መነሻ ስለ መጀመሪያ የጽሁፍ ምድቦች መሰረታዊ ኮምፕዩተር ሀሁ - Learn Fidel መሆን የተካነ ባህሪ ያስተሳሰብ ጀግና የተለያዩ ግጥሞች ቪዴዎና ዝንባሌ

jegna Ethiopia Amharic Tatariw jegnye Addis Ababa Fantaw Tesema
jegnaye Ethiopia Amharic Tatariw jegna mejemeriya Addis Ababa Fantaw Tesema

እንኳን ወደ ልዩ ጣቢያ መጡ!


ንታው እባላለሁ፡፡ ኢትዮጵያ እንዴት ብላ ማደግ ትችል ይሆን እያሉ አስበው ያውቃሉ? አስተሳሰብዎ አንደኛ ደረጃ እንዲሆንልዎ ይፈልጋሉ? ለሃገሬ ምን ላርግ እያሉ ውስጥዎ ይቃጠላል? የራስዎን አስተሳሰብ ማስተዳደርና መቆጣጠር ይፈልጋሉ? ወይስ እንደ ነገሩ በእግራችን ተንቀሳቀስን ውለን ካደርን በቂ ነው? እንግዳውስ ወደ ትክክለኛ ጣቢያ መጥተዋል፡፡ ዋናው አላማየ ሁላችንም የኢትዮጵያ ልጆች ተከባብረን በሰላም እንዴት መኖር እንደምንችል በቀላሉ ግልጽ ለማድረግ ነው፡፡ አቅርቦቴ ላይ አንዳንድ ወቀሳወች አሉ፡፡ በጥንቃቄ የተላበሰ ወቀሳ የማቀርበው ግን ግልፅ ባልሆነ አስተሳሰባችን ላይ እንጂ ግለሰቦችን እንዳልሆነ ከወድሁ አሳስባለሁ፡፡ ለጨለማ ጊዜ መብራት እንደሚያስፈልግ ሁሉ ለችገር ጊዜም ብልሃት ያስፈልጋል፡፡ የሰለጠነ ደግ አስተሳሰብ ለማዳበር፤ ከራሴ ጀምሮ ማንም ሰው ቢሆን አቅጣጫና ልምምድ ያስፈልገዋል፡፡ ይኸን ልምምድና አቅጣጫ ለማሳየት የተቻለኝን ልባዊ ጥረት አደርጋለሁ፡፡

ሰው ልጅ ብዙውን ጊዜ አጉል ባህሪው ሲነገረው አይወድም፡፡ ክብሩ የተነካ ይመስለዋል፡፡ በአለማችን ውስጥ ለመቀየር በጣም አስቸጋሪ ነው ከሚባሉት ውስጥ አንዱ፤ የሰወች ባህሪ ነው፡፡ ለምሳሌ ሰወች ሞኝ ሆነው ደግ የሆኑ ይመስላቸዋል፡፡ ሰወች ሲሳደቡ ጥሩ አስተሳሰብ ያለቀባቸው ፈሪ መሆናቸው አይገባቸውም፡፡ ሰወች ሃሳባቸው እንዲወደድላቸው እንጂ እንዲያስከብራቸው ብዙ ቦታ አይሰጡትም፡፡

ሰወች አጭበርባሪና ክፉ ሲሆኑ ከሌላው የተሻሉ ይመስላቸዋል፡፡ ሰወች በማሰብ፣ በማፍቀርና በመስራት ሰንፍ ሆነው በድህነት ውስጥ ቢኖሩም እምነታቸው በቂ ይመስላቸዋል፡፡ በፈጣሪ ፊት ግን ሰንፍ መሆን ሃጢያት እንደሆነ ዘንግተውታል፡፡ ሰወች በራሳቸው አስተሳሰብ ባሪያ ሆነው ነጻ የወጡ ይመስላቸዋል፡፡ ሰወች ከተቅለሰለሱ ወይም ከጮሁ የተሻሉ አማኞች ይመስላቸዋል፡፡ ሁሉም ነገር ጥቁርና ነጭ ነው ማለቴ አይደለም፡፡ በዚሁ ልክ ደግሞ አንዳንድ ጠንካራ አስተሳሰብ ያለቸው ብርቅ ኢትዮጵያውያን እንዳሉ አውቃለሁ፡፡ ሰወች አንድነት ሃይል ነው ይላሉ፡፡ መጀመሪያ ግን አንድነትን የሚገነባ በቂ እውቀት በቦታው መኖር አለበት፡፡ ሰወች ፍቅር ያሸንፋል ይላሉ፡፡ ይኸ ቆንጆ አባባል ቢሆንም በተግባር ሲሰራ ግን አይቼ አላውቅም፡፡ ለዘፈንና ለመዝሙር ግን ይመቻል፡፡ ሁልጊዜ ባዶ መፈክር ይሰለቻል፡፡ ሰወች አዕምሮአቸው አንድ ሊሆን የሚችለው በምክንያት ማሰብ ሲችሉ ነው፡፡ ልባቸው ሊወሃድ የሚችለው በፍቅር ማመን ሲጀምሩ ነው፡፡ የኢትዮጵያ ቁጥር አንድ ጠላት ኋላቀር አስተሳሰብ ነው፡፡ ዶክተር መሆን፣ ቄስ መሆን፣ የሃገር መሪ መሆን ወዘተ የሚያከብርና የሚከበር ባህሪ ከሌላቸው ዞሮ ዞሮ ከኋላ-ቀርነት ፈቅ አያደርግም፡፡

