You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ጉዳይና የግለሰቦች አስተያየት፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Tue, 08/28/2012 - 15:27

ህን ጽሁፍ ልጽፍ የቻልኩት ባለፈው ጊዜ ህብረተሰባችን ውስጥ በኢማኖ በኩል ለኢትዮጵያ ቀን 2012 ማስታወቂያ ላይ ስለቀረበው ህዝብ የማያምንበት ካርታ ጉዳይ ምክንያት ነው፡፡ የጽሁፉ ዋና አላማ ግን ብሄራዊ ጉዳይ ጥንቃቄ የሚያስፈልገው ስለሆነ ማንኛውም አገሩን ወዳድ (ናሽናሊስት) መሪ ጉዳዩን ትኩረት እንዲሰጠው ለማሳሰብ ነው፡፡ ለአንድ ትልቅ ሃሳብና ፈጠራ የመጀመሪያ ምንጩ አንድ ግለሰብ ነው፡፡ የተገኘው ሃሳብ ወይም ፈጠራ ተግባር ላይ መዋል የሚችለው ግን በህብረተሰቡ ወይም በሚመለከታቸው ሲደገፍ ነው፡፡ ወይም ሃሳቡ ጠቃሚ፣ አማራጭና ተቀባይነት ሲኖረው ነው፡፡ አሁን ትንሽ ፈጠራ የሚለውን ትቼ ሃሳብ ላይ ብቻ አተኩራለሁ፡፡

በተለምዶ እኛ ኢትዮጵያውያን የሆነ አንገብጋቢ ጉዳይ ላይ ለመነጋገር አቅቶን ሳይሆነ በእንጥልጥል እንተወዋለን፡፡ ምናልባት አይበጅም ወይም በመካከላችን ክርክር እንዳያመጣ ብለን አስበን ሊሆን ይችላል፡፡ ነገር ግን ነካ ነካ ተደርጎና ተሸፍኖ የታለፈ ጉዳይ በጊዜው መፍትሄ ስላላገኘ ወይም ቢያንስ ስላልተነጋገርንበት ተመልሶ አንድ ቀን ብቅ ይላል፡፡

ለምሳሌ በአንድ የቀረበ ሃሳብ ላይ የተወሰኑ ይሁኑም ብዛት ያላቸው የሚበልጡት ሰወች ከተስማሙና ይህ ቢሆን ይሻላል ካሉ ሃሳቡን ለአማራጭነት ከፍ ያደርገዋል፡፡ አንድ ሃሳብ እንደ ጥሩ አማራጭነት ቀርቦና ሃሳብ ተሰጥቶበት ከተደገፈ፤ እንዳይጸድቅ ደግሞ የሚያግደው ነገር መኖር የለበትም፡፡ በአማራጩ ሃሳብ ዙሪያ የተስማሙት ለምሳሌ “እኔ ብቻ አውቃለሁ” እንደተባለ ሆኖ መተርጎም የለበትም፡፡
አንድ ግለሰብ የመሰለውን ወይም የሚያውቀውን ተንትኖ እራሱን ሲገልጽ አውቃለሁ ብሎ ነው ተብሎ መፈረጅም ስህተት ነው፡፡ በዛ ፋንታ ግን ተቃውሞ ካለ የጉዳዩን አቅጣጫ ሳይቀይሩ ማስረዳት ተገቢ ነው ይመስለኛል፡፡ አብዛኛው የተስማማበትንም አማራጭ ሃሳብ መቀበል ትክክለኛ አሰራር ይመስለኛል፡፡ ሰው ፍጹም መሆን ስለማይችል ስህተት ወይም ከጊዜው ጋር የማይሄድ ነገር ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሃሳቦች በመጡ ጊዜ ግን ሃሳቦችን አስተናግዶ መፍትሄ መሻት እንጂ ግትር ማለት አያስፈልግም፡፡!

ንድ መሪ ብሄራዊ በሆነ ጉዳይ በቀረበ አማራጭ ሃሳብ ላይ በዚህ እንኳን አልበገርም የመሳሰሉትን ሳይል ለራሱም ሆነ ለሚመራው ተቋም ክብር ማሳየት ያለበት ይመስለኛል፡፡ ምክንያቱም ኢትዮጵያ የጋራ እንጂ የግል ስላልሆነች፡፡ የቀረበው ሃሳብ ካላረካ ደግሞ በቀረበው ሃሳብ ላይ መነሻ በማድረግ መፍትሄ መፈለግ ብልህነት ነው፡፡ በተለይ ጉዳዩ ብሄራዊ ነክ ከሆነ ጥንቃቄ የሚያስፈልገውና ህብረተሰቡንም ሆነ ኢትዮጵያን ማክበር አስፈላጊ ነው፡፡ ያ ካልሆነ ግን ሚዛናዊነት ያንስና ያው ዞሮዞሮ ዲክታቶርነት የሚጀምረው እንዲህ እያለ ነው፡፡ ለሰለጠነ ሰው ባለፈው ጊዜ የወጣው ማስታወቂያና ይዘቱ ከዛም ተከትሎ የተጻፈው ተራ ነገር ህብረተሰቡን ይቅርታ መጠየቅ የሚያሻው ነው፡፡ ሃገራችን ኢትዮጵያ ለዚህ የበቃችው አንድ ግለሰብ ወይም የተወሰኑ ግለሰቦች በሃገራችን እጣ ፋንታ ላይ በግድ ወይም ህዝብ ሳያማክሩ በራሳቸው ስለሚወስኑ ነው፡፡

ተጨማሪም አንድ መሪ ልክ እንደ መሪ አክት ማድረግ አለበት እንጂ የቀረቡትን አማራጭ ሃሳቦች ላለመቀበል ጉዳዩን ማስፋት ወይም ሌላ አቅጣጫ ማስያዝ አስፈላጊ አይመስለኝም፡፡ ጥሩ መሪ ማለት እኔ እንደማውቀው ሃላፊነት ካለባቸው ባልደረቦቹና ህብረተሰቡ ጋር አብሮ መስራት ማለት ነው፡፡ ስለዚህ አንድ መሪ እራሱንም ሆነ የሚመራውን ተቋም ለማክበርና ለማስከበር በተቻለ መጠን ክብርና ትህትና ማሳየት ወሳኝ ነው፡፡ የተሻለ ሰው ለመሆን፡፡ ይህ ከአንደኛ ደረጃ አስተሳሰብ ውስጥ አንዱ ነው፡፡

በዚች ቅድስት ኢትዮጵያ ሃገራችን ላይ ካመንና ከታገልን አንድ ቀን ስለምትነሳ እምነታችንም ከዛ ጋር አብሮ መሆን ይገባዋል፡፡ የኢትዮጵያ ጠላቶች የሚያቀብሉንን ዝም ብለን እንደ ፈረንጆቹ የምንቀበል ከሆነ የእናት ሃገር ሃላፊነታችን የቱ ላይ ነው? የወደፊቷ ኢትዮጵያ ቢያንስ የባህር በር ይኖራታል፡፡ "መጠጊያ ያጣ ዱቄት ከንፋስ ይጠጋል" እንደሚባለው እንዳንሆን በተለይ መድረኩ ያላቸው ሃገር ወዳድ ኢትዮጵያውያን መሪወች ይህንን የብሄራዊ አንገብጋቢ ጉዳይ አክብደው እንዲያዩት አሳስባለሁ፡፡

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