You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ነጻነት ምንድነው? ነጻ መሆንዎን እንዴት ያውቁታል?

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Sat, 09/12/2009 - 21:21

ትዮጵያ ተነሺ ላይ ከሰራኋቸው ስራዎች ውስጥ በጣም የምወደው አርዕስት ነጻነትን ነው፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ ነጻ ካልሆነ ሰው መሆኑ ይቀንስበታል ብዬ ስለማምን ነው፡፡ ለምን እንደሆነ ለማወቅ እባክዎን የዚህን ገጽ ይዘት በሙሉ ተረጋግተው እንዲያደቡ አሳስባለሁ፡፡ ነጻነት ማለት ምን እንደሆነ የተለያዬ አተረጓጎም ሊኖረው ይችላል፡፡ ነጻ ለመሆን መብትና ግዴታ ባንድ ላይ የሚሄዱና የሚፈጸሙ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡

ሆኖም ግን ነጻነት ማለት በራስ መወሰን ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት እርስዎ ማንም ሳያስገድደዎት እና የማንንም መብት ሳይነፍጉ ብዙ ነገሮች ላይ በራስዎ ወይም በጋራ መወሰን ሲችሉ ነው፡፡ ደሞክራሲ ሊባልም ይችላል፡፡ የርስዎ ሃሳብ ወይም ተሳትፎ ተሰሚነት አለው ማለት ነው፡፡ ይህንን በተግባር ለመተርጎም እርስዎ መብትዎን ማወቅ ግዴታዎን ደግሞ መወጣት አለብዎት፡፡

መብትዎን እንዲያውቁና ግዴታዎንም እንዴት እንደሚዎጡ በራስዎ ላይ ያለዎት እምነትና ተግባርዎ ነጻ ለለመሆዎ በጣም ወሳኝ ነው፡፡ መብትዎን ካላወቁና ግዴታዎን ካልተዎጡ ነጻ መሆን አይችሉም፡፡

ብትዎን ካላወቁና ግዴታዎን ካልተዎጡ ነጻ መሆን አይችሉም፡፡ መብትዎ ስል እርስዎ፣ ወገንዎ፣ አገርዎ፣ ወዘተ እንዲኖርዎት የሚፈልጉት ወይም የሚዎዱት ነገር ሊሆን ይችላል፡፡ ግዴታዎ ደግሞ ያንን የፈለጉትንና የወደዱትን ነገር ለማግኘት የሚሰጡት ወይም የሚከፍሉት ዋጋ ነው፡፡ ለምሳሌ እርስዎ መከበርና መወደድ ከፈልጉ ሌሎችን በማክበርና በመውደድ ዋጋ መክፈል አለብዎት፡፡ ኢትዮጵያ እንዲታድግና እርስዎም እንዲሻሻሉና ጥሩ ዜጋ እንዲወጣዎት ከፈለጉ እንደተጠቀሰው በቋንቋ፣ በቀጠሮ፣ በጨዋነት በሚዛናዊነት፣ ስራ በመስራት፣ ወገንን በማክበር፣ ነጻነትዎን በሚነፍግ ነገር ላይ ቆራጥና ቆፍጣና ሆነው ነጻነትዎን በመንከባከብና በመጠበቅ ወዘተ ዋጋ መክፈል አለብዎት፡፡ ይህንን ካላደረጉ ሰው መሆንዎ ይቀንሳል፡፡ ስለዚህ ሙሉ ነጻ ለመሆን መብትና ግዴታ በአንድ ላይ ተጣምረው የሚሄዱና የሚፈጸሙ መሰረታዊ ጉዳዮች ናቸው፡፡ መብትዎን እንዲያውቁና ግዴታዎንም እንዴት እንደሚዎጡ በራስዎ ላይ ያለዎት እምነት በጣም ወሳኝ ነው፡፡ እንግድህ የሰው ልጅ ስለነጻነት ሊኖረው የሚገባውን እምነት እንዴት እንደሆነ አብረን እናያለን፡፡

የሰው ልጅ ገና ሲወለድ ድንቅና ቀና ስለሆነ ጎጂም ተጎጂም መሆን አይፈልግም፡፡ እያደገ በመጣ ቁጥር አስተሳሰቡ፣ ፍላጎቱ፣ ድርጊቱ ወዘተ ይለወጥና ለኔና እኔ ብቻ ማለት ይጀምራል፡፡ ታዲያ የሰው ልጅ መሰረታዊ መብቶች ይረሱና አንዱ ሌላውን እየጎዳና እያጭበረበረ መጠቀም ይፈልጋል፡፡

