መሰረታዊ ትውውቅ የኮምፕዩተር አካሎች ኦፕሬቲንግ ሲስተም ሶፍትዌር ምንድነው? ትክክለኛ አጠቃቀም ደህንነትና ይለፍ-ቃል የአጠቃቀም ጥንቃቄ የኮምፕዩተር ደህንነት ቫይረስ ምንድነው?

jegna Ethiopia Amharic Tatariw jegnye Addis Ababa Fantaw Tesema

ክፍል ፰) የኦፕሬቲንግ ሲስተም እንክብካቤና ደህንነት፤

May 19, 2014. እርማት 2020

ታወቁትና ዋና ዋና ኦፐሬቲንግ ሲስተሞች ዊንዶውስ፣ ማክ እና ሊነክስ ናቸው፡፡ ኦፐሬቲንግ ሲስተም ማለት ምን እንደሆነ በፊት በቀላሉ አስረድቻለሁ፡፡ ብዙ ሰው ዊንዶውስ ለጥቃትና ለስለላ የተጋለጠ ነው፡፡ ይህ ማለት ዊንዶውስ ለመጠቃት ብዙ ቀዳዳ ስላለው በተደጋጋሚ ይጠቃል፡፡ በተለይ ተጠቃሚው ቀላልና ተገቢ ጥንቃቄ ካላደረገ ሳይታወቅ ጭምር ብላሽ ሶፍትዌሮች ኮምፕዩተሩ ላይ ሊሰፍሩ ይችላሉ፡፡

jegnaye Ethiopia Amharic Tatariw jegna mejemeriya Addis Ababa Fantaw Tesema ነዚህን ብላሽ ሶፍትዌሮች ለማስወገድ አንቲ-ቫይረስ እየተባሉ የሚሸጡ ሶፍትዌሮች አሉ፡፡ እነዚህ ሶፍትዌሮች 100% ሊረዱ አይችሉም፡፡ ሆኖም ግን አንቲ-ቫይረስ እየተባለ ተጠቃሚው ተጨማሪ ሶፍትዌር እንዲገዛ ይደረጋል፡፡ ለአንዳንዶች ንግድና መኖሪያ እንጀራ ነው፡፡ ዊንዶውስ ስራወችን ኮምፕዩተሩ ላይ ለማከናወን ከጊዜ ወደ ጊዜ ዘገምተኛ መሆኑ የተለመደ ነው፡፡ ማይክሮሶፍት፤ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙን ቢያመርትም ሃርድዌሩንና ሌሎች ተጨማሪ ሶፍትዌሮች ግን በሌላ ድርጂት የሚመረቱ ናቸው፡፡ በዚህም ምክንያት ዊንዶውስን ለተጨማሪ ጥቃት ያጋልጠዋል፡፡

ክ አፐል የሚባል ድርጂት የሚሰራው ነው፡፡ አፐል የኮምፕዩተሩን ሃርድዌር፣ ኦፕሬቲንግ ሲስተሙንና ተጨማሪ ፕሮግራሞችንም በራሱ ዘይቤ ይሰራል፡፡ በዚህም ምክንያት ሲስተሙ ከዊንዶውስ የበለጠ ዝግ ስለሆነ በቫይረስ የመጠቃቱ እድል አነስተኛ ነው፡፡ ለስለላ የመጠቃት እድሉ አነስተኛ ነው፡፡ ሽያጭን በተመለከተ የማክ ዋጋ ከዊንዶውስ ይበልጣል፡፡ ብዙ ግራፊክስ ነክ የሚሰሩና የዜና አውታሮች ይጠቀሙበታል፡፡ ማክ እኔ ተጠቅሜ አላውቅም ግን ማክ አስተቸገርኝ የሚሉ ጥቂቶች አይደሉም፡፡ ሆኖም ግን አንድ ሰው ማክን ጊዜ ተጠቅሞ ከተለማመደ በዛው ይቀራል ይባላል፡፡

ነክስ ባጭሩ ኮዱ ክፍት ምንጭ ነው፡፡ በአለም ውስጥ ባሉ ስማርት ህብረተሰቦች የሚሰራ ነው፡፡ ለመጠቀም ነጻም ነው፡፡ ሰሪው ህብረተሰቡ ገቢ የሚያገኘው በልገሳና በድጋፍ ሰጪወች ነው፡፡ ሊነክስን ማጥቃት በጣም አስቸጋሪ ነው፡፡ ምክንያቱም ሊነክስ በህብረተሰብ ስለሚሰራና ስለሚዳብር ሊነክስ ላይ የመጠቃት ጥርጥራ ከታየ ወዲያውኑ ስለሚነቃ ቶሎ ብሎ ህብረተሰቡ መፍትሄ ያገኛል፡፡ ቀዳዳው ይደፈናል፡፡ ችግሩ ይታረማል፡፡ ግለሰቦች ሊነክሰን ልክ እንደ ዊንዶውስና ማክ መጠቀም ይችላሉ፡፡ ሊነክሰን የበለጠ ልዩ የሚያደርገው ደግሞ ትልልቅ ካምፓኒወች፣ ድረጅቶች፣ ባንኮች፣ መንግስቶች፣ ወዘተ ሰርቨራቸው ላይ ሊነክስን በሰፊው ይጠቀማሉ፡፡ ምክንያቱም ሊነክስን መጠቀም ነጻ ሞኑና ደህንነቱ ብቻ ሳይሆን ፍጥነትም አለው፡፡

