You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

የኢትዮጵያዊ ስራና ጥልቅ ስሜት አቅም፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sun, 05/25/2014 - 17:52
tatariw ethiopia amharic addis ababa passions

መጀመሪያ ስሜት ምን እንደሆነ ማየት ያስፈልጋል። በኔ አስተያየት ስሜት በሁለት ይከፈላል። አንደኛው ሰውነታችን ሲነካ የሚነዝረን ወይም የሚሰማን ስሜት ነው። ይህንን በተመለከተ ፍቅረኛሞቹ ውይም ባልና ሚስት በግላቸው እንዳሰኛቸው ያድርጉ እንጂ እኔ ስለነሱ ስሜት ምንም አስተያየት አልሰጥም። አያገባኝም።

ሁለታኛው ስሜት ግን ሃሳባዊ ስሜት ነው። ሃሳባዊ ስሜት ለምሳሌ በዙሪያችን በሚደረጉ፣ በሚታዩና በሚሰሙ ነገሮች ላይ የምናሳየው ግንኙነትና ትስስር ነው። በየጊዜውና በዙሪያችን ልባችን እንዲያዝን ወይም እንዲደሰት የሚያደርጉ ስሜቶች አሉ። በተመሳሳይ ደግሞ አዕምሮአችን እንዲቀበልና እንዳይቀበል የሚያደርጉ ስሜቶች አሉ። ስለዚህ በእኔ እይታ ሃሳባዊ ስሜት ከልብና ከአዕምሮ ጋር ግንኙነት አለው። ባጠቃላይ ሃሳባዊ ስሜት ማለት ከልባችን ለመውደድና በአእምሮአችን ለመረዳት በዙሪያችን በሚከሰቱ ነገሮች ላይ የምናሳየው ጥልቅ ፍላጎትና የምናደርገው ግንኙነት ነው። አንድ ሰው ጥልቅ ፍላጎትና ግንኙነት ከሌለው ከልብ መውደድ አይችልም። ጥልቅ ፍላጎትና ግንኙነት ከሌለው በአዕምሮ መረዳት አይቻልም። ባጭሩ ሃሳባዊ ስሜት ማለት በህይወታችን ውስጥ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ ፍላጎት ማሳየትና ግንኙነት መፍጠር ማለት ነው። ይህ ጥልቅ ስሜት ለመስራት፣ ለመተግበር፣ ለማዳመጥ፣ ለማሸነፍ፣ ለመውደድ፣ ለመከባበር፣ በአዕምሮም ይሁን በአካል ታግሎ ነጻ መሆን፣ ለወገንና ለሃገር መድረስ፣ የተቸገሩትን መርዳትና የደከሙትን ማስተማርና መደገፍ ወዘተ ሊሆን ይችላል። ጥልቅ ስሜት ለኔ ከማንኛውም እውነታ ጋር ተጋፍጦ ማሸነፍና ለህይወት ትርጉም መስጠት ነው።

ትዮጵያ እንድትበለጽግና እንደ አንዲት ሃገርና ዜጋ መቀጠል እንድትችል ሰወች ከላይ በተጠቀሱት ነጥቦች ላይ ጥልቅ ስሜትና ጸባይ ሲኖራቸው ነው። ነገር ግን ብዙ ጊዜ እንደሚታየው ይህንን ስሜትና ጸባይ ኢትዮጵያውያን ገና አላዳበሩትም። ኢትዮጵያዊ ጨዋ ይባላል ግን የምናደርገው ከጨዋነት የራቀ ነው። ከእውነታው ጋር ፍላጎትና ግንኙነት አናደርግም። ብናደርግም የነካ ነካ ነው። ጥልቅ ስሜት የሚባል ነገር ብዙ ኢጥዮጵያውያን ላይ የተለመደ አይደለም።

