
ተወጥቶ ተወርዶ የትም ሀገር ቢኖር፣
አገርቤትም ሆነ ከባህር ባሻገር፣
ጉድለት አለ ሲባል ሥሰማ ሲነገር፣
ብዙ ያገሬ ሰው ቃሉን ሳያከብር፣
እቅድ ሳያወጣ ባጋጣሚ መኖር፣
እንዲህ የገነነ አይመስለኝም ነበር፡፡
ስማችን አይጥፋ በቀጠሮ ምክንያት፣
እስኪ በቃ ብለን ዛሬ እንነሳበት፣
በሰዓቱ እንድረስ ቃል ለገባንለት፣
ቶሎ ሳንዘገይ በተባለው ሰዓት፣
ከዛ ከተባለው ቦታ ለመገኘት፣
ለቀጠርነውም ሰው ክብር ለማሳዬት፣
በደንብ ተገንዝበን የቀጠሮን ክብዴት።
በሰዓቱ መድረስ እንደምን አቃተን?
እስከመቼ ድረስ ሁልጊዜ ዘግይተን፣
በትንሿ ነገር ካልተለማመድን?
ነጻነትና እድገት መቼ እናገኛለን?
ይህን ገጽ ለጓደኞችዎ ይንገሩ!
- 13585 reads
Comments
ሰላም ፋንታው
ሰላም ፋንታው
ኣሁንም ጥሩ መለክት ኣስተላልፈሃል። ብእውነቱ ያለህን እውቀት ለማካፈል እና ሌሎቻችንም መመርያ እንዲንከተል ለማበረታት የምታደርገው ጥረት እጅግ የሚደነቅ ነው።
እንበርታ! ከኣርጋው
አመሰግናለሁ አርጋው! //ፋንታው
አመሰግናለሁ አርጋው! //ፋንታው
መልካም ነገር ሁሉ ሲያዩት ደስ ያሰኛል
መልካም ነገር ሁሉ ሲያዩት ደስ ያሰኛል
እንዲህ ያለ መረብ ከወዴት ይገኛል?
በርታ ቀጥል ብልህ በጣም ደስ ይለኛል፡፡
ለድጋፍህ አመሰግናለሁ አዲሱ! ግጥሙም አሪፍ
ለድጋፍህ አመሰግናለሁ አዲሱ! ግጥሙም አሪፍ ነው፡፡ //ፋንታው
i like it
i like it
አዲስ አስተያየት ይጨምሩ