You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ቋንቋ የሃገር ዕድገትና የዜጋ ዕውቀት መለኪያ ነው!

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Thu, 07/08/2004 - 11:02

ንቋ ከጎደለ ማንነትም አብሮ ይጎድላል፡፡ ቋንቋ የተፈጠረው ለመግባባት፣ ያሰቡትንና የሚፈልጉትን ነገር በትክክል ለመግለፅ ነው፡፡ ቋንቋ የብዙ ነገር መክፈቻና መዝጊያ የሆነ ዋና ቁልፍ ነው፡፡ የቋንቋ እድገት ያገርና የዜጋን እድገት ከሚያመለክቱት ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ከዚያም አለፎ ሃሳብን ያለምንም ችግር በእናት ቋንቋ በትክክል መግለፅ እራሱን የቻለ ጥበብ ነው፡፡ እውቀትና ኩራትም ነው፡፡

የቋንቋ እድገትም ያገርና የዜጋን እድገት ከሚያመለክቱት ነገሮች አንዱ ነው፡፡ ነገር ግን እኛ ኢትዮጵያዊያን 'ላገሩ ፊደል እንግዳ ፥ ለእናቱ ቋንቋ ባዳ' እንደሚባለው እንመስላለን፡፡ ብዙወቻችን የእናታችንን ቋንቋ በትክክል እና በአግባቡ ለመጠቀም ደንታ አናደርግም፡፡ በቋንቋችን በምናወራ ጊዜ እንግሊዘኛ ወይም ሌላ የባዕድ ቋንቋ እንቀላቅልበታለን፡፡

ቋንቋ የብዙ ነገር መክፈቻና መዝጊያ የሆነ ዋና ቁልፍ ነው፡፡ ቋንቋ በተገቢውና በትክክል መጠቀም መቻል ማለት አንዱ እራሱን የቻለ የሃገር ዕድገትና የዜጋ ዕውቀት መለኪያ ነው፡፡

ይህን በምናደርግ ጊዜ የራሳችን ለሆነው ቋንቋ እንኳን በቂ ቁጥጥርና እውቀት እንደሌለን እራሳችንን እናጋልጣለን፡፡ የባዕዱንም ቢሆን በጣም ብዙወቻችን በቅጡ አንችለውም፡፡ የትኛውን ቋንቋ አጥርተን እንደምንናገር ለራሳችንም ልብ አንለውም፤ ሰሚውም የቋንቋ በቂ እውቀት እንደሌለን ያጋልጠናል፡፡

ባቶቻችን ቋንቋውን ከፈጠሩ በኋላ እንኳን፤ ቅኔውን፣ ሰምና ወርቁን፣ ግጥሙን እና ምሳሌያዊ አባባሎችን አሳልፈው ሰጥተውናል፡፡ ቋንቋችንን በአግባቡ ካልተጠቀምንበት ቋንቋው ብቻ ሳይሆን እራሳችንም ጭምር እንዳናድግ እንቅፋት ይሆንብናል፡፡ ይህንን ማስታወስና ለማንነታችንንና ለቋንቋችን ከተቆረቆርና ባግባቡ ከተጠቀምንበት ቋንቋ የማደግ ምልክትና በር ከፋች ነው፡፡ አባቶቻችን ቅኔውን፣ ሰምና ወርቁን፣ ግጥሙን እና ምሳሌያዊ አባባሎችን ፈጥረውና ተጠቅመው ለዕኛ አውርሰውናል፡፡ ታዲያ ያንን ማሻሻሉ እንኳን ቢቀር የወረስነውን ቋንቋ እንዳለ ለመጠቀም መቸገር የለበትም፡፡ ቋንቋን በትክክል አለመጠቀማችን የተለያዮ ምክንያቶች ሊኖሩን ይችላሉ፡፡ ሆኖም ግን እራሳችንን መቆጣጥርና ቀስ ብሎ አስቦ ለመናገር ሲያቅተን ካልሆነ በስተቀር ሌላ ዋና ምክንያት አለ ብዬ አላስብም፡፡ በተቻለ መጠን ምክንያቶቹን በዝርዝር፣ በቀላሉና በአማርኛ እጠቅሳለሁ፡፡
ቋንቋ፤ ፊደል ቆጥሬኣለሁ!

