You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የዘመኑ ስልክና ሩጫ በየቦታው፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sat, 08/17/2013 - 19:45
first image: 

ወች ለመተዋወቅም ይሁን መጥበስ የሚችሉበት ቦታ ቁጥሩ ብዙ ነው፡፡ ያው ሰው አውቶብስ ለመያዝም ሲጠብቅ አጋጣሚው ስላለ በዛ በጠበበ ጊዜ ውስጥም ቢሆን ለደፈረ ታዲያስ ማለት አይቀርም፡፡ እንዲሁ ዝም ብሎ ለጊዜው ለመነጋገር ወይም ስለአየሩ የመሳሰሉትን ለመጫወት፡፡ አንዳንዱ ሰው በተፈጥሮው ከሰው ጋር ማውራት ደስ ስለሚለው የማያውቀውንም ቢሆን አውቶቡስ መጠበቂያ ላይ አንዳንድ ጊዜ አየት አድሮጎ ፈገግ ካለ በኋላ ታዲያስ ይላል፡፡ ለነገሩ ባሁኑ ጊዜ ብዙ ሰው በስልክ ተጠምዶ ስልክ ላይ ያወራል፣ ሙዚቃ ወይም የሆነ ነገር ያዳምጣል፣ ያነባል ወይም ያያል፡፡ ከዚህ ሁሉ ስራ የፈታ ጥቂት ነው፡፡ በዛም ላይ ደግሞ በአይን ብቻ ታይተው ገና ታዲያስ ሳይባሉ ስልካቸውን የሚያወጡ አሉ፡፡ ከሰው ለመሸሸግ ወይም ላለማናገር፡፡ ምናልባት እውነታቸው ይሆናል፡፡ ስልክ እኮ ያወሩበታል፣ ያነቡበታል፣ ፎቶና ቪዴወ ያነሱበታል፡፡ ስለዚህ ከማያውቁት ሰው ጋር መተያየትና ማውራት ምን ጥቅም አለው?

ጁ ላይ ስልክ ያልያዘ ሰውማ ስራ የፈታ ይመስላል፡፡ ታዲያ ትንሽ ለማውጋት ፈልጎ ታዲያስ ካለ ..... እንዴ፤ ሰውየው ምን ነካው? የማያውቀውን ሰው ከማየትና ታዲያስ ከማለት ይልቅ የራሱን ስልክ አውጦ የሆነ ነገር አያረግም? ከየት የመጣ ቂል ነው ባክችሁ? ስልክ የለውም? ወይስ የሱ ስልክ ስትታይ ታሳፍራለች? ያሰኛል፡፡ እሱ ግን በልቡ የሚያስበው አዬ ይኸ ህብረተሰባችን እኮ አርቲፊሻል ሆነ በማለት አሳስቦታል፡፡ አሁን ምናለበት ስልኩን እዚህ መንገድ ላይ እንኳን እረፍት ቢሰጡት ይላል፡፡ ሰው ሁላ ተበላሸ፡፡ በየቦታው ስልክ፣ በግር ለሚከደው እርቀት መኪና፣ አውቶቡስ እያለ በመኪናህ አድርሰኝ፣ ድስት እያለ ማይክሮወይቭ ምናምን የሚመርጠው በዛ፡፡ እያለ ይህንን ሲያሰላስልና የማያውቃቸውን ሰወች በሃሳቡ ሲፎግራቸውና ሲያማቸው ድንገት ለጊዜው በስልክ ያልተጠመደች ወጣት ከጎኑ ቆመች፡፡

ሰው ማየት አይኑ ስለተለማመደ ችግር የለበትምና እስከዛሬ ካያቸው ወጣት ሴቶች ቆንጆ ሆና አያት፡፡ ምናልባት ስልክ ስላላወጣች ይሆናል ቆንጆ የሆነችበት፡፡ ለማንኛውም እስከዛሬ መልስ አገኘም አላገኘ ወንዱን ታዲያስ ወንድም! ሴቱን ደግሞ ታዲያስ እህት! እያለ ነበር ወግ የሚጀምረው፡፡ ዛሬ ግን ይቺን ወጣት እንዲህ አላት፡፡

