You are here

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ኢትዮጵያውያን እንብላ እንደምንለው ሁሉ እንስራስ ማለት እንወዳለን? አይመስለኝም! አሁን ያለንበት ሁኔታ ምስክር በአካልና በአዕምሮአችን ስለማንሰራ ነው፡፡ ጉድ ፈላ!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

መሰረታዊ የአስሊ ዕውቀት፡፡ የአስሊ አጠቃቀም አጉል ባህሪ ካለወት አስሊወ በቫይረስና በሰላዮች ይጠቃል፡፡ ርካሽ ወይም ነጻ የሆኑ ጥሩ አማራጮችን ያውቃሉ?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ብቃትዎ ምን ያውቃሉ? ለምሳሌ ስለ እልህና ንዴት፤ ወድቆ መነሳት፤ ነጻነት፤ መምራትና መግባብት ወዘተ፡፡ ማሰብ፣ መናገርና ማድረግ መተው ዝምታ ነው!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

ስለ ባህሪዎ ምን ያውቃሉ? ቀላል ነገሮች ላይ ይሳሳታሉ? ለምሳሌ በቀጠሮ መዘግየት፣ ቋንቋ መቀላቀል፣ ከማዳመጥ ይልቅ ብዙ ማውራት፣ እምነትዎስ ነካ ነካ ነው?

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

የሚያልሙትን ስራ አግኝተው ለማቆየት ስልቱን ያውቁታል? በስራ አለም ውስጥ የተጻፉና ያልተጻፉ ህጎችን ልብ ካሉ በስራዎ ለመደሰት፣ ለማደግና ለመርካት ይረዱወታል!!

Tatariw Amharic website Ethiopia wake up

በቀላሉ እራስዎን ይንከባከባሉ? የሚበላ ምግብ፣ የሚጠጣ መጠጥና የሚታሰብ ሃሳብ ወደ ሰውነታችን ስለሚገባ ህይወታችን ውስጥ ሚና አለው፡፡ ለምን?

1
2
3
4
5
6

ዮቲዩብን ቪደወ ያለ ሽቦ ቴሌቪዢን ላይ ለማየት፤

tatariw's picture
Submitted by tatariw on Thu, 01/16/2014 - 18:21
Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema

ህንን ዘዴ ከዚህ በፊት ያልጠጠቀሙበት ከሆነ አሁን መጠቀም ይችላሉ፡፡ ስማርት ቴሌቪዥን ካለዎት ያለ ምንም ሽቦ ማያያዢያ ከላፕቶፕ/ታብሌት ወይም ከእስማርት ስልክወ የዩቲዩብ ቪደወ ማየት ይችላሉ፡፡ ቴሌቪዥኑ ግን ከ ላፕቶፕ/ታብሌት/ስልክ ጋር መዛመድ አለበት፡፡ ቴሌቪዥኑ ኢንተርኔት ውስጥ ለመግባት የሚያስችል መሆንም አለበት፡፡ የዚህ ዘደ ከፍተኛ ጥቅሙ ከዝምድናው በኋላ የዩቲዩብን ቪደው ለማየት ቀጥታ ኢንተርኔት ላይ እንጂ ከላፕቶፕ/ታብሌት/ስልክ ላይ አይተላለፍም፡፡ ይህ ማለት ላፕቶፕ/ታብሌት/ስልኩን ለማዘዢያ ብቻ ለመጠቀም ነው፡፡ መመሪያው ከዚህ እንደሚከተለው ነው፡፡

ፎቶው ላይ ቀስቱ እንደሚያሳየው "ዩቲውብ" ምልክት ቴሊቪዢኑ ላይ ይጫኑ፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
ለማዛመድ ቀስቱ የሚያሳየውን ተመሳሳይ ምልክት ቴሊቪዢኑ ላይ ይጫኑ፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
ቀስቱ እንደሚያሳየው የማዛመጃውን መለያ ቁጥር ቴሌቪዢኑ ያሳይወታል፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
በላፕቶፕ/ታብሌት/ስልክ ስእሉ ላይ በሚታየው አድራሻ በመግባት መለያ ቁጥሩን መጻፊያ ቦታ ያገኛሉ፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
መጀመሪያ ቀስት 1 የሚያሳየውን የቴሌቪዢን ምልክት ጠቅ ያድርጉ፡፡ ከዛ በኋላ ቀስት 2 የሚያሳየውን YouTube TV የሚለውን ይምረጡ፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
ቀስቱ የሚያሳየው ቀይ ምልክት ቪደወው ወደ ቴለቪዢኑ መላኩን ለማሳየት ነው፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesemaአሁን ቀስቱ የሚያሳየው ቪደወው ቴሌቪዢኑ ላይ እየታየ ነው፡፡

Ethiopia Wake Up Tatariw Ethiopia attitude Addis Ababa Amharic Fantaw Tesema
መልካም እድል፡፡ ምናልባት ካልሰራለወት እንደገና ነጥቦቹን ተመልሰው በትክክል ይከተሉ፡፡ ተጨማሪ መረጃ ከፈለጉ የጉግለ እርዳታ አለ ፡፡

Comments

በጣም ጥሩ አገልግሎት እየሰጠ ያለ ድህረ ገጽ ነው። ኢትዮጵያዊው ሊያውቀው የሚገባና በተለያየ ምክንያት ሊያውቀው ያልቻለውን/ያላወቀውን ነገር እየዳሰሳችሁ ማሳወቅ መሞከራችሁ እጅግ ደስ የሚልና የተቀደሰ ሃሳብ ነው። ይህን ካልኩ በኋላ አንድ የቃል እርማት ባደርግ ለስራችሁ መቃናት የበኩሌን እገዛ እንዳደረኩ እቆጥረዋለሁና እንሆ፡፟ Smart TV የሚለውን የእንግሊዘኛ ቃል ወደ አማርኛ ስትመልሱ የተጠቀማችሁት ቃል "ብልጥ" የሚል ነው፡፤ እንደሚመስለኝ ግን የግድ አማርኛ ቃል ይተካ ከተባለም መሆን ያለበት "ብልህ" እንጂ ብልጥ አይደልም። ብልጥ ኔጌቲቪቲ ትርጉምም ይሸከማል። ብልጥ አስተዋይ ማለት ላይሆን ይችላል፡፤ ብልህ ግን ሙሉ ለሙሉ ፖስቲቭ ትርጉም የሚሸከም ቃል ነው። እንደነዚህ አይነት ቃሎች ብዙ ግዜ ወደ አማርኛ ከመመለስ ይልቅ እንዳሉ ብንጠቀማቸው ይሻላል፡፤ አለበለዚያ የትርጉም መፋለስ ያስከትላሉ። በተረፈ እጅግ በጣም በጣም ድንቅ ስራ ነው። ስማችሁም በርግጥ ይመጥናችኋል። በርቱ!

ሰላም!
ለእርማትና ለምክር አመሰግናለሁ። በዚህም ደስ ብሎኛል። ልክ ነው፤ ያላስፈላጊ ትርጉም የትርጉም መፋለስ ያስከትላሉ። አሁን ስማርት ቴሌቪዥን/ወዘተ በማለት አስተካክያለሁ። ለእርዳታዎም እንደገና አመሰግናለሁ።
ከሰላምታ ጋር! //ፋንታው

አዲስ አስተያየት ይጨምሩ