ንደ ዊንዶውስ በቀላሉ ነክሶ አይቆምም፡፡ እነዚህ የጠቀስኳቸው ሊነክስን የሚጠቀሙ ድርጅቶች ሰርቨራቸው 24 ሰአት ሙሉ ያለማቋረጥ መስራት ስላለበት ሊነክስ ከዊንዶውስ የበለጠ አስተማማኝ ነው፡፡ ታዲያ እንዚህ ድርጅቶች ከሊነክስ ህብረተሰብ ካምፓኒ ጋር ቴክኒካዊ ኮንትራት አላቸው፡፡ ይኸ ማለት የሊነክስ ህብረተሰብ ከልገሳና ከድጋፍ ሰጪ በተጨማሪ ሌላም ገቢ አለው ማለት ነው፡፡ እስካሁን ድረስ ብዙ ሰወች ሊነክስ የተሰራው ለሰርቨር እንጂ እንደ ዊንዶውስ በግል ለመጠቀም አስቸጋሪ ነው ብለው ይገምታሉ፡፡ ይህ አባባል ለምሳሌ ከ1990ወቹ አመታት በፊት ቢሆን ኖሮ በከፊል ትክክል ነው፡፡ አሁን ግን በተለይ ከ 2000 ዓ.ም. ጀምሮ ሊነክስን በግል ለመጠቀም እንዳውም ከዊንዶውስ ይቀላል፡፡ ሊነክስ ባለቤት የለውም ብለው እርዳታ ሲፈልጉ ቶሎ እርዳታ የማያገኙ ስለሚመስላቸው ሊነክስን ለመጠቀም የሚፈሩ ሰወች አሉ፡፡ ነገር ግን ኢንተርኔት ላይ የሊነክስ ህብረተሰብ ንቁ ተንቀሳቃሽ ስለሆነ ቶሎ ምላሽ ይሰጣል፡፡

ላይ ከጠቀስኩት ጥቅሞች በተጨማሪ ደግሞ የሚያስፈልጉ ሶፍትዌሮች በሙሉ አንድ ቦታ ላይ ስላሉ አያስቸግርም፡፡ ሃርድዌሮቹን የሚያጣጥሙት ሶፍትዌሮችን እንኳን ለማግኘት እንደ ዊንዶውስ ከሌላ ቦታ ፈልጎ ማምጣት አያስፈልግም፡፡ ሁሉም ነገር ተጣጥሞ ኮምፕዩተሩ ላይ ይሰፍራል፡፡ በአማርኛ ወይም በሌላ ቋንቋ እዛው በቀላሉ መጻፍ ይቻላል፡፡ ከ20 አመታት በፊት አካባቢ ጀምሮ እኔ በዊንዶውስና በሊነክስ መካከል እያፈራረቅሁ እጠቀም ነበር፡፡ ያው አሁንም ቢሆን ዊንዶውስና ሊነክስ ሁለቱም እራሱን የቻለ ጠንካራና ደካማ ጎን አላቸው፡፡ አሁን ግን ሊነክስ በጣም ተሻሽሏል፡፡ በእይታም ደረጃ ሊነክስ ውብ ነው፡፡ ከውስጥም ሆነ ከውጭ ቆንጆ እንደሆነች ሴት ፍቅር ያስያዛል፡፡ እውነቴን ነው! አንድ ኮምፕዩተር ላይ ሊነክስን ለመሞከር የግድ ኮምፒውተሩ ላይ በቀጥታ ማስፈር አያስፈልግም፡፡ በሲዲ፣ ዲቪዲ ውይም ዩኤስቢ ቀድቶ ካዛ ላይ መሞከርና መንዳት ይቻላል፡፡ ሊነክስን እዛው ተመሳሳይ ኮምፕዩተር ላይ ከዊንዶውስ ጎን ወይም ላዩ ላይ ጭኖ መሞከር ይቻላል፡፡ ሊነክስ የዚህን ያህል ቀላልና ሁለገባዊ ነው፡፡

እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!

Error: No site found with the domain 'tatariw.net'