እኛ እራሳችንን እንደምንወደው ሁሉ ሌሎችም እራሳቸውን እንደሚወዱ ግን ብዙዎቻችን እንዘነጋለን፡፡

ንድ ሁላችንንም የማያከራክር ነገር ቢኖር የሰው ልጅ እራሱን ይወዳል፡፡ እኛ እራሳችንን እንደምንወደው ሁሉ ሌሎችም እራሳቸውን እንደሚወዱ ግን ብዙዎቻችን እንዘነጋለን፡፡ ሌሎችን ሳይጎዱ እራስን መውደድ መጥፎ አይደለም፡፡ ምክንያቱም የሰው ልጅ በተገቢው እራሱን ሲወድ እራሱንና ሌሎችንም ለመጥቀምና ለመርዳት ያስችለዋል፡፡ እኛ ኢትዮጵያውያን ግን ይባስ ብሎ እንኳን ሌሎችን ልንወድ ቀርቶ በግላችን እኛው እራሳችንን ለመውደዳችን ብዙ የሚያከራክሩ ጉዳዮች አሉ፡፡ አንደኛውና ትልቁ አደገኛ አመላችን ብዙዎቻችን ስለግል ነጻነታችን ያለን ግንዛቤና የግል ነጻነታችንንም ለማስከበር ምን ማድረግ እንዳለብን አናውቅም ወይም ችላ እንላለን፡፡ የግል ነጻነትን ማስከበር ማለት እራስን መጠበቅና መንከባከብ ማለት ሊሆን ይችላል፡፡ ሌሎችን ሳንጎዳ እራሳችንን ከተንከባከብንና ከጠበቅን እራሳችንን በተገቢው እንደምንወድ ይቆጠራል፡፡

1፤ ብዙ ሰዎች ስራ ኖሯቸው ሆዳቸውና ፍለጎታቸው በገንዘብና በቁሳቁስ ከሞላላቸው ነጻነታቸውን ችላ ይሉታል፡፡ አንዳንዶቹም በግርግር አንዳድ ጊዜ ፊታቸውን አሳይተው ወይም እርዳታ ሰጥተው በዛው እልም ይላሉ፡፡ ቋሚ ነገር የላቸውም፡፡

2፤ ሌሎች ደግሞ ጥቅም ካገኙ ወገናቸውንና አገራቸውን አሳልፈው ይሰጣሉ፡፡

3፤ የቀሩት ደግሞ ተሳትፎና ትብብር ሳያደርጉ የሚሰሩትን ለማሳሳት የጠለፋ ወሬ ያወራሉ፡፡

4፤ ቆራጦች ደግሞ የፈለገ ይሁን ነጻነታቸውን አሳልፈው አይሰጡም፡፡

ከ1 - 3 ከሰፈሩት ነጥቦች አንዷ እንኳን የምትመለከትዎት ከሆነ ሊያሳስብዎት ይገባል፡፡ በተለይ ግን ሁለተኛውና ሶስተኛው ነጥብ የሚመለከትዎት ከሆነ በመጀመሪያ ደረጃ ይህ አካሄድዎ ደስታ አይሰጥዎትም፡፡ ምን እያደረኩ ነው ብለው እራስዎን ከጠየቁ ብዙ መልሶች ያገኛሉ ብዬ አስባለሁ፡፡ አጣብቂኝ ውስጥም ገብተው ይሆናል፡፡ ሆኖም ግን በህይዎትዎ ውስጥ ብዙ ጥሩ ምርጫዎት አሉዎትና ከጎጂ ይልቅ ጠቃሚ ለመሆን እንደገና እራስዎን ይጠይቁ፡፡ የመጀመሪያው ነጥብ ብቻ የሚመለከትዎት ከሆነ የብዙ ሰዎች አይነት ችግርና አመለካከት አለዎት፡፡ ብዙ መጥፎ ነገሮች አለአግባብ ሲከሰቱ ስላዩ እኔ ሰላማዊ ነኝ፣ ሰላም እሻለሁ፣ አያገባኝም፣ እግዜር ወይም አላህ ያውቃል፣ ቤተሰቤን ላስተዳድርበት፣ ልጆቼን ላሳድግበት፣ ስራዬን ልስራበት፣ ትምህርቴን ልማርበት፣ ፈርቻለሁ፣ ያመንኳቸው ከዱኝ፣ ሁሉም ለራሱ ጥቅም ብቻ ነው የሚሯሯጠው፣ አገሬንና ወገኔን እወዳለሁ ግን ሰዎች አይቀየሩም፣ ብዬ ብዬ ታክቶኛል፣ ወዘተ እያሉ ተበሳጭተውና ውስጥዎ እያረረ ተስፋ ቆርጠው ነጻነትዎን ችላ ብለውት ወይም አጋጣሚ እየጠበቁ ሊሆን ይችላል፡፡

