ሰውና አስተሳሰብ ሲጠያየቁ
ያስተሳሰብ ጀግና ስል አንድ ሰው ባመነበት ነገር ላይ ገትሮ ሲይዝ ለማለት ነው፡፡ ባጭሩ ያስተሳሰብ ጀግና ማለት አንድ ሰው ያሰበውን ለማሳካት በቀጣይነት የሚያደርገው ሃሳባዊ ትግልና ጥልቅ ፍለጎት ነው፡፡
እራሴን ለማወቅ ሰጥቼው ፈተና፣
ሳፈላልግ ነበር የአዕምሮን ቁንጅና፣
አየኋት ተገኘች ያስተሳሰብ ጀግና !
እጆቼን ዘርግቼ ሰላምታ ልሰጣት፣
ናፍቆቴን ላሳያት፣
ፍቅሬን ልገልጽላት፣
ዘመናት አልፈዋል እሷን ስፈልጋት፣
በስተመጨረሻ ዛሬስ አገኘኋት፣
እስከሚዘረጉ እጆቿን ጠበኳት ፡፡
የሃሳብን እጆች አጣኋቸው የሉም፣
መንካትም አልቻልኩም፣
ማየትም አልቻልኩም፡፡
እኔ ኮ አልታይም አንተ ሞኝ ሰው፣
እንዴት ወዲህ መጣህ ወደማታውቀው፣
ከቶ ለምድነው አይንህ ያላየው?
አዕምሮህስ ቢሆን የት አደረስከው?
እኔ እምገለጠው ለሚያስብ ሰው ነው!
ታውቀኛለህ እንዴ የምን ጠጋ ጠጋ፣
እንዲህ በቀላሉ አይኾንም ጀግና፣
ሌላ ጊዜ ናልኝ ተለማመድና፣
ስትጠቀምበት ያለህን ማሰቢያ፣
ያኔ ትሆናለህ ያስተሳሰብ ጀግና፣
እጅ እየዘረጋህ ሞኝ አትሁንብኝ፣
ማሰብ ተለማመድ እኔን ከፈለከኝ!
ይኸንን አትርሳ እኔን እንዲታውቀኝ፡፡
በቀጭን ቀጠሮ አሰናበተኝ፣
ቀጠሮየን ይዤ እኔም ተመለስኩኝ፣
ምን እንዳጋጠመኝ እያሰላሰልኩኝ፣
አይቀርም አንድ ቀን አገኛታለሁኝ!
እጄን ሳልዘረጋ እግባባታለሁኝ፡፡
እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!