You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ኮምፕዩተርወ በቀላሉ እንዳይጠቃ ጥንቃቄ ያድርጉ፤ ክፍል ሶስት፤ ባህሪና አጠቃቀም።

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Thu, 04/24/2014 - 23:09
Ethiopia wake up addis ababa amharic ethiopia tatariw

ክፍል አንድ ላይ ደህንነት ከምን ጋር እንደሚመሳሰል አይተናል። ክፍል ሁለት ላይ ደግሞ ሶስቱን ዋና ዋና ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች ባጭሩ እንዴት እንደሚሰሩ ከዛም ደካማና ጠንካራ ጎናቸውን አይተናል።

ሁን ሶስተኛው ክፍል ላይ ደግሞ ስለ ሶስቱም ኦፕሬቲንግ ሲስተሞች አጠቃቀም እናያለን። እንደሚታወቀው አብዣኛው ሰው ዊንዶውስ ይጠቀማል። አንደኛው ክፍል ላይ በዝርዝር ዊንዶውስ ለምን ለጥቃት እንደተጋለጠ ገልጫለሁ። የኮምፕዩተር ጥቃትን ለመቀነስ የተጠቃሚው ባህሪ ወሳኝ ነው። የተጠቃሚው ባህሪ/የአጠቃቀም ባህል ሊያስጠቃውም ሊያድነውም ይችላል። የሚከተሉት ነጥቦች ለሁሉም አይነት ኦፕሬቲንግ ሲስተም መጠቀሚያ ናቸው። ሆኖም ግን ዊንዶውስ ብዙ ቀዳዳ ስላለው በሚያስፈልግ ጊዜ በተለይ ዊንዶውስ እያልኩ እጠቅሳለሁ።

ለፊያ ቃልወን (ፓስወርድ) አልፎ አልፎ ይቀይሩ።
ማለፊያ ቃል ከሌላ ሰው ጋር የማይጋሩት የግል ብቻ ነው። ጠንካራ ማለፊያ ቃልም መሆን አለበት። ማን ኢንተርኔት ላይ እንደሚያፈነፍን ስለማይታወቅ ማለፊያ ቃል አልፎ አልፎ መቀየር አለበት። ለምሳሌ YezihAmet#2014QrtOne1 (የዚህ አመት ቁጥር 2014 ኳርተር ዋን 1)ማለት ነው። ትልቅና ትንሽ ፊደሎች፣ ቁጥሮችና ምስል አለበት። ሌላ ጊዜ ከሶስት ወራት በኋላ ሲቀየር የመጨረሻወቹን አራት አሃዛት ብቻ መቀየር ነው። አመቱ ሲያልቅ ደግሞ 2014 ይቀየራል። የራስወን የሚስማማወትን ግን የማይረሱትን ቅንብር መፍጠር ይችላሉ።
አንድ አይነት ማለፊያ ቃል በየቦታው መጠቀም ለጥቃት ያጋልጣል። ለምሳሌ ለጉግልንና ለባንክ መግቢያ በአንድ አይነት ማለፊያ ቃል መጠቀም ለጥቃት ያጋልጣል።

የኦፕሬቲንግ ሲስተም አያያዝና ተጨማሪ ሶፍትዌሮች በተለይ ዊንዶውስ፤

ኦፕሬቲንግ ሲስተምና ተጨማሪ ሶፍትዌሮች በየጊዜው ይታደሳሉ። የሚታደሱትም ደህንነትን ለመጨመርና ለመጠቀም የበለጠ ምቹ እንዲሆኑ ነው። በተለይ ኦፕሬቲንግ ሲስተምን በፍጥነት ማደስ ወይም አፕ ቱ ደይት መሆኑ ማረጋገጥ ያስፈልጋል። መጠቀሚያ ሶፍትዌሮችንም መታደስ የሚያስፈልጋቸው ከሆነ አልፎ አልፎ መፈተሽ ያስፈልጋል። ጊዜቸው ያለፈባቸውንም ወይም መተደስ ያቆሙ ሶፍትዌሮች ካሉ ማስወጣት ቀዳዳ መድፈን ነው። ኮምፕዩተር ልክ እንደ መኪና እንክብካቤና ክትትል ያስፈልገዋል።

