አዲስ ዓመት 2013 ላይ ምንድነው የኔ እድገት?
አዲስ ዓመት ሲገባ ምንድነው የኔ እድገት?
365 የአመቱ ቀናት፣
ቁጥሮች ስለሞሉ ምንድነው የኔ እድገት?
ትምህርት ለመውሰድ ካለ ያጠፋሁት
ገትሮ ለመያዝ ካለ ያለማሁት
በጎ ወይስ መጥፎ ካፌ ያወጣሁት?
ሰው ስለመሆኔ ምንድነው ያሰብሁት?
ዝም ብዬ እያየሁ ባሪያ የሆንኩበት፣
ወይም ወገኔ ላይ ጨካኝ የሆንኩበት፣
ቀና ሃሳብ ካለኝ ለማሳየት ውጤት፣
አንድ ሁለት ብዬ የሚቆጠር ስኬት፣
ምን እንደሰራሁኝ ልኩን የማይበት፣
ውሸት የሌለበት፣
መጀመሪያ ክብር ስለ ሰው ልጅ ህይወት
መከበር ከፈልግሁ በሰፊው ህዝብ ፊት፡፡
መልካም አዲስ ዓመት!
ኮተት ያልበዛበት
እዚህ ድረስ ስላነበቡ አመሰግናለሁ! ከታች አስተያየት ለመስጠት አይርሱ!!
Error: No site found with the domain 'tatariw.net'