እንደሚታወቀው አንድ መቶ እጅ ብሎ ነገር የለም። እና ሁሉም ሰው እንደዚህ ነው ማለቴ አይደለም። ነገር ግን ለምሳሌ በጣም ብዙ ኢትዮጵያውያን ስሜት ከሌላቸው ውጤቱ ብሄራዊ ችግር ይሆናል። የሚታየውም ይኸ ነው። ለምሳሌ ከቀጠሮ፣ ከቋንቋ፣ ከወገንና ከሃገር፣ ከመውደድ፣ ከማሸነፍ፣ በደንብ ከመስራት፣ ከማክበር፣ ከራስና ከወገን ታማኝነት ወዘተ ጋር የረባ ጥልቅ ስሜት የለንም። በተለይ በተደጋጋሚ የሚታዩ ስሜቶች ስህተታችን ሲነገረን ስህተትን ከማረምና ከመማር ይልቅ ስህተቱ ለምን ተነገረን ብለን የምናሳየው ስሜት ነው። የውርዴት ስሜት። በተለይ ይኸ ከትንሽ እስከ ትልቅ መሪወች ላይ ይብሳል።

ሰው ከልቡ ለመውደድና በአእምሮው ለመረዳት የሚችለው በዙሪያው ከሚከሰቱ ሁኔታወች ላይ ፍልጎት አሳይቶና ግንኙነት አድርጎ የሚሰማው ስሜት ሲኖረው ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያን በህይወታቸው ላይ ፍላጎት የማያሳዩትና ግንኙነት የማይፈጥሩት የሚማሩት አጥተው አይደለም። የሚያዩት አጥተው አይደለም። የሚያነቡት አጥተው አይደለም። የሚያስተምራቸው ወይም የሚነግራቸው አጥተው አይደለም። የሚጨቁናቸው አጥተው አይደለም። ጽፎም የሚያቀርብላቸው አጥተው አይደለም። ግን ለመማር፣ ለማንበብ፣ ለመውደድ፣ ለመስማትና ለማየት ጥልቅ ስሜት ስለሌላቸው ነው። በአእምሮም ይሁን በጉልበት (የሚያጠቃቸው ሲኖር) ለመታገል ስሜት ስለሚያንሳቸው ነው። ከእውነታ ጋር ፍላጎት ስለማያሳዩና ግንኙነት ስለማይፈጥሩ ነው (ስሜት)። ምክንያቱም ልባቸው እንዳይወድ ዘግተውታል። አይናቸው እንዳያይ ጋርደውታል። አእምሮአቸው በትክክል እንዳይረዳ ችላ ብለውታል። በደንብ እንዳይታገሉ አቅማቸውን ይጠራጠሩታል። ትክክል ለመሆን ስሜት የላቸውም። ሃገር ቤት ያሉት ወገኖቻችን ጋር የጋራ ነገርና ትሥሥር ቢኖረንም በነሱ መፍረድ ባይቻልም ዲያስፖራው የተለየ አለም ውስጥ ነው እሚኖረው። የተሻለ የሚታይና የሚደረግ አለም ውስጥ እየኖረ የበለጠ ጥልቅ ስሜት ማዳበር በቻለ ነበር።

