You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ስለ ኢትዮጵያ ተነሺ፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sat, 07/10/2004 - 11:17
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic

እኛ ኢትዮጵያውያን ማድረግ በምንችላቸው ቀላል ነገሮች ላይ ድንበር እስካላስቀመጥን ድረስ ነጻ መሆን፣ ማደግና መደሰት እንደምንችል በቀላሉ ኣቅጣጫ ለማሳየት ነው። የኢትዮጵያ ተነሺ አቀራረብ ምናልባት ብዙወቻችንን በቀጥታ ሊነካ ይችላል። ነገር ግን ዋናው ኣላማ ሁሉም የኢትዮጵያ ልጆች ተከባብረውና ተባብረው ስርአት፣ ትዕግስትና እውቀት ከዛም በራስ መተማመን እንዲያዳብሩ አቅጣጫ ለማሳየት ነው። በእርግጥ አንዳንድ ወቀሳወች ሊኖሩ ይችላሉ፡፡ ጥንቃቄ የተሞላበት ወቀሳ የማቀርበው ግን ግልፅ ባልሆኑ አስተሳሰብና ድርጊታችን ላይ እንጂ ግለሰቦችን እንዳልሆነ ከወድሁ አሳስባለሁ፡፡ ለጨለማ ጊዜ መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለችገር ጊዜም ብልሃት ያስፈልጋል፡፡ ኋላ ቀርነትን ለማሸነፍ የራስን አስተሳሰብና ድርጊት በተገቢው ለማስተካከል ማንም ሰው ቢሆን አቅጣጫና ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ የሰው ልጅ፤ ብዙውን ጊዜ እውነቱ በአንድ ጊዜ ፍርጥ ብሎ ሲነገረው ላይወድ ይችላል፡፡ በአለማችን ውስጥ ለመቀየር በጣም አስቸጋሪ ጉዳይ ነው ከሚባለው አንዱ ባህሪ ነው፡፡ በዚህም የተነሳ ቶሎ ብሎ ከራስ ስህተት ለመማር ያስቸግራል፡፡ ሆኖም ግን የሆነ ጊዜና ቦታ ላይ የሆነ ሰው መናገር አለበት፡፡ ታዲያ ኢትዮጵያ ወደኋላ መቅረቷ ምስክር ስለሆነና የዚህ መንስኤውም መሰረታዊ የአስተሳሰብ ለውጥ ማድረግ ነው ብዬ ያመንኩበትን ነገር በቀላሉ ለወገኖቼ ለማካፈል ነው፡፡

ይህ ፅሁፍ በትርፍ ጊዜዬ ከማደርጋቸው ስራወች አንዱ ነው፡፡ ሙያየ አይደለም፡፡ ነገር ግን "ሞኝ ውኃ ሲወስደው ይስቃል" እንደሚባለው ሆነን እንዳንቀር ለወገንና ለሃር በማሰብ ነው የምፅፈው፡፡ ይህ ማለት ችግር እያለብን እንደሌለብን ሆነን ባለንበት መቀጠል አያስፈልግም፡፡ ለጨለማ ጊዜ መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለችገር ጊዜም ብልሃት ያስፈልጋል፡፡

ታዲያ ኋላ ቀርነትን ለማሸነፍ የራስን አስተሳሰብና ድርጊት በተገቢው ለማስተካከል ከትንሽ ጥቆማ ጋር በራሳችን መጣር አለብን፡፡ የሚስተካከሉት ነገሮች ብዙና ጊዜ የሚፈልጉ ቢሆኑም እራስን ለማስተካከል አሁን መጀመሩ አይከፋም፡፡ እድሜዎ አራትም ይሁን ሰማንያ ትምህርት አያልቅም፡፡ ስለዚህ ይህችን ልዩ ጽሁፍ አንብበው ከወደዷት በተግባር እንዲተገብሯት በአክብሮት እጠይቀዎታለሁ፡፡ ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኩር እንጂ ላደጉም ሆነ በማደግ ላይ ላሉ ሃገሮችም ጭምር ይጠቅማል፡፡

ኢትዮጵያ ተነሺ የትምህርት መስጫና የሞራል መገንቢያ ቦታ ነች፡፡ የሚብለጨለጭና የሚሽከረከር ነገር እዚህ የለም፡፡ ስለዚህ ተረጋግተውና ሃሳብዎን አጠቃለው እንድያነቡ ተጥሮበታል፡፡ በተረፈ መልካም ማንበብ ይሁንለዎት፡፡ እባክዎ አስተያየትዎ አይለየኝ!

ኢትዮጵያ ተነሺ!
ዕውቀት፣ ባህሪና አንድነት ሃይል ነው!
ለውድቷ እናቴ ለወርቅነሽ ተሰማ መታሰቢያ ይሁን፡፡
እንደ ኢትዮጵያ አቆጣጠር ሃምሌ 1996፡፡