተትም ሆነ ትምህርት ወስጃለሁ፡፡ ስለዚህ እርስዎ ስልቱን በተገቢው ካዎቁት ልክ እንደኔ ማንም ወገኛ ስራ ቀጥሪ በነገር አያሸዎትም!!!

አንዳንድ ስራ ፈላጊወች ስራ ለማግኘት መጀመሪያ አካሄዳቸውንና ስራ እደት ትንደሚገኝ ትኩረት ሰጥተው ሳያውቁ እንዲሁ በደፈናው ማመልከቻ ጽፈው ከላኩ በሗላ ስራ የሚያገኙ ይመስላቸዋል፡፡ ማድረግ ያለባቸውን ነገር ሳያደርጉ ቀርተው ስራውን ሲያጡት ደግሞ አድሎ የደረሰባቸው ይመስላቸዋል፡፡ አድሎ ቢኖርም አድሎውን በእውቀት፣ ባቀራረብና ጥሩ ባህሪ በማሳየት ሊቀይሩት መቻላቸውንም የማያውቁ አሉ፡፡ አሁን ብዙ ኮተት ሳላበዛብዎት ወደ ቁም ነገሩ እንግባ፡፡

Comments

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