አንድ ሰው ጓደኛውን፣ ቤተሰቡን፣ ህብረተሰቡን፣ ሃገሩን ከዛም አልፎ አለምን መቀየር ይችላል። ብዙ ኢትዮጵያውያን እያንዳንዳቸው በጥልቅ ስሜት ከእውነታ ጋር ግንኙነት ከፈጥሩ ለሁላችንም እድገትና አስተዋጽኦ እንደሚያደርጉ የሚያውቁት አይመስልም። ችላ ስለሚሉት በአካባቢያቸው፣ በሃገርና በመገናቸው በሚፈጠሩት ነገሮች ላይ እንዲሁም በሚናገሩትና በሚያደርጉት ነገር ላይ ፍላጎት አያሳዩም፤ ግንኙነት አይፈጥሩም። ስሜት የላቸውም። ይህ አባባል ምናልባት አንዳንድ ሰወች ላይቀበሉት ይችላሉ። እኔ ግን የማወራው ነካ ነካ ስሜት ሳይሆን ስለ ቋሚ፣ ቀጣይና ታማኝ ስሜት ነው። ስለ ገትሮና ጸንቶ መያዝን ነው እማወራው። እንደ ሳሙና የሚሙለጨለጭ ለራስም ሆነ ለሌላ ሰው የሽንገላ ስሜት አይደለም የማወራው። ሰወች ከዚህ በፊት የማያውቁትን፣ ልብ ያላሉትን ወይም ያልሰሙትን ሲነግሯቸው ይህ ነገር ልክ ነወይ? ይሰራል ወይ ብለው ትንሽ እንኳን ስሜት አይሰጡትም። ለጉዳዩ ትኩረትና ስሜት ሰጥቶ ከመመርመር በፊት እከሌ ስለኔ አውቅልሃለሁ አለኝ በማለት እራሳቸውን ዝቅ ያደርጉታል። የምንጠቀምበት ስልክ፣ የምንነዳው መኪና፣ የበርንንበት አውሮፕላን፣ የምንጽፍበት ኮምፕዩተር፣ የምንለኩሰው ኤሌክትሪክ ወዘተ በውጭ ሃገር ግለሰቦች በጥልቅ ስሜት የተገኘ ነው። ተሞክሮና ተፈትኖ ስራ ላይ ውሏል። እኛም እንጠቀምበታለን። እኛ ግን ለራስችን በራሳችን ሃስብ ሲፈልቅ የመመርመር ስሜታችን በጣም አነስተኛ ነው። ስናደንቅ ትንሹን ሃሳብ ትልቅ አድረገን እናጎላዋለን። ምክንያቱም ስለ ትልቅ ነገር ያለን ስሜት አነስተኛ ስለሆነ ነው። ስንቃወም ደግሞ አቅጣጫውን እንቀይራለ። ምክንያቱም ለመቃወም ምክንያቱን ፈልገን የማወቅና የማግኘት ስሜታችን አነስተኛ ስለሆነ ነው። ባጭሩ ጊዜን፣ ቀጠሮና ቋንቋን፣ ተፎካካሪ ጥያቄወችን እንደምሳሌ መጥቀስ ይቻላል። በቀላሉ የብዙ ኢትዮጵያውያን ስሜት የዚህ ያህል ነው። የሰው ልጅ ባለውና በትንሹ ጀምሮ ካልተለማመደ ትልቅ ነገር ማድረግ አይችልም። ሳይለማመድ ከየት ያመጣዋል?

መስራት፣ ለመውደድ፣ ለመታገል፣ ለማሸነፍ፣ በአምላክ ለማመን፣ የተቸገሩትን ለመደገፍና ለመተባበር የምናሳየው ስሜት በጣም አነስተኛ ነው። ጥልቅ ስሜት የለንም። ብዙ አይቻለሁ። ብዙ ሰወች ኢትዮጵያ ውስጥ ስላለው ችግር ያወራሉ። ወያኔን ይረግማሉ። ለኢትዮጵያ መልካም ይመኛሉ። ቦታ ጊዜና ጽሁፍ እየመረጡ ዛሬ ወያኔ በኋላ ደግሞ መንግስት ይላሉ። የስብሰባና የሜዲያ ኤቲክስ የሚሉት ዜማ አላቸው። ኤቲክስ ማለት ደግሞ የሞራል መርሆ ማለት ነው። ይህንን እንኳን ጠንቅቀው የማወቅ ስሜት ስለሌላቸው ኤቲክስ የሚባለውን አደናግረው ይጠቀሙበታል። ለራሳቸው እንኳን ቋሚና ታማኝ ስሜት የላቸውም። ትልቁ ጦርነት የአዕምሮና የሃሳብ ጦርነት መሆኑ ገና ስሜታቸው ውስጥ አልገባም። በሌሎች ስር መውደቅና በራስም አስተሳሰብ ባሪያ መሆን እንጂ መታገል አያሳፍርም። በንግግር እንኳን ገትሮ የመያዝ አሞት የላቸውም። ምክንያቱም ንግግር ይረጫል። ለብዙሃን ይደርሳል። አስተያየትና ፍላጎትን ይቀይራል። ህዝብ ይቀሰቅሳል። ህዝብን ከእውነታው ጋር አገናኝቶ ጥልቅ ስሜት እንዲኖረው ያደርጋል። በዚህ ላይ ብዙ ኢትዮጵያውያን ነካ ነካ እንጅ ጥልቅ ስሜት የላቸውም።