ያጠቃቀም ባህሪና አለማወቅ፤

ብዙ ዊንዶውስ ተጠቃሚወች በተለይ የኢትዮጵያውያን ችግር ያጠቃቀም ባህሪ ችግርና አለማወቅ ናቸው።
ነጻ የሆኑ ሶፍትዌሮችን ሳያጣሩ መሰብሰብ ያስጠቃል። ከሶፍትዌሩ ጋር ማስታወቂያ ይጨምሩበታል። ይህንን ማስታወቂያ በኋላ ማስወጣት በጣም አስቸጋሪ ነው። የት ሄዶ እንደሚቀመጥ አይታወቅም። እነዚህ ለዊንዶውስ የተሰሩ አብዛኛወቹ የነጻ ሶፍትዌሮች አላማ አላቸው። ጥሩ የነጻ ሶፍትዌሮች ቢኖሩም ማጣራት ያስፈልጋል። ቤቱን ብርግድ አድርጎ ከፍቶ የማያውቀውን ሰው ወደ ቤቱ የሚያስገባ የለም። እኔ ኢትዮጵያዊ በባህሌ እንግዳ ማስተናገድ አይቸግረኝም ለሚል ሰው ኮምፕዩተርን በተመለከተ አያዋጣም!!

ነጻና ጠቃሚ መስለው ኮምፕዩተሩን ለማበላሸት ወይም ተጠቃሚው ምን አይነት እንቅስቃሴ እንዳለው ለመሰለልም የሚላኩ ሶፍትዌሮች አሉ። ለምሳሌ የተጠቃሚውን እንቅስቃሴ የሚፈልጉት ማስታወቂያ እየላኩ ለማስቸገር ወዘተ ነው። ስለላ ከሆነ ደግሞ ተጠቃሚው ምን እንደሚያደርግ ለመከታተልና ከተሳካም የተጠቃሚውን ኮምፕዩተር ለመጥለፍ ወይም ያለውን ሰነድ ለመስረቅ ወዘተ ነው። ይህ ሁሉ የሚደርሰው ግን ተጠቃሚው ሳያጣራ ወይም በግደለሽነት እነዚህ ጎጂ ሶፍትዌሮች ኮምፕዩተሩ ላይ እንዲሰፍሩ ስለሚፈቅድ ነው። ጎጂ ሶፍትዌሮች ሳይፈቀድላቸው በራሳቸው ለመግባት በመርፌ ቀዳዳ ግመል እንደሚባለው ነው። ለዚህም ነው የተጠቃሚው ያጠቃቀም ባህሪ ብዬ የጠራሁት። ምክንያቱም ብዙው ሰው የነጻ ሶፍትዌር ሲባል ከጀርባው ምን እንዳለበት አይገምትም። ነጻ ስለሆነ ብቻ መጠቀም ይፈልጋል። ለጓደኛም የነጻ ፕሮግራም አለ ተጠቀምበት ብሎ መንገር የተለመደ ነው። ጉዳቱ ግን አይታይም። ኢትዮጵያዊማ ከሆነ እንኳን ሶፍትዌር ቀርቶ ሳይሰራ እንኳን በነጻ ነጻ እሆናለሁ ብሎ የሚያልም ጥቂት አይደለም።

ሌላው ደግሞ ማለፊያ ቃል የሌለበት ክፍት የሆነ የነጻ ኢንተርኔት መጠቀም አንዱ የመጠቂያ መንገድ ነው። ነጻ ያደረጉት ዝም ብለው አይደለም። የሆነ ተንኮል አለበት። ሰወች ግን በዚህም ይታለላሉ።

