You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ማንነት ከሞላ ጎደል፤ ማን ነኝ ብለው ያውቃሉ?

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Tue, 03/01/2011 - 10:08

ህይወት ላይ አርኪና ተቀባይነት ያለውን ነገር ለማድረግ ብዙ ቀላልና ከባድ ነገሮች ሂሳብ ውስጥ ይገባሉ፡፡ ታዲያ እንዳው አልፎ አልፎ እኔ ማነኝ? የማደርጋቸውን ነገሮች የምጠቀምበት ስልት ምን ይመስላል? ምን እያደረኩ ነው? ብለው እራስዎን ጠይቀው ያውቃሉ? ማን ነዎት? የዚህ አርዕስት አላማ እርስዎ ሰው እንደመሆንዎ መጠን በነገሮች ላይ ያለዎት አስተሳሰብና ድርጊት ምን እንደሆነ መርምረው እራስዎ እንዲደርሱበት ፍንጭ ለማሳየት ነው፡፡ እርስዎ በራስዎ ማንነትዎን በሚያስቡትና በሚያደርጉት ነገር መሰረት በማድረግ ማን እንደሆኑ በራስዎ እራስዎን እንዲጠይቁ ታስቦ ነው፡፡ እነዚህ አስተሳሰቦችና ድርጊቶች ህይወት ላይ ከፍተኛ ቁርኝት ስላለቸው ከታች የተጠቀሱትን ነጥቦች ሲያነቡ አረፍ እያሉ እንዲያስቡበት እጠይቃለሁ፡፡

ተጠቀሱት ነጥቦች ቀላልና በቀላሉ የሚታለፉ ሊሆኑ ይችላሉ፡፡ ዋናው ቁምነገር ግን ቀላሎቹ ነገሮች በሚከሰቱ ጊዜ በትክክልና በተገቢው ካልተደረጉ በቂ ልምምድ ስለማይኖር ከፍ ያለ ቁምነገር ለማድረግ ያዳግታል፡፡ አንዳድ ሰዎች ከበሉና ከጠጡ፣ ስራም እንደነገሩ ሰርተው ከተመልሱ፣ ከዛም ባገኟት ገንዘብ ለምግብ፣ ለልብስ፣ ለቤተሰብ፣ ለቤትና ለመሳሰሉት ከበቃቸው ህይዎት ከዛ በልይ መሆኗን ይዘነጋሉ፡፡ ለማለት የፈለኩት ታስቦበትም ይሁን ባጋጣሚ የሰው ልጅ በተቻለ መጠን ህይወት ውስጥ በሚከሰቱ ነገሮች ላይ ተገቢውን ውሳኔ መወሰንና ማድረግ አለበት፡፡ አይ ይቺማ ምን አላት ብሎ ማለፍና መናቅም እንደ እጅ መስጠት ሊቆጠር ይችላል፡፡
እርስዎም እንደሚያውቁት ሰው ፍጹም አይደለም፡፡ ሆኖም ደግሞ ከዚህ በታች የተጠቀሱት ነጥቦች በተቃራኒው ከተደረጉ ቢያንስ ህይወት እንዲጥምና እርካታ እንዲኖረው አስተዋጽኦ ያደርጋሉ፡፡

ለቀጠሮ ቁርጥ አድርጎ ወዲያውኑ ቀጠሮ እንደመያዝ እንደዋወል ይላሉ?
ባጋጣሚ በቀጠሮ ዘግይተው የት እዳሉና መቼ እንደሚደርሱ ከመናገር ይልቅ እየመጣሁ ነው ይላሉ?
ሲያዳምጡ፣ ሲናገሩና ሲያስቡ ፊትዎ ይቋጠራል?
ሃሳቦች ሲቀርቡ በአፍራሽነት መልኩ ግን ማለት ያበዛሉ?
ሳያጣሩ በሃሜት አምነው ይወስናሉ?
ሻይ ቤት ውስጥ ተቀምጠው ለበርካታ ሰዓታት በወሬ ጊዜዎን ያባክናሉ?
ስለ ሌላ ሰው ማውራትና ማማት ያዘወትራሉ?
ስራዎን ለደመወዝ ነው ብለው ያስባሉ?
ጓዴኛ ወይም የቅርብ ቤተስብ ጋር በተደጋጋሚ ይጨቃጨቃሉ?
ለሚስትዎ ወይም ለባልዎ ታማኝ አይደሉም?
ለትንሽም ሆነ ትልቅ የሚደረግ ነገር ላይ እጅ ይሰጣሉ?
ኢትዮጵያዊ ሆነው ከልብ ኢትዮጵያዊነት አይሰማዎትም?
ጥራት ያለው ነገር ሲያዩ ወይም ተካፋይ ሲሆኑ አያደንቁም?
ቶሎ ቱግ ብለው ይናደዳሉ?
የሆነ ነገር ለማድረግ ይህንን አልችልም ብለው ችሎታዎን ባጭሩ ይገቱታል?
ሲጋራ ያጨሳሉ? ጫት ይቅማሉ?
በየአጋጣሚው ከልክ በላይ ይጠጣሉ? ጠጥተውስ መኪና ይነዳሉ?
ገንዘብና ቁሳቁስ ደስታ የሚሰጥ ይመስልዎታል?
ጓደኞችዎን ወይም የሚያውቋቸውን የሚያስታውሷቸው እርስዎ እርዳታ ሲፈልጉ ብቻ ነው?
እከሌ ወይም የሚጠላኝ ሰው አለ ብለው እራስዎን ይጠራጠራሉ?
ብዙውን ጊዜ እርካሽ ነገር ከሱቅ ይገዛሉ?
በቀላሉ መደሰት ጥሩ ቢሆንም ይረካሉ?
አጥፍተው ይቅርታ አይጠይቁም? ወይም ሳያጠፉ በፍራቻ ወይም በይሉኝታ ይቅርታ ይጠይቃሉ?
ማንነትዎን ደብቀው ያለምንም ምክንያት ኢሜል ይልካሉ? ፈሪ ነዎት?
ሰልፍ ላይ ተራዎን ሳይጠብቁ ወይም ቀድመው ሳይመጡ ዘው ብለው መስተንግዶ ይፈልጋሉ?
ዝግጅት ኖሮዎት ማስታወቂያ ሲያዎጡ አድራሻ፣ ሰዓትና ዋጋ ይረሳሉ ወይም ይደብቃሉ?

ለቅርብ ጓደኞችዎም ቢሆን በጅምላ እንኳን አደረሳችሁ ብለው SMS ይልካሉ?
ነጻ አይደለሁም ብለው ካሰቡ ነጻ ለመሆን እርምጃ አልወሰዱም?
ነጻ ነኝ ብለው ካመኑስ ነጻነትዎን ለራስዎ ብቻ ይዘው ዝም ብለው ቁጭ ብለዋል?

Comments

It is always nice to know that you hold on to your unique way of doing things. The points you mentioned are moralistic and reflect your own thoughts about what is wrong with other people. I am sure many share your views on what is wright and wrong. They may not follow them strictly on a daily basis. My only comment is that try to have a structure on the points you mentioned. You need to put them under sutitles or sub-points that are comprehendible.

Otherwise, I admire, as usual your resoluteness, clarity and decisiveness in your approach to life.

Good luck with Tatariw

Tewasen

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