
አብዛኛው ስራ የሚገኘውም በዝምድና፣ በትውውቅና በጓደኝነት ነው፡፡ ከዛም የተረፈው የስራ ኣይነት ማስታወቂያ ላይ ይወጣል። ትውውቅና ጓደኝነትም ለመፍጠር አጋጣሚው መፈጠር አለበት፡፡ ይህንንም አጋጣሚ እራሳችን ከጊዜ ጋር ለመፍጠር ሊሳካም ላይሳካም ይችላል። በተጨማሪም ስደት ውስጥ ሆኖ ተስማሚ ስራ ለማግኘት ፈተና ከመሆኑም በተጨማሪ ውስብስብም ነው፡፡ እያንዳንዳችን ግን ስራ ለማግኘት ተጨማሪ ጥረት ማድረግ አለብን፡፡ ታዲያ ይህንን ውስብስብ የሆነ ጉዞ እንዴት እንወጣዋለን? ስራ የማግኘት እድላችንንስ እንዴት ማስፋት እንችላለን? ያገሩን ባህልና ቋንቋ ከሞላ ጎደል መቻል፣ የህዝቡን ያኗኗርና የአቀራረብ ዘይቤንም በቅጡ ማወቅ ደህና ስራ ለማግኘት ትልቅ አስተዋፅኦ አለው፡፡ ይህንን ማዎቅ ስራ ከማግኘትም ባሻገር በግል ህይወታችንና በሌሎች የማህበራዊ ጉዳዮች ላይም ጭምር በዕውቀት እንዲንዳብር ይረዳናል፡፡
በትውውቅ፣ በዝምድናና በጓደኝነት ተይዘው ያላለቁ ክፍት የስራ ቦታዎች ማስታዎቂያ ላይ ይዎጣሉ፡፡
ማስታወቂያውም ጋዜጣ፣ መጽሄት፣ ኢንተርኔት ወዘት ላይ ሊሆን ይችላል። በማስታወቂያውም ላይ ስለመስሪያ ቤቱ፣ ስለ ስራው አይነት፣ ምን አይነት የስራ ልምድ ያለው ሰራተኛ እንደሚያስፈልግ ባጭሩ መጥቀስ የተለመደ ነው፡፡ አመልካቾችም ከደወሉ ደግሞ ማንን ማናገር እንደሚቻል ከስልክ ቁጥር ጋር ይገለጻል፡፡ ይህንን አጭር የስራ ማስታወቂያ በጥንቃቄ ረጋ ብሎ ማንበብና መረዳት በጣም ይጠቅማል፡፡ ማስታወቂያውንም አንብበው ወዲያውኑ ማመልከቻ ከጻፉ ስራ የማግኘትዎ እድል በጣም የመነመነ ነው። ከዛ በፊት ግን በቅድሚያ ማድረግ ያለብዎትን ነገሮች በዝርዝር እናያለን፡፡ ምክንያቱም ማስታወቂያው ላይ በሰፈረው መረጃ ብቻ ማመልከቻ ከተላከ ስራውን ማግኘት ቀርቶ ለቃለ ምልልስ እንኳን ለመጠራት እድሉ ጠባብ ነው፡፡
አንድ የስራ ማስታወቂያ በወጣ ጊዜ በአስሮች የሚቆጠሩ ሰወች ማመልከታቸው የተለመደ ነው፡፡ አመልካቾች በበረከቱ ቁጥር ውድድሩም ይጠነክራል፡፡ ታዲያ ማስታወቂያውን አንብበው በጥሞና ከተረዱ በኋላ ወደ መስሪያ ቤቱ ደውለው የሚመለከተውን ግለሰብ ቢያናግሩ ይጠቅማል፡፡ ከመደወልዎ በፊት ዝግጅ ማድረግ አለብዎት፡፡ ሲደውሉም ስልኩ በጸሃፊ ከተነሳ ማን እንደሆኑ፣ ለምን እንደሚደውሉና ከማን ጋር መነጋገር እንደሚፈልጉ ባጭሩ ቀንጨብ አድርገው ይጠይቁ፡፡
ማስታወሻ!
