You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ከፖለቲካ ነጻ ነኝ የሚሉ ሰወች ምን እየተሰማቸው ይሆን?

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Wed, 10/02/2013 - 19:16

ንደ ኢትዮጵያ ዲክታተር ባለበት ሃገር ውስጥ ፖለቲካና ሃይማኖት የጥቂት ሰወች መጠቀሚያ ነው፡፡ ፖለቲካ ሲሆን ተጠቃሚወቹ ሰፊውን ህዝብ ያስገድዳሉ፡፡ ሃይማኖት ሲሆን ደግሞ ሰፊውን ህዝብ በእምንቱ እንዲፈራ ወይም ጭንቅላቱን አጥበው ጸጥ እንዲል ያደርጉታል፡፡ ከሁለቱም ወገን ሆኖ ደግሞ አጫፋሪ አለ፡፡ አያገባኝም ብሎ የሚተውና ዝም የሚልም ጥቂት አይደለም፡፡ አብዛኛው የኢትዮጵያ ህዝብ የሚበደለው ዝም ስለሚል ነው፡፡ ፖለቲካ አያገባኝም ቢልም ዞሮ ዞሮ ህይወቱ የሚወሰነው በፖለቲካ ነው፡፡ እሱ ግን ፖለቲካ አያገባኝም ስለሚል ሁል ጊዜ ተገዢ እንጂ ተካፋይ አይደለም፡፡ ውኃ ስለቀጠነ ፖለቲካ ነው ማለትም ትርጉሙን ያሳጣዋል፡፡ ዞሮ ዞሮ የጥቂት ሰወች ክፋት ህይወቱን እንዳናጋው ቢያውቅም ችሎ ዝም ይላል፡፡ ወይ አይታገል፤ ወይ አይመርጥ፡፡ ለነገሩ ነው እንጅ ምርጫ የሚኖረው ከትግል በኋላ ነው፡፡

ግል ማለት ደግሞ፤ በጋራ ሲሆን ሃገርና ወገን ጥቃት እንዳይደርስበት በማንኛውም መንገድ አብሮ መታገል ሊሆን ይችላል፡፡ በግል ጉዳይ ሲሆን ደግሞ ባህሪን ለማሳመር መታገል ሊሆን ይችላል፡፡ ሰው ሃገሬና ህዝቤ ላይ በደል አይድረስ ማለት ፖለቲካ የሚመስላቸው ብዙ ኢትዮጵያውያን አሉ፡፡ የሚበደሉት ግን እራሳቸው ናቸው፡፡ ነጻ አለመሆናቸውን ያውቁታል ወይስ አያውቁትም ለማለት ለኔ በጣም ያስቸግረኛል፡፡ የሚያስብና የሚቆረቆረው ግን ቢያንስ አላማው እስከሚሳካ ድረስ ስለሚታገል ሁል ጊዜ የውስጥ እርካታ አለው፡፡ ለሃገሩና ለወገኑ ሲል አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ፡፡

ደ አርዕስቱ ስንመጣ አንዳንድ ኢትዮጵያውያን ደግሞ የሆነ ድርጅት ሲከፍቱ ወይም የሆነ ነገር ሲሰሩ ገና ሲጀምሩ ከፖለቲካ ነጻ የሆነ ብለው ያስተዋውቃሉ፡፡ ገና ሳይጠየቁ፡፡ አሁን ምን አለፋቸው፡፡ በራሳቸው ወይም በሚሰሩትና በሚያደርጉት ነገር ላይ ለምን ድንበር ያስቀምጡበታል? ለማንኛውም ኖርዌይ ውስጥ ያሉ ሃገር ወዳድ ጥቂት ኢትዮጵያውያን የሚከበሩትና እንደ ምሳሌ የሚጠሩት ፖለቲከኞች ሆነው ሳይሆን ሃገራችን ኢትዮጵያ ውስጥ ያለውን የወያኔን የግፍና ጭቆና ስርአት ለማስወገድ ከሚታገሉትና ከሚቃወሙት ጋር አጋር ስለሆኑ ብቻ ነው፡፡ በመጨረሻም በህይወት ውስጥ ዝም ማለት ያስንቃል መስራት ግን ያስከብራል፡፡

Comments

ባነሳኸው ሐሳብ ሙሉ በሙሉ እስማማለሁ። ስለፖለቲካ አብዛኛዉ ማህበረሰብ ያለዉ ግንዛቤ በጣም የተዛባ ነው። ፖለቲካን ለተወሰኑ ግለሰቦች ብቻ የመተዉ እና በነዚህ ጥቂት ግለሰቦች የሚወስኑት ፖለቲካዊ ዉሳኔወች የሚመስሉ ነገር ግን የያንዳንዱን ግለሰብ ኢኮኖሚያዊ ፣እና ማህበራዊ ጉዳዮችን የሚያናጉ ዉሳኔወች ሊሆኑ እንደሚችሉ የለማስተዋል ችግር ይታያል።

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