መነሻ ስለ መጀመሪያ የጽሁፍ ምድቦች መሰረታዊ ኮምፕዩተር ሀሁ - Learn Fidel መሆን የተካነ ባህሪ ያስተሳሰብ ጀግና

ክፍል ፯) ኮምፕዩተርዎ በቀላሉ እንዳይጠቃ ይጠንቀቁ!

mejemeriya computer Ethiopia Amharic Tatariw Addis Ababa Fantaw Tesema ተጠቃሚው ኮምፕዩተር እንዳይሰራ ለማድረግና መረጃወቹንም ለማበላሸት ተባይ እየሰሩ የሚያሰራጩም አሉ፡፡ እኛ በአካል ስለማናየው ነው እንጂ ከፍተኛ የሳይበር ጦርነት አለ፡፡ ለዚህ አላማ፣ ለመከላከልና ለማጥቃትም ጭምር ብዙ ገንዘብና የሰው ሃይል ይውላል፡፡ ዝም ብሎ ግለሰቦችን መሰለል ጥቅም ስለሌለው ብዙው ጥቃትና ስለላ የሚደረገው በድርጅቶችና በሃገሮች መካከል ነው፡፡

ገር ግን ለምሳሌ እንደ ኢትዮጵያ ያለ አምባገነን ሰርአት ያላቸው ሃገሮች ግለሰቦችንም ይሰልላሉ፡፡ አሁን እኔ በድርጅቶችና በሃገሮች መካከል የሚደረገው ስለላ የረቀቀ ስለሆነ አላውቅም፡፡ ግን አንድ ግለሰብ ኮምፕዩተሩ በቀላሉ እንዳይጠቃበት ለመርዳትና ፍንጭ ለማሳየት ነው፡፡ የግል ኮምፕዩተርን ከጥቃት ለመቀነስ ልክ የግል ቤትን መስኮትና በራፍ መቆለፍ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ወደ ከተማም ሲደርሱ መኪናን ፓርክ ካደረጉ በኋላ ሞተሩን አጥፍቶ መከላከያ አላርሙን ቀስቅሶና በራፎቹን ቆልፎ ወደ ሱቅ መሄድ ጋር ይመሳሰላል፡፡ በግልጽ እንደሚታወቀው ቤትን ካልቆለፉ እቃ ይዘረፋል፡፡ መኪናም ካልቆለፉ መኪና ውስጥ ያለው እቃ ይሰረቃል፡፡ መኪናዋ እራሷም ልትወሰድ ትችላለች፡፡ የቤቱም ሆነ የመኪናዋ ባለቤት በተቻለው ሁሉ ጥንቃቄ ማድረግ አልበት፡፡ ሁኔታው ተጋኖ ለምሳሌ ሌባው የተቆለፈውን ቤት በመጥረቢያ ፈልጦ ከገባ ሌላ ጉዳይ ነው፡፡

ና ሲጀመር የሚያውቀውና መዝረፍ ያሰበው ነገር አለ ማለት ነው፡፡ በተመሳሳይም ሌባው መኪናዋን በክሬን አንስቶ እንደተቆለፈች በጭነት መኪና ይዟት ጥርግ ቢል ሌላ ጉዳይ ነው፡፡ ዋናው ቁም ነገር ግን ባለቤቱ በቀላሉ እንዳይጠቃ የመጀመሪያውን ጥንቃቄ ማድረግ አለበት፡፡ በሌላ መልኩ ደግሞ የማያውቁት ሰው በራፍ ቆርቁሮ መግባት ቢፈልግ ሳናጣራ ዝም ብለን ቤት ለንግዳ ብለን ቤቱን አናስረክብም፡፡ ይህን የሚያደርግ ሰው ካለ በቀላሉ ሊጠቃ የሚችል ቂል ሰው መሆን አለበት፡፡ መኪናዋንም በተመለከተ ለምሳሌ ባለቤቱ መኪናዋን እያሽከረከረ እንዳለ ድንገት አንዱ ለመፈናጠጥ ቢጠይቅ የማያውቁትን ሰው ማፈናጠጥ ለአደጋ ሊያጋልጥ ይችላል፡፡

ኮምፕዩተር ደህንነት ለመጠበቅ የቤትና የመኪናው ምሳሌ ጋር ይመሳሰላል፡፡ የሚለያቸው ነገር ቢኖር የቤትና የመኪና ጥቃት አካላዊ ነው፡፡ የኮምፕዩተር ጥቃት ግን ስውር ነው፡፡ ይኸን ስውር የሆነ ኮምፕዩተር ጥቃት ለመከላከል ደግሞ እራሱን የቻለ ቀላል የሆነ የመከላከያ እርምጃ አለው፡፡ ይህ መከላከያ እርምጃ ግን እንደ ሽንኩርት ልጫ የተደራረበ ስለሆነ የሚያሰለች ሊሆን ይችላል፡፡ በደረጃና በሽፋን የተከፋፈለ ነው፡፡ ብዙውን ጊዜ ሰወች ኮምፕዩተራቸው የሚጠቃው ባለማወቅና በችልተኝነት ነው፡፡ ዋናው የሚያጋልጣቸው ምክንያት ግን የኮምፕዩተር አጠቃቀም ባህሪያቸው ነው፡፡ ይህ እንዴት እንደሆነ የሚቀጥለው ክፍል ላይ አቀርባለሁ፡፡ የመጨረሻው ክፍል ላይ ደግሞ በቀላሉ ጥቃትን እንዴት መቀነስ እንደሚቻል በዝርዝር አቀርባለሁ፡፡

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!

አስተያየት መስጫ፤

* ተፈላጊ መረጃ
1000
Captcha Image

አስተያየቶች

እስከ አሁን አስተያየት አልተሰጠም፡፡ የመጀመሪያ ይሁኑ!