አንዳንድ ስራ ቀጣሪዎች እጩ ሰራተኛ ለማግኘት ደላላ ወይም "አዕምሮ አዳኞች" የሚባሉ ጋር ግንኙነት አላቸው። የዚህ አይነት ነገር ከሆነ እዛው ማስታወቂያው ላይ ያገኙታል። ስለዚህ እርስዎ በቀጥታ ወደ ቀጣሪውም ሆነ ደላላው ዘንድ ከደወሉ የት እንደሚደውሉና ከማን ጋር እንደሚነጋገሩ ቢለያይም የስልቱ መሰረት ግን አንድ ነው።
ማነጋገር ከሚፈልጉት ግለሰብ ጋርም በተገናኙ ጊዜ፤ እንደምን ዋሉ! ስሜ እከሌ ይባላል፡፡ የምደውለው ከዚህ ቦታ ነው፡፡ የመጣሁት ከዚህ አገር ነው (እንደ ሁኔታው ቢለያይም ከየት እንደመጡ መንገር ይጠቅማል እንጂ አይጎዳም። እንዳውም በራስወ እንደሚተማመኑና ግልጽ እንደሆኑ ያሳውቃል) ያወጡትን የስራ ማስታዎቂያ አይቸዋለሁ፡፡ ስራው ይህንንና ይህንን ስለሚመስል እኔም የዚህ አይነት ልምድ ወይም ፍላጎት ስላለኝ ይስማማኛል፡፡ ማመልከቻም ለመላክ አስቤአለሁ፤ ካሉ በኋላ አንዳንድ የተዘጋጁባቸውን ጥያቄዎችን ይጠይቁ፡፡ ይህ የስልክ ንግግር በሚካሄድበት ጊዜ ረጋና ቀስ ብለው ባጭሩና ግልጽ በሆነ ሙሉ ቋንቋ ቢናገሩ ሰሚው በቀላሉ ይረዳዎታል፡፡ በመካከል ሰሚው በሚናገር ጊዜ እንዳያቋርጡት ጥንቃቄ ያድርጉ፡፡ የዚህ ንግግር አላማ ማመልከቻ ከመላክዎ በፊት እርስዎን ባጭሩ ለማስተዋወቅ ነው እንጂ ብዙ ወሬና ኮተት ማብዢያ አይደለም፡፡ ስለዚህ በተቻለ መጠን ባጭሩ ጥሩ ትዝታ ጥለውና አመስግነው ንግግሩን መጨረስ አለብወት፡፡
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 15495 reads
Comments
እውነት ነህ ወንድም
እውነት ነህ ወንድም
እሞክራለሁ። አመሰግናለሁ!! //ፋተ
እሞክራለሁ። አመሰግናለሁ!! //ፋተ
የሞባይል ቴክኒሻንነኝ ሞባይል ለመጠገን
የሞባይል ቴክኒሻንነኝ ሞባይል ለመጠገን ምንያስፈልጋል?
ለምሳሌ Google ላይ "tools to
ለምሳሌ Google ላይ "tools to repair mobile phone" ብለው ከፈለጉ የተለያዩ መቆስቆሻወች ምክርና ዝርዝር ይመጣልወታል! መልካም እድል። //ፋተ
ደስ ይላል
ደስ ይላል
ዴስ ይላል
ዴስ ይላል
በጣምተመቸኝ
በጣምተመቸኝ
በህይወቴ እመኘው የኔበረ ገፅ ይቀጥል ደስተኛ
በህይወቴ እመኘው የኔበረ ገፅ ይቀጥል ደስተኛ ነኝ።
ጣቢያውን ስለወደዱት አመሰግናለሁ! //ፋተ
ጣቢያውን ስለወደዱት አመሰግናለሁ! //ፋተ
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