ነጻነት እራስን በመሸወድና በልመና አይገኝም። አያቶቻችን ኢትዮጵያ ክብሯ ተጠብቆና ተከብራ እንዲትቆይ ያደረጓት በጉልበትም ይሁን በአእምሮ ቆራጥ ስለሆኑና መስዋእት ስለከፈሉ ነው። ከባንዳወቹ በስተቀር ፋሽት ኢጣሊያን ኢትዮጵያ ውስጥ እንደ መንግስት አልተቀበሉትም። እኛም ጋር በርካታ ግለሰቦች እውነተኛ የሃገርና የወገን ፍቅር ስሜት ሲያሳዩ እንዳውም ብቻቸውን ይሆናሉ። ስሜታዊ ናችሁ ይባላል። ኢትዮጵያ ውስጥ ለሚደርሰው ግፍ ስሜት ማሳየት ለኔ ምንም ስህተት አላይበትም። ሁሉም ጽሁፌ ላይ ስሜት ስል ደግሞ የክፋት ስሜት ማለቴ አይደለም።

ርቶ፣ ወዶና ታግሎ ለማሸነፍ የብዙ ኢትዮጵያውያን ጥልቅ ስሜት በጣም አነስተኛ ነው የሚል እምነት አለን። ለዚህም ምስክሩ ያለንበት ሁኔታና የምንኖርበት ህይወት ነው። ኢትዮጵያ ያለችበት ደረጃ ነው። ማንም ሰው ይሁን ማንም ዜጋ ሰው እንደመሆኑ ከማንም አያንስም። የሚለያየን ግን ከእውነታው ጋር የምናሳየው ጥልቅ ስሜት፣ ከህይወት ካር የምንፈጥረው ግንኙነትና የምናገኘው የህይወት ትርጉም ነው። ብዙ ኢትዮጵያውያን በህይወታቸው ውስጥ የቱን ያህል እንደተጎዱና የማን ጥፋት እንደሆነ የማወቅ፣ የመዳሰስና የመጨበጥ አቅምና ስሜታቸው በጣም አነስተኛ ነው።

በመጨረሻም እኔ ትክክል ነኝ ለማለት ሳይሆን ሰው የራሱን ህይወት ማሸነፍ የሚችላው ከእውነት ጋር ጥልቅ ስሜት ሲኖረው ነው ለማለት ነው። እውነታውና ጥልቅ ስሜቱን ደግሞ እኔ አልፈጠርኩትም። እውነታውና ጥልቁ ስሜቱ የሰው ልጅ በህይወቱ ፍሬአማ እንዲሆንና ህሊናው እንዲረካለት በፈጣሪ አምላካችን፣ በተሞክሮና በልምድ፣ እንዲሁም በሰው ሰራሽ ህግ ተሰርቶ ቁጭ ብሏላ። ያንን እንጠቀምበት ለማለት ነው። ብዙወቹ ያደጉት ሃገር ዜጎች በተለይ ለራሳቸውና ለሃገራቸው ለመስራት፣ ለመውደድና ለመታገል ጥልቅ ስሜት አላቸው። እኛስ?

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