ያ ከሆነ እባክዎን ተስፋ አይቁረጡ ወደ ነጥብ አራት ለመቀላቀል የተቻለዎትን ያድርጉ፡፡ ይተባበሩ፡፡ በግልጽም መውጣት ካልፈለጉ ብዙ አይነት የትግል ምርጫወች አሉ፤ ለምሳሌ የነጻነትን መንፈስ ለሌሎች ማሰማትና እንዲነቁ ማድረግ፣ እርስዎ የተመቸዎትንና የመረጡትን የድጋፍ አይነት መስጠት ወዘተ፡፡ መቼም ዝምተኛና ገለልተኛ ሆነው ከቆዩ ነጻ እንደማይሆኑ እርስዎም ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ ከተባበሩ ትብብርና አንድነት ሃይል ስለሆነ ነጻነትዎ እሩቅ አይሆንም፡፡

ሁን እርስዎ ነጻ ለመሆን የበለጠ ፍላጎትዎና ትብብርዎ እንዲጨምር አንዳንድ ማበረታቻ የሚሆኑ ሀኔታዎችን እጠቅሳለሁ። በመጀመሪያ ደረጃ አንድ ሰው ስለ ነጻነት በቅጡ የሚረዳው እራሱን ከራሱ ጋር ማስታረቅ ሲችል ነው፡፡
ከላይ እንደጠቀስኩት እርስዎ በራስዎ ላይ ያለዎት እምነት ለግልዎ ነጻነትና ደስታ፤ ከዛም ለወገንዎና ለኢትዮጵያችን ነጻነትና እድገት ወሳኝ ነው፡፡

በውስጥዎ ነጻነትን ለማዳበር ታዲያ እኔ ጥሩ ሰው ነኝ፤ ጥሩ ነገር እናገራለሁ፤ ጥሩ ነገር በተግባር በማድረግ አምናለሁ፤ አደርጋለሁም፤ መብትና ግዴታየን ጠንቅቄ ስለማውቅና ለመተግበርም ወደኋላ ስለማልል ነጻ ነኝ ብለው በራስዎ ሲተማመኑ ወይም ሲያምኑ ብዙ ጥሩ በሮች ይከፈታሉ፡፡ ይህ ስሜት አስበውና ተሰምቶዎት ከውስጥ የመነጨ መሆን አለበት፡፡ በህይዎተዎ ላይም ምን መሆንና ማድረግ እንደሚፈልጉም ማወቁ በራስዎ ላይ ጥሩ እንዲሰማዎት ይረዳዎታል፡፡ ይህ ጥሩ ስሜትና እምነት እንዲዳብርልዎት ባጋጣሚው ሁሉ በማሳየት መለማመድና መደጋገም አለብዎት፡፡ ልምምዱና ድግግሞሹም ስለ ነገሮችና ጉዳዮች ከአሁኑ የበለጠ ብልህና ጥሩ ሰው እንዲሆኑ ይገፋፋዎታል፡፡ ይህ ሁኔታ በራስዎ ነጻ ስለሞሆንዎ ምልክት ነው፡፡

ይይህ ከውስጥ የሚመነጭ ጥሩ እምነትዎ በተግባር በሚታይ ጊዜ ባካባቢዎ፣ በወገንዎ ወይም ባገርዎ ላይ ተጽዕኖ ሊያደርግ ይችላል፡፡ ሆኖም ግን እርስዎ በዚህ አቋምዎና ዕምነትዎ ደፋር፣ ጠንካራና ጽኑ መሆን አለብዎት፡፡ እምነትዎ ወደ ውንነት በሚተረጎም ጊዜ ያለሙትና የሚፈልጉት ነገር እውን ይሆናል፡፡ በርግጥ ማንም ሰው ፍጹም ባይሆንም እርስዎ ግን ወደ ፍጹምነት በሚጠጉ ጊዜ ነጻነትዎና ደስታዎ ይጨምራል፡፡ የሚፈልጉትንም ነገር ለማግኘት ብዙ በሮች ይከፈታሉ፡፡ ይህ በጥቅሉ ስለነጻነትዎ ከውስጥ የሚሰማዎት ስሜት ወይም እምነት ነው፡፡ በርግጥ አንዳንድ ነገሮች አንዳድ ጊዜ ከቁጥጥር ውጭ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ እርስዎም እንደሚያውቁት ማንኛውም ነገር መፍትሄ ስላለው እርስዎ በጥሩ እምነትዎ ጸንተውና ቆርጠው መፍትሄ ለማግኘት መስራትና በጋራ ጉዳይ ላይ መተባበር እንጂ ለችግሮች እጅ መስጠት፣ ጊዜ መስጠት ወይም ችላ ማለት የለብዎትም፡፡