እሱ፤ "ታዲያስ አንቺ!" ምናልባት ቅድም ሲያስበው የነበረው እህት ማለትን ያስረሳው ይመስላል፡፡
እሷ፤ "ምነው እባክህ? እንደዛ ነው እሚባለ?" ብላ አፋጠጠችው፡፡
እሱ፤ "ታዲያ ዛሬ ገና አየሁሽ! ስምሽን አላውቀው፡፡ ብርቱካን ብልሽ ብርቱካን ካልሆንሽስ?"
እሷ፤ ከሱ የበለጠ ሞቅ ያለ ፈገግታ ካሳየችው በኋላ "አይ ምንም አይደለም" ብላ ስሟን ነገረችው፡፡
እሱ፤ እሱም ስሙን ነገራትና በዛች በተጣበበችና በሩጫ ጊዜ ውስጥ ብዙ ተጫወቱ፡፡ ተጠያየቁም፡፡ እሱም የሚያጣራውን በሚያውቀው ዘይቤ አጣርቶ ያንን የማይወደውን ስልክ ቁጥር መውሰድ ፈለገ፡፡ የሷ ቋንቋና ምልክት ባይታወቅም የምትገፋፋው መሰለው፡፡ በዛች ባጭር ጊዜ ውስጥ ደህና ተስማምተው ሲያወሩ ድንገት የሷ አውቶቡስ ቀድሞ ሊመጣ ሆነ፡፡ ሆኖም ግን እሱ ለሚወደው ወግ ጊዜ አጥሮት ይሁን ወይም ፈርቶ ስልክ ቁጥሯን ሳይጠይቃት አውቶቡሱ መጣ፡፡ ሲተዋወቁ ያልተጨባበጡትን ሲለያዩ በጅ ተጨባብጠው ቻው ተባባሉ፡፡

እሱ፤ እሷ ወደ አውቶቡሱ እየሄደች ገና ፈቀቅ ከማለቷ እሱ በሽቆ ስለነበርና እሷ ስትጠብቅ የነበረውን አውቶቡሱም አይቶ የቆየና አሮጌ ስለነበር፤ ቀስ ብሎ "ከርካሳ አውቶቡስ፤ ቀማኝ! ይኸን ነበር ስትጠብቅ የነበረው?" ሲል....
እሷ፤ "ምን አልክ!"
እሱ፤ እንዴት ሰማችኝ ብሎ እሳት የላሰ ጆሮዋን እያደነቀ በድንጋጤ "አይ፤ አንቺን አይደለም" አላት፡፡
እሷ፤ ወደሱ ኮስተር ብላ የነበረውን ወደ አውቶቡሱ ስትገባ ፈገግ እያለች 'አንተ ራስህ ካውቶቡሱ አትሻልም!' ብላው መንቀር መንቀር እያለች "አሁን እኮ ከኋላየ እያየኝ ነው'' ብላ አውቶቡሱ ውስጥ ጥልቅ አለች፡፡ እሱ ግን አልሰማትም፡፡ ልጅቷ ምን ነካት? እሱ የሚያስበው ስለ ጆሮዋ እሷ የምታስበው ስለ ጀርባዋ፡፡
እሱ፤ ከሄደች በኋላ "ይቺስ ጆሮዋ ከስልክ የበለጣ እሳት የላሰ ነው! ለዚህ ነው ስልክ ያልያዘችው! የሚቀጥለውን አውቶቡስ ያዢ ብዬ ብጠይቃት? ወይም ቀስ ብዬ ትንሽ መንገድ ብዘጋባት ኖሮ" እያለ ሲያሰላስል... ያንን የማይወደውን ስልክ ቁጥር ለመውሰድና እንደሌሎቹ በየመንገዱ በስልክ ለመቅደድ ይመስላል፡፡
እሷ፤ እሷ ደግሞ አውቶቡስ ውስጥ ገብታ ቁጭ እንዳለች ''ኡፍፍፍፍ እንደ ዛሬ ተደብሬ አላውቅም! እኔ እራሴ የሱን ስልክ ብጠይቀው ኖሮ.......ምናምን"፡፡ ልጅቷን ምን ነካት? ለመሆኑ እሱ ስልኩን ለሷ መስጠት መቻሉን እንዴት አወቀች? እሱ እንደሆነ አንዳንድ ጊዜ ካልተሳሳተ በስተቀር ወገኛ ስለሆነ ወንድ ለሴት ስልክ አይሰጥም የሚል ዘይቤ አለው፡፡ እሷ ይህን አታውቅም! ስልክም ቢሰጣት ኤጎዋን/ጉጉቷን ለመሙላት ነው እንጂ እንደማትደውልና ውሼታም መሆኗን እራሷ ታውቀዋለች፡፡

እሱ፤ "ጊዜ ቢያጥረኝም ሌላ ኮተት ከማብዛት ቁጥሯን ብጠይቃት ኖሮ.... ጎረቤቴ አይደለችም...... ሌላ ጊዜ እንዴት አገኛታለሁ ሲል አንድ ዘፈን ትዝ አለውና ቀስ ብሎ እንዳትሰማው፤
የሰማዩ ጌታ የምድሩ ባለቤት፣
የምወዳትን ልጅ አርግልኝ ጎረቤት፡፡

ከዛም ልጅቷን የቀማው አውቶቡስ ከአይኑ ሲጠፋ፤
ፍቅር፣ ፍቅር፣
በቃ ሄደች ይቅር፡፡
ብሎ እዚቹ በዚቹ እራሱ በገጠማት በመጨረሻዋ ግጥም ፍርፍር ብሎ እየሳቀ ሳለ ሲጠብቀው የነበረው አውቶቡስ ይዞት ጥርግ አለ፡፡

Comments

It is a nice one Fantaw. My comment is if you specify the name of the characters rather than using a general pronoun( he and she), it will be easy to remember and to tell the stories for others. I appreciate you effort.

Regards

Semahagn

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