ትዮጵያን በዋነኛነት ወደኋላ የሳባት፤ የብዙዎቻችን መሰረታዊ አስተሳሰብ መዛባት ነው ብየ አስባለሁ፡፡ የባህሪ እንጂ የሃገር መጥፎ የለውም፡፡ በተለይ ኢትዮጵያ በክርስትናም ሆነ በእስልምና የተባረከችና ከፍተኛ ሚስጥረኛ ሃገር ነች፡፡ እንደ ታሪኳ ግዙፍነት ደግሞ እኛ ልጆቿ የሚመጥናት የሰለጠነ አስተሳሰብ ሊኖረን ይገባል፡፡ ፈጣሪ አምላካችንም ያለማቋረጥ በኛ ማዘን የለበትም፡፡ ኢትዮጵያም አፍ አውጥታ የምትናገር ቢሆን፤ በአናቴ ላይ ስትራመዱ ትደብሩኛላችሁ የምትለን ይመስለኛል፡፡

የአንዲት ሃገር ስምና ዝና ሊወደድ ወይም ሊጠላ የሚችለው፤ በዜጋዋ አይነትና ብዛት ሳይሆን በሃገሪቷ ዜጋ ባህሪና ታታሪነት ላይ መሰረት አድርጎ ነው፡፡ ኢትዮጵያ ድሃ የሆነችው በኛ በልጆቿ አስተሳሰብ ምክንያት ነው፡፡ ይኸ ኢትዮጵያዊ ጥሩ ስነ-ምግባር የሚባለውን እኔ በግልጽ ስራ ላይ ውሎ እስካሁን አላየሁትም፡፡ ባየውና ብደርስበት ኖሮ ይኸን ጽሁፍ አልጽፍም ነበር፡፡ የሆነ ጊዜና ቦታ ላይ ግን የሆነ ሰው መናገር አለበት፡፡ አዕምሯችን ፈቃደኛ ከሆነ፤ በሞኝነት ፋንታ ደጎች መሆን እንችላለን፡፡ ልባችን ክፍት ከሆነ ፍቅር ምን እንደሆነ እናውቀዋለን፡፡ ከሰማነው ይልቅ በምናየው ላይ የበለጠ እናተኩራለን፡፡

ኸ ፅሁፍ በትርፍ ጊዜዬ በዝንባሌ ከምሰራቸው ስራወች አንዱ ነው፡፡ ሙያየ አይደለም፡፡ ነገር ግን ሰዋዊ የሆነ ጠንካራ አስተሳሰብ አለኝ ብየ አምናለሁ፡፡ ሞኝ ውኃ ሲወስደው ይስቃል እንደሚባለው ሆነን እንዳንቀር ለወገንና ለሃር በማሰብ ነው፡፡ የሚስተካከሉት ነገሮች ብዙ ጊዜ የሚወስዱ ናቸው፡፡ እራስን ለማስተካከል ግን አሁን መጀመሩ ጥሩ ምርጫ ነው፡፡ እድሜዎ አራትም ይሁን ሰማንያ ትምህርት አያልቅም፡፡ ስለዚህ ይህችን ልዩ ጽሁፍ አይተውና አንብበው ከወደዷት በተግባር እንዲተገብሯት በአክብሮት እጠይቃለሁ፡፡ ይህ ፅሁፍ በኢትዮጵያዊያን ላይ ያተኮረ ቢሆንም ላደጉም ሆነ በማደግ ላይ ላሉ ሃገሮች ጭምር ይጠቅማል፡፡ ጀግናየ ዶት ኮም ጣቢያ የትምህርት መስጫና የሞራል መገንቢያ ጣቢያ ነው፡፡ በተረፈ የጀግናየ ጣቢያ ንድፍ ልክ እንደ ይዘቱ ዘመናዊ ነው፡፡ ብዙው ንድፍ በእጅ የተሰራ ነው፡፡ ፈጣን፣ ንጹህ፣ ግልጽና ምቹ ነው፡፡ ሃሳቦቹም የቤት ናቸው፡፡ ስለዚህ ተረጋግተውና ትኩረት ሰጥተው ቤት ውስጥ የተሰራ የሚጥም ምግብ የሚበሉ እንዲመስልዎት የተቻለኝን ልባዊ ጥረት አድርጌአለሁ፡፡

ከትላንቱ ይልቅ ዛሬ ሁላችንም የተሻለ ሰው መሆን እንችላለን!

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!

Error: No site found with the domain 'tatariw.net'