ህንን ነጻነትዎን እንዴት ማስፋፋትና መከላከል እንደሚችሉ ቀጣዮቹን ማብራሪያዎች እባክዎን ያንብቡ! ኢትዮጵያ ማደግ ትችላለች? አዎን፥ በደንብ ትችላለች፡፡ እንዴት ማደግ ትችላለች? ባህሪያችን ሲስተካከል፡፡ ኢትዮጵያስ ጥሩ አገር ነች? በሚገባ፥ አዎ ነች፥
ምክንያቱም የሰው ባህሪ እንጂ የአገር መጥፎ የለውም፡፡ ኢትዮጵያስ በማን ጥረት ማደግ ትችላለች? በኛ በኢትዮጵያዊያን፡፡ ሁሉም ኢትዮጵያዊስ እንዴት ነጻ ሊወጣ ይችላል? እያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ከራሱ ጋር ሲታረቅና በአንድነት አምኖና ነቃ ብሎ ኋላቀር አስተሳሰቡን በአዲስና በገንቢ አስተሳሰብ ሲተካው!! ይህንን እንዴት ማድረግ ይቻላል? እባክዎን ማንበብዎን ይቀጥሉ፡፡

የሃገር መጥፎ የለውም! የአንዲትን አገር ዜጋ ነጻነት ጥሩና መጥፎ የሚያደርገው የዜጎቿ አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡

የአንዲትን አገር ዜጋ ነጻነት ጥሩና መጥፎ የሚያደርገው የዜጎቿ አስተሳሰብና ድርጊት ነው፡፡ ባጠቃላይ ያገሪቷ ዜጋ የባህሪ ውጤት ነው ሊባል ይችላል፡፡ ታዲያ እኛ ኢትዮጵያዊያን ለሁላችንም የሚጠቅምና ለአገራችንም ጥሩ ስም የሚያሰጣትን ነገር በተግባር ለማሳየት ጥረት ማድረግ ያስፈልገናል፡፡ ይህንንም ተገቢ ለውጥ የምንጀምረው 'ነጻነት ምንድነው?' ከሚለው ጽሁፍ ላይ በዝርዝር እንዳብራራሁት በውስጣችን ጎበዝ፣ ጠቃሚና ጥሩ ሰው ለመሆን በራሳችን ላይ እምነት ማዳበር ስንችል ነው፡፡ አሁን ያንን እምነት በተግባር እንዴት መተርጎም እንደሚቻል በሚቀጥሉት ጽሁፎች በቀላሉ አስረዳለሁ፡፡

ከልዩነታችን ይልቅ ተመሳሳይነታችን በጣም የቀረበ ነው፡፡ ነገር ግን በቀላል ነገሮች ላይ ልዩነት ፈጥረን ብዙ ጊዜያችንን፣ ዕውቀታችንንና ሃይላችንን መጠቀም የለብንም፡፡ ተመሳሳይነታችን የበለጠ ይቀርባል፡፡ ለምሳሌ የጋራ አገር አለን፡፡ የጋራ ታሪክ አለን፡፡ የጋራ ሰንደቅ አላማ አለን፡፡ የጋራ የተፈጥሮ ሃብት አለን፡፡ ኢትዮጵያ የብዙ ብሄረሰቦች መኖሪያ ቤት ነች፡፡ የሁላችንም ነች፡፡ ምግብም የሚርበን በስንፍናችን ምክንያት እንጂ ምግብ ጠፍቶ አይደለም፡፡ የምንጣላውም ባለማስተዋል ምክንያት እንጂ ሰላም ጠፍቶ አይደለም፡፡ ያለውን ሰላም እንዴት አድርገን መጠቀም እንደምንችል በቂ እውቀት ማዳበር ያስፈልገናል፡፡ እንዴትና ከምን ተነስተን ማደግ እንደምንችል ታታሪው አቅጣጫውን ይጠቁማል፡፡ እርስበርስ በመከባበርም ያሉን ቋንቋዎች፣ ባህሎች እንዲሁም አገራችን ኢትዮጵያም ማደግ እንደምትችል ፅኑ እምነት እንዲያድርብን ያስፈልገናል፡፡