ዋናወቹ አንዱ የመጠቂያ መንገድ ደግሞ ካልታወቀ ቦታ በኢሜይል ማጣቀሻና ተያያዘው የሚመጡ ሰነዶች ናቸው። ማጣቀሻውን እንዳለ ከኢሜይሉ ሲከፍቱት በሌላ ጊዜ ተጨማሪ ማስታወቂያ እንዲመጣ መንገር ነው። ሰነዱን ሲከፍቱት ደግሞ ተባይ የያዘ ሰነድ ከሆነ ወዲያውኑ የተጠቃሚው ኮምፕዩተር በተባይ ሊለከፍ ይችላል። ኮምፕዩተሩ ለስለላ የተመቻቸ ሊሆን ይችላል። ከእውነተኛ አድራሻና ታማኝ መስለው ቀርበው የግል መራጃንም የሚጠይቁ አሉ። ለዚህ ሁሉ ተጠቃሚው መጠንቀቅ አልበት እንጅ ዝም ብሎ የግል መረጃ በጭራሽ መስጠት የለበትም። እዚህ ጋ ተጠቃሚው እራሱን መጠበቅ ከፈለገ ያልታወቀና ያልተጠበቀ ወይም ጥርጣሬ ያለበትን መልክት መክፈት ወይም ምላሽ መጠት የለበትም። አንዳንድ ሰወች ኮምፕዩተራቸው ከተለከፈ ወይም መለከፉን ሲጠራጠሩ አዲስ ኮምፕዩተር መግዛት ከችግራቸው የሚያድናቸው ይመስላቸዋል። ዞሮ ዞሮ ኮምፕዩተሩን የሚጠቀምበት ሰው ባህሪው ያው እስከሆነ ድረስ ጉልቻ ቢቀየር ወጥ አያጣፍጥም። ያንኑ የተለከፈውን ኮምፕዩተር እንደገና አዘጋጅቶና ገንዘብም ቆጥቦ መኖር ይቻላል።

ንተርኔት መቅዘፊያው ቅድሚያ ዝግጅት ካልተደረገለት ለምሳሌ የጂሜይል ማለፊያ ቁልፉን ላስታውስልህ ወይ ብሎ ሊጠይቅ ይችላል። ተጠቃሚው በስንፍናም ይሁን ባለማወቅ "አወ" ብሎ ከመለሰለት በሚቀጥለው ጊዜ በቀጥታ ይገባል። ተጠቃሚው ይህን በሚያደርግ ጊዜ ማለፊያ ቃሉ በማን እንደታየ መቆጣጠር አይችልም። ኮምፕዩተሩን በማይጠቀሙበት ጊዜ ደግሞ ከገቡበት ሳይወጡ (ሎግ አውት) ሳያደርጉ የሚተውም አሉ። ኮምፕዩተሩንም ሲርቁ ሳይወጡ ወይም ሳይዘጉት የሚሄዱ አሉ። ሰው ቤቱን ከፍቶ ወደ ገበያ አይሄድም!! ይኸ ሁሉ አመላቸው እንዲጠቁ ያደርጋቸዋል። ለነገሩ የግል ኮምፕዩተራቸውን በተመለከተ ሰወች ያጠቃቀም ባህሪያቸውን ካሳመሩ አንቲቫይረስ / antivirus እንኳን ላያስፈልጋቸው ይችላል። ከሁሉም በላይ ግን ሰወች ሊኑክስ እንዲሞክሩ እመክራለሁ። ሊኑክስን ለመውደድ ቀላል ነው። ለወደፊት ስለ ሊኑክስ ካለፈው ሁለተኛው ክፍል ኦፕሬቲንግ ሲስተ ሌላና ተጨማሪ ማብራሪያ እሰጣለሁ።

ሆኖም ግን የሚቀጥለው ክፍል ላይ ስለ አንቲ ቫይረስና ፋየርወል አስረዳለሁ።

እንደዚህ ተከፋፍሎ በቅደም ተከተልና በመልኩ ስለቀረበ አንባቢወች እንደሚወዱትና እንደሚከታተሉ ተስፋ አለኝ።

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