ይ እኔ እኮ ፊደል ቆጥሬአለሁ፣ 12 ኛን ጨርሻለሁ፣ መሃንዲስ ነኝ፣ ሃኪም ስለሆንኩ ህመምተኛ ፈውሻለሁ፣ የባዕድ ቋንቋም ስለተማርኩ እንደፈለኩ ቀላቅዬ ብናገር ምናለበት? ቋንቋ ለመግባቢያ ነው ሊሉ ይችላሉ፡፡ በርግጥ ቋንቋ ለመግባቢያ ነው፡፡ ቋንቋ እየደባለቁ መናገር ሁልጊዜና በየቦታው አያግባባም፡፡ ለምሳሌ የተለያዩ ቋንቋዎች እርስዎ ከቻሉና በአንድ ቋንቋ መናገር ሲጀምሩ በጀመሩበት ቋንቋ አጥርተው ከተናገሩ ያንን ቋንቋ መቻልዎን ያሳያሉ ለማለት ነው፡፡ ለመግባባትም ይቀላል፡፡ ያኔ ነው ቁጥጥርዎን፣ መማርዎን፣ ችሎታዎንና ማንነትዎን ማሳዎቅ የሚችሉት፡፡ ቁምነገሩም ያለው እዛ ላይ ነው!! አንዳንድ ሰዎች እራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው፤ ቀጠሮ ሲኖር በሰዓቱ ለመድረስ መጨነቅ፣ ቋንቋ ለመናገር መጨነቅ ምንድነው ይላሉ? ብዘገይም ምንም አይደለም፤ ሳወራ ቋንቋ ብደባልቅም ምንም አይደለም ይላሉ፡፡ እንዲህ አይነት ሰዎች ታዲያ እራሳቸውን ስንስርአት ለማስያዝ ጭንቀት ነው ብለው ስለሚያስቡ በሌላውም የህይዎታቸው ክፍል ውስጥ አኗኗራቸውና አሰራራቸው ድንገተኛ ነው፡፡ አቀራረባቸው፣ አሰራራቸው፣ አኗኗራቸው፣ አነጋገራቸው፣ ነጻነታቸው ወዘተ ስነስርአትና ውል የለውም፡፡
አንዳንድ ሰዎች እራሳቸውን መቆጣጠር ሲያቅታቸው፤ ቀጠሮ ሲኖር በሰዓቱ ለመድረስ መጨነቅ፣ ቋንቋ ለመናገር መጨነቅ ምንድነው ይላሉ?

ቋንቋችን ስልታዊ ነገር መናገር አይቻልም ብለው ስለሚያስቡ አመሰግናለሁ! ለማለት እንኳን በእንግሊዘኛ ይጠቀማሉ፡፡ የዘመኑ እናቶችም ልጆቻቸው 'ማዘር' ካላሉ ቅር ይላቸዋል የሚል ቀልድ ሰምቻለሁ፡፡ ያለና የነበረ ቃላትን በመጠቀም መለማመድ ካልተቻለ፣ አዲሱን ስልታዊና ሳይንሳዊ ቃል በራስ ቋንቋ ለመሰየም እንዴት ይቻላል? የመማር አንዱ ጥቅሙም ያ ነበር፡፡ ፊደል እንቁጠር እንጂ ምናልባት ከ 'ሀ' እስከ 'ፐ' እንኳን ያሉትን ፊደሎች በስርዓትና በትክክል አንጠራቸውም ይሆናል? ትምህርት ቤት ከነበርን ቆይቷል ወይም ትላንትና ነበር፡፡ ነገር ግን አሁን ሁሉም ነገር ተረስቷል፡፡ ሆኖም ግን ፊደል ስለቆጠርን ሁሉንም ነገር ያወቅን ይመስለን ይሆናል፡፡ ታዲያ አቶ አወቀና ወይዘሮ አወቀች እንድንባል የእናታችን ቋንቋ ውስጥ ሳያስፈልገን የባእድ ቋንቋ እንቀላቅልበታለን፡፡ ሌላው የሚደንቀው ነገር ደግሞ የባዕዱንም ቋንቋ ቢሆን ብዙዎቻችን በቅጡ አንችለውም፡፡ "ማወቅ መላቅ፥ አለማወቅ መናቅ" የሚባለው አባባል ሊያሳስበን ይገባል፡፡
አነስተኛም ሆነ ከፍተኛ ትምህርት ተምረን ቀላል ነገሮች ላይ እንኳን እራሳችንን ስነስርአት እንዲይዝ ካልተቆጣጠርነውና ካላዘዝነው ጠቃሚና የረቀቀ ነገር ለማድረግ ያስቸግራል።

ትንሹም ትልቁም ቋንቋን እንዳሰኘው በዘፈቀደ ከተናገረና ከቀላቀለ የራሱን ቋንቋ ያዳክማል፤ ለራሱም ለተናጋሪውም ቢሆን ቀላሉን ነገር መጠቀም ሲቸግረው ሌላው የህይዎቱም ክፍል ይከብድበታል፡፡ ለቋንቋችን ብንቆረቆር ከምንጠብቀው በላይ ይጠቅመናል፡፡ ታዲያ ይህንን ማንበብና መስማት ብቻ ሳይሆን በስነ-ልቦናችን ውስጥ አሳድረን በተግባር ከተጠቀምንበት ህይዎት ትጠቅመናለች፡፡ ምክንያቱም መሻሻልና እድገት የሚገኘው ማንኛውም ተገቢ የሆነ ነገር በተግባር ሲተረጎም ነው፡፡

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