ለተንኮል የምንጠቀምበትን እውቀት፣ ጊዜና ሃይል ለልማት፣ ለትብብርና ለመከባበር ብናውለው ኢትዮጵያ ማደግ ትችላለች፡፡ ሁላችንም የዚህ አይነት እምነት ካደረብን የማንሻሻልበት ምክንያት የለም፡፡ ሁላችንም ጥሩ ባህሪ ኖሮን በተለያየ መልኩ ማመዛዘን ከቻልን፥ እንኳን ኢትዮጵያ ቀርታ አለምም አንድ መሆን ትችል ነበር፡፡ የጋራ አገር፣ ታሪክ፣ የተፈጥሮ ሃብት ወዘተ እንዳለን ሁሉ ለኢትዮጵያና ለራሳችንም ጭምር የሚጠቅም የጋራ የሆነ መልካም ባህርይ በእጅጉ ማዳበር ያስፈልገናል፡፡ ይህም የጋራ የሆነ ባህርይ የሚያስፈልገን አገራችንን ለመውደድና እርስበርስም ለመከባበር እንድንገለገልበት ነው፡፡ ታዲያ ተከባብረን በተመሳሳይነታችን ካተኮርን ኢትዮጵያ ያለጥርጥር ማደግ ትችላለች፡፡ ኢትዮጵያም የምትፈልገው ይህንን ነው፡፡ ኢትዮጵያ ይህንን ለምን እንደምትፈልግና እኛም የሚያስፈልገውን ነገር እንዴት እንደምናደርግ ባጭሩና በቀላሉ እጠቁማለሁ፡፡

ኢትዮጵያ ይህንን ለምን ትፈልጋለች? ከፈለገችስ ምን ማድረግ አለብን? ኢትዮጵያ መቼ ነው ማደግ እምትጀምረው? ብለው ሊጠይቁ ይችላሉ፡፡
እርሰዎ "ጨዋ ማን" የሚለውን ሁሉንም ክፍል አንብበው በእርስዎ ላይ ለውጥ ከጀመሩ ኢትዮጵያ ዛሬውኑ ማደግ ትጀምራለች፡፡ ኢትዮጵያ ገና ጥሬ ነች፡፡ አሁን ባለንበት የዕውቀት ደረጃ የማናውቀው ብዙ ጠቃሚ ጥሬ ሃብት ለሁላችንም ልትሰጠን ትችላለች፡፡ በደንብ መያዝ ያለብን የወረስናቸው ታሪካዊ ቅርሶች አሉን፡፡ ታሪካዊ ቦታወች አሉን፡፡ በአመት ከሁለት እስከ ሦስት ጊዜ ድረስ የሚለማ መሬት አለን፡፡

ኛ ደግሞ የተለያዩ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤዎች አሉን፡፡ ይህ እራሱን የቻለ ፀጋ ነው፡፡ እውቀታችንን ለማዳበርና ሰላም ለመፍጠር ባህላችንን እርስበርስ መማማርና መንከባከብ ያስፈልገናል፡፡ ነገር ግን በጣም ብዙዎቻችን ሁኔታዎችን አመዛዝኖ ጠቃሚነታቸውን ለማወቅ ያለን ዕውቀት ውስን በመሆኑ ይህ ፀጋ ለምን እንደሚጠቅም በግልጽ አይታየንም፡፡ በአፍ ብቻ ብዙዎቻችን ኢትዮጵያዊያን ነን እንላለን፡፡ ተግባር ላይ ሲሆን ግን ኢትዮጵያዊነታችንን የሚያፈርሱ ነገሮችን እናደርጋለን፡፡ ለምሳሌ በቆዳቸው ቀለምና በባህላቸው ለየት ያሉትን ኢትዮጵያዊያን ወገኖቻችንን በተግባር ቀርቶ ባስተሳሰባችን እንኳን መጨቆን የለብንም፡፡

እነዚህ በርካታ ቋንቋዎች፣ ባህሎችና የአኗኗር ዘይቤዎቻችን ለፈጠራ ችሎታችን ማዳበሪያ እጂግ በጣም ጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ይህ ማለት ታዲያ ሁላችንም የተለያዩ ችሎታዎችና ተሰጣኦ ስላለን ለፈጠራ ችሎታችንና እርስ በርስ ለመማማር ያበረታታል፡፡ ሁላችንም በየፊናው በሰላምና በመከባበር በተገቢው ከሰራን አገራችን ኢትዮጵያ ማደግ ትችላለች፡፡ የማደግ መቻሉም እምነት በልባችን ውስጥ እንዲያድር ያስፈልጋል፡፡

Comments

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