You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ ኔግሮ እና የኢትዮጵያ እንጀራ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sun, 08/14/2016 - 09:06
Tatariw Ethiopia Amharic website Addis Abeba

ማሳሰቢያ፤ እዚህ ጽሁፍ ላይ አፍንጫ የሚያስነፋ ጠንካራ አባባል አለ።

ይህ ጽሁፍ ከአንድ አመት ከግማሽ በፊት 12 ጥያቄና መልሶች ያቀፈ ጽሁፍ ጋር ተያያዥነት አለው። መጀመሪያ የመጀመሪያውን ጽሁፍ ካነበቡ የዚህ ገጽ ጽሁፍ ነጥብ የበለጠ ግልጽ ይሆንልወታል።

ትዮጵያ ውስጥ እርቧቸው ትምህርት ቤት ክፍል ውስጥ እንቅልፍ የሚቃጣቸው አሉ። እርቧቸው ወደ ስራ ቦታ የሚሄዱ አሉ። ምግብ ለምነው የማያገኙ አሉ። ቁርስ በልተው ምሳ የማይደግሙ አሉ። ቀኑን ሙሉ ሳይበሉ የሚውሉ አሉ። ከቆሻሻ መጣያ ቦታ ለቅመው የተበላሸ ምግብ የሚበሉ አሉ። ቤተሰብ እንዳይርበው ደፋ ቀና እያለ ሳይቆጥብ ሁሉንም የላቡን ዋጋ ለምግብ ብቻ የሚያውል ብዙ ነው። በአለም እንደሚታወቀው ደግሞ እርቧቸው የሚሞቱ አሉ። በምግብ እጦት መጎሳቀል ምክንያት አቅማቸው የደከሙ አሉ። ተመጣጣኝ ምግብ ሳያገኙ ቀርተው ጤንነታቸው ሙሉ ያልሆነ አሉ። ምግብ ለማግኘት ሲሉ ለወንጀል የሚገፋፉ ሊኖሩ ይችላሉ። በተመጣጣኝ ምግብ ማነስ ምክንያት ለማሰብና ለመስራት አቅም የሚያንሳቸው አሉ። የምግብ እጦት የሚያስከትለው ችግርና ውድቀት ብዙ ነው። በቂ ምግብ ማጣት ነጻነትንም ያሳጣል። ምክንያቱም ሰወች ለመታገል አቅም ያንሳቸዋል፤ ለምግብም ሲሉ ባሪያና ተገዢወች የሚሆኑ አይጠፉም። በዚህም ምክንያት አድሎ አለ። ጭቁንና ምስኪን ወገኖቻችን ለነጻነታቸው ሲሉ ህይወታቸውንም እየከፈሉ ነው። በአሁኑ ወቅት ወገኖቻችን እርዳታና ድጋፍ ከመቸውም የበለጠ ይፈልጋሉ። አለሁልህ የሚላቸው ይፈልጋሉ። እኛስ ውጭ የምንኖር ኢትዮጵያውያን ወገኖቻችንን ለማገዝ ትንሽም ነገር ቢሆን እንዴት መተባበር እንችላለን? አሁን ካልደረስንላቸው መቼ?

ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ለሁሉም የሚበቃ ምግብ እንደሌለ በታሪክ የታወቀ ነው። አሁንም እየታየ ነው። ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ይህንን ችግር ይረዱታል? ያውቁታል? ይሰማቸዋል? የሚለውን ባጭሩ አብረን እናያለን።

ትዮጵያዊ ዲያስፖራ ግን ወደ ውጭ ሲወጣ ቢያንስ የምግብ ችግር የለበትም። ነጻነቱም የተሻለ ነው። በምዕራቡ አለም ውስጥ ደግሞ ስራ ከሌለው ለመኖሪያ የሚሆን ድጎማ ያገኛል። ልጅ ሲወልድ የማሳደጊያ ድጎማ ይሰጠዋል። ሌሎችም የተለያዩ ጥቅማ ጥቅሞችንም ያገኛል። እራሱን የቻለ ደግሞ በነጻነት የተሻለ ህይወት ይኖራል። ከናፍቆትና አንዳንዱም የመኖሪያ ፈቃድ ገና የሌለው ቢሆንም ኢትዮጵያ ውስጥ እንዳለው ወገኑ አይራብም። ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ በሰው ሃገር ውስጥ ባዳ ሆኖ እንኳን እርዳታ ያገኛል።

ታዲያ ይህ ሁሉ ችግር እየታየ የኢትዮጵያ ባህል ምግብ ለምን ወደ ውጭ ሃገር ይወጣል? እኔ ቁጥር ባይኖረኝም ወደ አረብ ሃገር፣ አውሮጳ፣ አሜሪካ፣ አፍሪቃ፣ አውስትራሊያ ወዘተ ከኢትዮጵያ የሚወጣ የባህል ምግ በጣም ብዙ እንደሚሆን ማወቅ አያስቸግርም። በዚህ ፋንታ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ የሃገሩን ባህል ምግብ ካሰኘው ከሚኖርበት ውጭ ሃገር ውስጥ አመሳስሎ ለመስራት ሰፊ እድል አለው። ታዲያ ለምን ከኢትዮጵያ የመጣ ምግብ ይፈልጋል? እኔ እንደማየው ብዙ ዲያስፖራ ኢትዮጵያውያን ርህራሄና እውቀት ያንሳቸዋል። ይህ ለምን እንደሆነ ማስረዳት አለብኝ።

ይማኖተኞች ነን ብለው ከኢትዮጵያ በመጣ ምግብ ጾማቸውን የሚፈቱ ከሆነ ጾሙ ትርጉም የለውም። የጾም ትርጉሙን ለሚያውቅ ይኸ የውሸት ጾም ይባላል። ለማስመሰል ያህል ደግሞ ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያዊ ነኝ፤ ፓትሪወት ነኝ እያሉ በግላቸው ወደቤታቸው ገዝተው ለወገን እርህራሄ አለማሳየት እራስን በከንቱ መደለል ነው። ይኸ ደግሞ ውሸታም አገር ወዳድ ያስብላል። አስመጭና ላኪ ወያኔ ነው ካሉ በኋላ ከተቃውሞ ስብሰባ ወይም ሰልፍ ሲመለሱ የሚቃወሙት አካል በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ያቀረበላቸውን የባህል ምግብ መብላት ከእንሰሳወቹ አስተሳሰብ ጋር ይመሳሰላል። የዚህን ያህል የሰው ልጅ ቂል መሆን የለበትም። ከዚህ የበለጠ ሰው መሆንን የሚያሳንስ ድርጊት ያለ አይመስለኝ። በተለይ ምግብን በተመለከተ ዲያስፖራ ኢትዮጵያዊ እየተሞኘ ችግር ማባባስ እንጂ መፍትሄ መፍጠር አልተለማመደም። ግንባሩ ላይም "እኔ ውሸት ነኝ!" የሚል ጽሁፍ በትልቁና በወፍራሙ ለጥፎ ቢዞር የሚስማማው ይመስለኛል።

መጀመሪያ ደረጃ፤ እንደተለመደው እዚህ ታታሪው ላይ ኢትዮጵያ ውስጥ ታፍኖ በሚኖር ጭቁን ወገኔ ላይ ወቀሳ የለኝም። እኛ ኢትዮጵያውያን ዲያስፖራወች ግን በህይወታችን ውስጥ የምናስብለት፣ ስሜት የሚሰጠንና የሚያረካን ነገር ለማድረግ እውቀትና ርህራሄ እንደሚያንሰን ይሰማኛል። ለህሊናችን ብቻ ሳይሆን ህይወታችን ትርጉምና ቅርጽ እንዲኖረው የምንቆረቆርለት ነገር ሊኖረን ይገባል። ህይወታችን ቀፎ፣ ልባችን ድንጋይና አዕምሯችን ባዶ መሆን የለበትም። እንሰሳወች ያሳዩአቸውንና ያቀረቡላቸውን ይመገባሉ። ሰውን እንሰሳ ነው ማለቴ ሳይሆን አስተሳሰባችን ከእንሰሳወቹ አስተሳሰብ ጋር መመሳሰል የለበትም ለማለት ነው። ለምሳሌ በእንግሊዘኛ They behave like animals ይባላል። በኖርዌጂኛ ደግሞ De oppfører seg som dyr ይባላል። ይህ የሚባለው በሌላውም ባህል ቢሆን ሰወች ልክ እንደ እንሰሳ ሲያስቡ ወይም ሲያደርጉ ሲታዩ ነው።

እንሰሳወቹን አስተሳሰብ በተመለከተ አንድ ምሳሌ ላቅርብ። ሁለት ላሞችን እናነጻጽር። የመጀመሪያዋ ላም ገና በርሀብ ስላልደከመች ፈቅ ብላ እየተንቀሳቀሰች ሳር ትግጣለች። ሁለተኛዋ ግን ተርባ መንቀሳቀስ አትችልም። ለመጀመሪያዋ ላም ተጨማሪ ሳር ቢቀርብላት የቀረበላትን ሳር ትበላለች እንጂ የሁለተኛዋ ላም ችግር አይገባትም። የባህል ምግብን በተመለከተ አብዛኛው ኢትዮጵያዊ ዲያስፖራ አስተሳሰብ ልክ የመጀመሪያዋ ላም አስተሳሰብ ጋር ይመሳሰላል። ይህን አባባል ሲያዩ አፍንጫቸውን የሚነፉ ሰወች እንደሚኖሩ እገምታለሁ። በጣም አዝናለሁ። ይህን ቆንጆ አድርጎ መናገር ግን አይቻልም!!

ለዚህም ነው ነጮች የኔግሮወች አስተሳሰብ፣ ባህሪና አኗኗር ልክ እንደ እንሰሳወቹ ነው የሚሉን። የዚህም ምስክርነት ወደኋላ መቅረታችን ነው። ከዚህ የበለጠ ሌላ ምን ማስረጃ አለ? በነገራችን ላይ ሃገር ቤት ሲሄዱ ቋንቋ መደባለቅን፣ ጉራ ማብዛትን፣ የወገንን ችግር ሳይረዱ ስለ መንገድና ህንጻ ማውራትን ወዘተ ሁሉ ይጨምራል።

ማንኛውም ነገሩን ላለማስፋት ከራስ አልፎ ለወገን ማሰብና ርህራሄ ማሳየት ለህይወት ትርጉም አለው። በምድርም ሆነ በሰማይ ተቀባይነት አለው ብዬ አምናለሁ። ትርጉም አለው ብለን ዋጋ የምንሰጠው ነገር ህይወታችን ውስጥ ማስገባት ያለብን ይመስለኛል። እራሳችን በራሳችን ደግሞ እኔ ጥሩ ሰው ነኝ ብለን ለራሳችን የምንነግርበት አንዱ ቆንጆ አጋጣሚ ሊሆን ይችላል። የራሳችንንም ሞራል ከፍ ማድረግ አለብን። በቀላሉ ተጨማሪ እርዳታና ትብብር ለማድረግ ይገፋፋናል። ወገኖቻችንም የሚያስብላቸው ወገን እንዳለና የትብብር መንፈስ እንደሰፈነ ይሰማቸዋል። ትንሽ ነገር ቢመስልም መልእክቱና መንፈሱ ቀላል አይደለም። የአዕምሮ አንድነትና የልብ ውህደት ለመፍጠር ከወገኖቻችን ጎን መቆማችንን የምናሳይበትም አንዱ ቀላል መንገድ ነው። እዛው እሳቱ ውስጥ ሆነው እነሱ የሚታገሉለት ነጻነት ለኛም ጭምር ነው። ዲያስፖራውም በሚኖርበ ውጭ ሃገር ውስጥ ሌላ የምግብ ምርጫ ስላለው የባህል ሆዱን ተቋቁሞ ትብብር ካላደረገ ውለታ ቢስ ያደርገዋል። ህይወት ዝም ብላ በሆድ ብቻ አትለካም። ትርጉም አላት። ሰውን ሰው መሆኑን የሚያረጋግጥለት ደግሞ ተግባሩ ነው። ዛሬ የተበላ ምግብ ነገ በመቀመጫ ውልቅ ብሎ ይወጣል። ከእምነትም አኳያ ብናየው የሰው ልጅ ለነፍሱ እንጂ ለስጋው አይኖርም። ይህንንም ማወቁ ምን እያደረግን እንደሆነ እያንዳንዳችንን እንዲንጠይቅ ሊረዳን ይችላል? ወይ ከሰማይ ወይ ከመሬት አልሆንም። ዝም ብሎ በራሱ ሳይደረግ የሚመጣ ነገር የለም።
እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ!

Comments

Matthias Kebede's picture

Hi Fantaw
It is very touching and inspiring.
Thank you and keep it up the good work.
BR, Matthias

This is the least we in diaspora can do in a long term. Thanks and I hope some people will be inspired and pass the idea. //FT

Hello Seifu,
May be it is timely.... but I believe we should have began doing it long time ago. Thanks again.

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